የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 12/03 ገጽ 4
  • የግንባታ ፕሮጄክት ዜና

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የግንባታ ፕሮጄክት ዜና
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
km 12/03 ገጽ 4

የግንባታ ፕሮጄክት ዜና

አዲሱ የቤቴል ሕንጻና የመሰብሰቢያ አዳራሽ የግንባታ ፕሮጄክት በክረምቱ ወራት እንኳን ሥራው ጥሩ እድገት አሳይቷል። ሁለቱም የግንባታ ፕሮጄክቶች ጣሪያ የለበሱ ሲሆን አብዛኞቹ በሮችና መስኮቶች ተገጥመዋል። አሁን የቀረው ውስጡን ማጠናቀቅ፣ ለመሰብሰቢያ አዳራሹ የሚሆን መጸዳጃ ቤትና የፍሳሽ ማስወገጃ የመገንባት ሥራ ነው። በዚህ እትም ላይ የወጡት ፎቶግራፎች የተነሱት በመስከረም ውስጥ ሲሆን ስለ ግንባታው ፕሮጄክት እድገት የተሻለ ግንዛቤ ይሰጧችኋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ግንባታው በሚቀጥለው ግንቦት ይጠናቀቃል ብለን እንጠብቃለን። በእነዚህ ሕንጻዎች የምንጠቀምበትን ጊዜ በጉጉት የምንጠባበቅ ሲሆን በጸሎትና መዋጮ በማድረግ የምታደርጉትን ድጋፍ እናደንቃለን።

በዚህ አጋጣሚ በመንግሥት አዳራሽ የግንባታ ቡድኖች ስለተከናወነው ሥራ ብንገልጽላችሁ ደስ ይለናል። ባለፈው ዓመት የሚከተሉት የመንግሥት አዳራሾች ተገንብተው ተጠናቅቀዋል:- በአዲስ አበባ:- አየር ጤና/ምዕራብ፣ አማኑኤል፣ አራት ኪሎ/ስድስት ኪሎ፣ አቃቂ/ቃሊቲ፣ እንጦጦ/ሽሮ ሜዳ፣ ገርጂ/መገናኛ እንዲሁም ሳሪስ/ገላን። ከአዲስ አበባ ውጪ:- ቦዲቲ፣ ቡታጅራ፣ ጫኖ (አርባ ምንጭ አካባቢ)፣ ፍቼ፣ ጢስአባሊማ (ወልድያ አካባቢ)፣ አድዋ፣ ቱላ (አዋሳ አካባቢ)፣ ዊቾ እና ቤራ (ይርጋለም አካባቢ)፣ ሆማቾ እና ዌሌሃንገላ (አለታ ወንዶ አካባቢ)፣ ደንቢዶሎ፣ ሱሉልታ (አዲስ አበባ አካባቢ)፣ በቅሎ ሰኞ እና ኮቴ ገነት እንዲሁም ጉርሙ ኮይሻ እና ኦፋሴሬ (ሶዶ አካባቢ)፣ ቀርሰዲ (ፊንጫ አካባቢ)፣ ኮምቦልቻ፣ መንዲ እና መተሃራ። ከዚህ መገንዘብ እንደሚቻለው እስከ አሁን የግንባታ ቡድኖቻችን 80 የሚያህሉ የመንግሥት አዳራሾችን አጠናቅቀዋል። ከእነዚህ መካከል አንዳንዶቹ ገጠር ውስጥ ርካሽ የግንባታ ቁሳቁሶችን በመጠቀም የተሠሩ ናቸው። ሆኖም ሁሉም ለዓይን ማራኪና ንጹሕ ናቸው። በዓለም አቀፉ የወንድማማች ማኅበራችን ድጋፍ ላገኘናቸው ለእነዚህ ዝግጅቶች ያለን አድናቆት ከፍተኛ ነው። እነዚህ አዳራሾች የእውነት አምላክ የሆነውን ይሖዋን የሚያመልኩ ብዙ አዳዲስ ሰዎችን ለመርዳት ያገለግላሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን።

[በገጽ 4 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

አዲሱ የቤቴል ቢሮ እና የመኖሪያ ሕንጻ

[በገጽ 4 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ከፊት ለፊት ያለው የመሰብሰቢያ አዳራሹ ሲሆን በርቀት የሚታየው ጸግሞ የቅርንጫፍ ቢሮው ሕንጻ ነው

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ