የ2004 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት
1 ይሖዋ ተራ የሆኑ ሰዎች በዓለም ዙሪያ መከናወን ያለበትን ሥራ እንዲፈጽሙ እያስታጠቃቸው ነው። ይህን የሚያደርግበት አንደኛው መንገድ በየሳምንቱ በሚካሄደው ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት አማካኝነት ሥልጠና በመስጠት ነው። ሁኔታህ በፈቀደልህ መጠን በትምህርት ቤቱ የተሟላ ተሳትፎ እያደረግህ ነው? ተማሪዎች ከዝግጅቱ የላቀ ጥቅም እንዲያገኙ ለማስቻል ከጥር 2004 ጀምሮ አንዳንድ ማሻሻያዎች ተግባራዊ ይሆናሉ።
2 ረዳት ምክር ሰጪዎች ይቀያየራሉ:- ማስተማሪያ ንግግርና የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ጎላ ያሉ ነጥቦች የሚያቀርቡ ወንድሞች ረዳት ምክር ሰጪው የሚሰጣቸው ሐሳብ እንደጠቀማቸው ተናግረዋል። በጉባኤው ውስጥ ጥሩ ችሎታ ያላቸው በቂ ሽማግሌዎች ካሉ ረዳት ምክር ሰጪ ሆኖ የማገልገሉ ኃላፊነት በየዓመቱ በዙር ሊደርሳቸው ይችላል። በዚህ መንገድ የሥራውን ጫና የሚጋሩ ከመሆኑም በላይ እነዚህን ክፍሎች የሚወስዱ ሽማግሌዎችና ጥሩ ችሎታ ያላቸው የጉባኤ አገልጋዮች፣ ንግግር የማቅረብና የማስተማር ብቃት ያላቸው የተለያዩ ወንድሞች ካላቸው ችሎታ ጥቅም ያገኛሉ።
3 የቃል ክለሳ ፕሮግራሙን ማስተካከል:- የቃል ክለሳ በሚቀርብበት ሳምንት ጉባኤያችሁ የወረዳ ስብሰባ የሚያደርግ ከሆነ ክለሳው (እና በሳምንታዊ ፕሮግራሙ ላይ ያሉት ሌሎች ክፍሎች) አንድ ሳምንት ዘግይቶ የሚቀርብ ሲሆን የቀጣዩ ሳምንት ፕሮግራም ደግሞ አንድ ሳምንት አስቀድሞ መቅረብ አለበት። ሆኖም የቃል ክለሳውና የወረዳ የበላይ ተመልካቹ ጉብኝት በሚገጣጠሙበት ጊዜ የሁለቱን ሳምንት ፕሮግራሞች ሙሉ በሙሉ ማቀያየር አያስፈልግም። ከዚህ ይልቅ በፕሮግራሙ ላይ የሰፈረው መዝሙር፣ የንግግር ባሕርይና የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ጎላ ያሉ ነጥቦች መቅረብ አለባቸው። የማስተማሪያ ንግግሩ (ከንግግር ባሕርይ ቀጥሎ ይቀርባል) ለሚቀጥለው ሳምንት ከወጣው ፕሮግራም ላይ ይወሰዳል። የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ጎላ ያሉ ነጥቦች ከቀረበ በኋላ ለግማሽ ሰዓት ያህል የአገልግሎት ስብሰባ የሚካሄድ ሲሆን ሦስት የ10 ደቂቃ ክፍሎች ወይም ሁለት የ15 ደቂቃ ክፍሎች እንዲቀርቡ ፕሮግራሙን ማስተካከል ይቻላል። (ማስታወቂያ አይቀርብም።) የአገልግሎት ስብሰባው ሲያበቃ መዝሙር ይዘመርና ለግማሽ ሰዓት ያህል የወረዳ የበላይ ተመልካቹ ፕሮግራም ይቀርባል። በቀጣዩ ሳምንት፣ በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም ላይ የወጡት የንግግር ባሕርይ እና የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ጎላ ያሉ ነጥቦች ከቀረቡ በኋላ የቃል ክለሳው ይቀጥላል።
4 መንፈሳዊ እድገት እንድታደርግ በሚያስችልህ በእያንዳንዱ አጋጣሚ ተጠቀም። በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና መጠቀምህን ስትቀጥል ጉባኤው በአንተ ይታነጻል፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት አፈጻጸም ረገድ ድርሻ ይኖርሃል እንዲሁም እንድናውጀው የተሰጠን አስደናቂ መልእክት ባለቤት ይወደሳል።—ኢሳ. 32:3, 4፤ ራእይ 9:19