ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች መጋቢት:- ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። አዳዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ለማግኘት ልዩ ጥረት ይደረጋል። የምናነጋግራቸው ሰዎች ይህ ጽሑፍ ካላቸው የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል! የተባለውን መጽሐፍ ማበርከት ይቻላል። ሚያዝያ እና ግንቦት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች ይበረከታሉ። በመታሰቢያው በዓል ወይም በሌሎች ስብሰባዎች ላይ ቢገኙም ወደ ጉባኤ ስብሰባዎች አዘውትረው ለማይመጡ ሰዎችና ፍላጎት ላሳዩ ሌሎች ሰዎች ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርጉ የአምልኮ አንድነት የተባለውን መጽሐፍ ለማበርከት ጥረት አድርጉ። በተለይ የምናነጋግራቸው ሰዎች እውቀት መጽሐፍንና አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር አጥንተው ከነበረ በዚህ መጽሐፍ ተጠቅሞ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ልዩ ጥረት መደረግ ይኖርበታል።
◼ አንዳንድ ጉባኤዎች መጽሔቶችን ወይም ሌሎች ጽሑፎችን ተሰብሳቢዎች ራሳቸው አንስተው መውሰድ እንዲችሉ አዳራሹ ውስጥ ጠረጴዛ ላይ እንደሚደረድሩ ተስተውሏል። ጽሑፎችን ለአስፋፊዎች (የሚጠኑ ጽሑፎች ከሆኑ ደግሞ ፍላጎት ላላቸው ሰዎች) እንዳስፈላጊነቱ በጥንቃቄ የማከፋፈሉ ኃላፊነት የተጣለው በመጽሔት አገልጋዩና በጽሑፍ አገልጋዩ ላይ በመሆኑ ይህ አሠራር መቅረት አለበት። የመንግሥት አገልግሎታችንን ለአስፋፊዎችና አዘውትረው በአገልግሎት ስብሰባችን ላይ ለሚገኙ ሰዎች ማከፋፈል ያለባቸው የመጽሐፍ ጥናት የበላይ ተመልካቾች በመሆናቸው ተሰብሳቢዎች ራሳቸው እንዲወስዱ ጠረጴዛ ላይ መቀመጥ የለበትም።—1 ቆሮ. 14:40
◼ የዚህ ዓመት ልዩ የሕዝብ ንግግር የሚቀርበው እሁድ፣ ሚያዝያ 18, 2004 ነው። ርዕሱ “ደፋሮች ሁኑ፣ በይሖዋ ታመኑ” የሚል ነው። የሕዝብ ስብሰባቸውን ቅዳሜ የሚያደርጉ ጉባኤዎች ንግግሩን የሚያቀርቡት ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 24 ይሆናል። የወረዳ የበላይ ተመልካቹ ጉብኝት ሚያዝያ 18 ላይ በሚውልባቸው ጉባኤዎች ንግግሩ ሚያዝያ 25 ላይ ይቀርባል። በመታሰቢያው በዓል ላይ የተገኙትንና ፍላጎት ያላቸውን ሌሎች ሰዎች ለመጋበዝ ጥረት አድርጉ።
◼ እንደገና የደረሱን ጽሑፎች:- አማርኛ፦ ትራክት ቁጥር 19-22። አረብኛ፦ እውቀት፣ ዎርሺፕ ጎድ፣ አምላክ ስለ እኛ ያስባልን?፣ ሥላሴ፣ የቪዲዮ ካሴቶች:- መጽሐፍ ቅዱስ። እንግሊዝኛ፦ መጽሐፌ፣ ዎርሺፕ ጎድ፣ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፣ አዎጅ ነጋሪዎች፣ የመዝሙር መጽሐፍ (ትንሹ)፣ አፕላይ ዩርሰልፍ ቱ ሪዲንግ፣ አምላክ ስለ እኛ ያስባልን?፣ በደስታ ኑር፣ ሳትስፋይንግ ላይፍ፣ ሥላሴ፣ የተለያዩ የቪዲዮ ካሴቶች፣ ትራክት ቁጥር 14, 16, 19, 21-24። ፈረንሳይኛ፦ መጽሐፌ።