የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
የካቲት 9 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 34 (77)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የታኅሣሥ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የታኅሣሥ 2003 ንቁ! መጽሔቶችን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አስፋፊው የሚያስተዋውቀው አንዱን መጽሔት ብቻ ቢሆንም ሌላኛውንም አያይዞ ያበረክታል። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ ውይይቱን ለማስቆም “የራሴ ሃይማኖት አለኝ” ለሚል ሰው ምን መልስ መስጠት እንደሚቻል የሚያሳይ ይሁን።—ማመራመር መጽሐፍ ገጽ ከ18-19ን ተመልከት።
10 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
25 ደቂቃ:- “ስለ ይሖዋ ድንቅ ሥራዎች መናገራችሁን ቀጥሉ።” (ከአንቀጽ 1-10) አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ። ለአንቀጾቹ የቀረቡትን ጥያቄዎች ተጠቀም። ሁሉም በመታሰቢያው በዓል ሰሞን የአገልግሎት እንቅስቃሴያቸውን ከፍ እንዲያደርጉ አበረታታ።
መዝሙር 23 (48) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 16 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 22 (47)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ:- “መለኮታዊ ድጋፍ ያለው ሥራ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አዋጅ ነጋሪዎች ከተባለው መጽሐፍ ገጽ 547-48 ላይ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።
20 ደቂቃ:- “ስለ ይሖዋ ድንቅ ሥራዎች መናገራችሁን ቀጥሉ።” (ከአንቀጽ 11-17) አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ለአንቀጾቹ የቀረቡትን ጥያቄዎች ተጠቀም። አንድ አስፋፊ ተመላልሶ መጠየቅ የሚያደርግለትን ሰው ወደ መታሰቢያው በዓል ሲጋብዘው የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 13 (33) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 23 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 95 (213)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። በሚቀጥለው ሳምንት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለሚደረገው ውይይት ሁሉም ባለፈው የአገልግሎት ዓመት በተደረገው የልዩ ስብሰባ ቀን ላይ የያዙትን ማስታወሻ ከልሰው እንዲመጡ አበረታታቸው። በገጽ 8 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የታኅሣሥ 15 መጠበቂያ ግንብ እና የታኅሣሥ 22, 2003 ንቁ! (እንግሊዝኛ) መጽሔቶችን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አስፋፊው የሚያስተዋውቀው አንዱን መጽሔት ብቻ ቢሆንም ሌላኛውንም አያይዞ ያበረክታል። በአንደኛው ሠርቶ ማሳያ መደምደሚያ ላይ አስፋፊው በቀጣዩ ጉብኝት ወቅት አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር ተጠቅሞ መልስ የሚሰጥበት አእምሮን የሚያመራምር ጥያቄ ያቀርባል።
15 ደቂቃ:- “ዘወትር በስብሰባ ለመገኘት ቅድሚያ መስጠት አለብን።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በሁሉም የጉባኤ ስብሰባዎች ላይ ለመገኘት ያደረጓቸውን ማስተካከያዎች የሚናገሩ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች አስቀድመህ አዘጋጅ።
20 ደቂቃ:- ይሖዋን ‘በጉባኤ መካከል’ አመስግኑት። በመስከረም 1, 2003 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 19-22 ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። (1) መዝሙር 22:22, 25 በስብሰባዎች ላይ ሐሳብ የምንሰጥበትን ምክንያት የሚያሳየው እንዴት ነው? (2) ጸሎት ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው? (3) ዝግጅት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (4) ሁላችንም በስብሰባዎች ላይ ምን የማድረግ ግብ ሊኖረን ይገባል? (5) በስብሰባዎች ላይ ከፊት ለፊት መቀመጣችን ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው? (6) ሌሎች የሚሰጡትን ሐሳብ በጥሞና ማዳመጥ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (7) በራሳችን አባባል ሐሳብ መስጠት የምንችለው እንዴት ነው? (8) በምንሰጣቸው ሐሳቦች ሌሎችን ማበረታታት የምንችለው እንዴት ነው? (9) ስብሰባውን የሚመራው ወንድም ምን ኃላፊነት አለበት?
መዝሙር 36 (81) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መጋቢት 1 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 67 (156)
5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የየካቲት የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በመጋቢት የሚበረከተውን ጽሑፍ ከተናገርክ በኋላ በጥር 2002 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይ ከወጡት አቀራረቦች ውስጥ አንዱን በአጭሩ ተናገር።
25 ደቂቃ:- በበጎ ሥራ ባለጠጎች ሁኑ። (1 ጢሞ. 6:18 የ1954 ትርጉም ) ከታች የቀረቡትን ጥያቄዎች በመጠቀም አንድ የጉባኤ ሽማግሌ ባለፈው የአገልግሎት ዓመት የተካሄደውን የልዩ ስብሰባ ፕሮግራም ከአድማጮች ጋር በውይይት ይከልሳል። አድማጮች በስብሰባው ላይ የተማሩትን በሥራ ላይ ማዋል የቻሉት እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ ጋብዝ። (ሐሳብ የሚሰጡባቸውን ነጥቦች አስቀድሞ ማከፋፈል ይቻላል።) በሚከተሉት የፕሮግራሙ ክፍሎች ላይ ተወያዩ:- (1) “በበጎ ሥራ መካፈል ብዙ በረከት ያስገኛል።” (መክ. 2:11) የአምላክ አገልጋዮች ከዚህ ዓለም ከንቱ ሥራዎች ይልቅ በአምላክ ቃል ውስጥ የተገለጹትን በጎ ሥራዎች የሚያከናውኑት ለምንድን ነው? (2) “በአምላክ ዘንድ ባለጠጋ ሁኑ።” (ማቴ. 6:20) አንዳንዶች ‘በሰማይ መዝገብ የሰበሰቡት’ እንዴት ነው? ይህስ ምን ጥቅሞች አስገኝቶላቸዋል? (3) “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በማስጠናት በአገልግሎታችሁ ባለጠጎች ሁኑ።” (om ገጽ 91) የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማግኘትና ለማስጠናት ምን ሊረዳን ይችላል? (4) “በዚህ የመከር ወቅት የምንሠራቸው መልካም ሥራዎች።” (ማቴ. 13:37-39) በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩት ክርስቲያኖች በጎ ሥራዎችን በመሥራት ረገድ ምን ምሳሌ ትተውልናል? የመንግሥቱ የስብከት ሥራ በጊዜያችን እየተስፋፋ ያለው እንዴት ነው? (5) “መልካም ሥራችሁ ይሖዋን የሚያስከብር ይሁን።” (ማቴ. 5:14-16) አንዳንዶች ‘ብርሃናቸውን ያበሩት’ እንዴት ነው? (6) “ይሖዋን በማወደስ ለሚያከናውኑት መልካም ሥራ ወጣቶችን ማመስገን።” (መዝ. 148:12, 13) በወረዳችን ውስጥ ክርስቲያን ወጣቶች ይሖዋን እያወደሱ ያሉት እንዴት ነው? (7) “በጎ ሥራ በመሥራት የይሖዋን በረከት ማጨድ።” (ምሳሌ 10:22) በጎ ሥራዎችን መሥራታችንን ስንቀጥል በግለሰብ፣ በቤተሰብ፣ በጉባኤና በድርጅት ደረጃ ምን በረከቶችን እናገኛለን?
15 ደቂቃ:- “ይሖዋ የሚፈልግብንን ማሟላት እንችላለን።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ለአንቀጾቹ የቀረቡትን ጥያቄዎች ተጠቀም። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ በተጠቀሱት ጥቅሶች ላይ ሐሳብ እንዲሰጥ አድርግ።
መዝሙር 43 (98) እና የመደምደሚያ ጸሎት።