ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ታኅሣሥ:- እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው። በአማራጭነት የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ፣ መጽሐፍ ቅዱስ—የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው? ወይም በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ የተባሉትን መጽሐፎች ማበርከት ይቻላል። ጥር:- ጉባኤው ያለው ከ1988 በፊት የታተመ ማንኛውም መጽሐፍ። እነዚህ መጽሐፎች ከሌሏችሁ ጎረቤት ጉባኤዎች እንደ መንግሥትህ ትምጣ ወይም የቤተሰብህን ኑሮ አስደሳች አድርገው የመሳሰሉት መጽሐፎች ትርፍ ይኖሯቸው እንደሆነ ጠይቁ። የቆዩ መጽሐፎች የሌሏቸው ጉባኤዎች የሰው ዘር አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ የተባለውን የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ማበርከት ይችላሉ። የካቲት:- ድሮው ክሎዝ ቱ ጀሆቫ። አማርኛ:- ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል! መጋቢት:- ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። አዳዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ለማግኘት ልዩ ጥረት ይደረጋል። የምናነጋግራቸው ሰዎች ይህ መጽሐፍ ካላቸው የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል! የተባለውን መጽሐፍ ማበርከት ይቻላል።
◼ ከመጋቢት እስከ ግንቦት ባሉት ወራት ጊዜያዊ ልዩ አቅኚ ሆናችሁ ማገልገል የምትፈልጉ የዘወትር አቅኚዎች፣ ሽማግሌዎች ወይም የጉባኤ አገልጋዮች የሚከተሉትን መረጃዎች በትልቅ ወረቀት ጽፋችሁ እስከ ታኅሣሥ 31, 2003 ድረስ ልትልኩልን ትችላላችሁ:- 1) ስም 2) ዕድሜ 3) የተጠመቅክበት ቀን 4) የጋብቻ ሁኔታ [ነጠላ ወይም ያገባ መሆኑንና የሚያስተዳድረው ቤተሰብ ብዛት] 5) ለማገልገል የምትችልባቸው ወራት [ከመጋቢት እስከ ግንቦት?] 6) የምትናገራቸው ቋንቋዎች 7) አመልካቹ ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው ሥራ አዘውትሮ የሚካፈል መሆን አለመሆኑን። ከዚያም የጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ አባላት የድጋፍ ሐሳባቸውን ካሰፈሩ በኋላ ይፈርሙበታል።
◼ በሒሳብ አገልጋይነት የሚሠሩ ወንድሞችን ለማስታወስ ያህል፣ ለዓለም አቀፉ ሥራ እና ለመንግሥት አዳራሾች ግንባታ የሚሰበሰቡት መዋጮዎች በየወሩ ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው መላክ ይኖርባቸዋል እንጂ የመንግሥት አዳራሽ ብድር ለመክፈል ወይም ሌሎች የጉባኤውን ወጪዎች ለመሸፈን መዋል አይኖርባቸውም።