የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 3/04 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
  • ንዑስ ርዕሶች
  • መጋቢት 8 የሚጀምር ሳምንት
  • መጋቢት 15 የሚጀምር ሳምንት
  • መጋቢት 22 የሚጀምር ሳምንት
  • መጋቢት 29 የሚጀምር ሳምንት
  • ሚያዝያ 5 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
km 3/04 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

መጋቢት 8 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 16 (37)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ለሚቀጥለው ሳምንት የአገልግሎት ስብሰባ ሁሉም “መልካሚቱን ምድር ተመልከቱ” የተባለውን አዲስ ብሮሹር ይዘው እንዲመጡ አሳስባቸው። በገጽ 4 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የጥር 1 መጠበቂያ ግንብ እና የጥር 2004 ንቁ! መጽሔቶችን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።

12 ደቂቃ:- “አዲስ የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም።” በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። የወረዳ ስብሰባ የምታደርጉበትን ቀን ተናገር። ጉባኤያችሁ የወረዳ ስብሰባ የሚያደርገው በመጪዎቹ ጥቂት ወራት ውስጥ ከሆነ በስብሰባው ላይ መጠመቅ የሚፈልጉ አስፋፊዎች ለሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ማሳወቅ እንዳለባቸው ተናገር። ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎቻቸውን ወደ ስብሰባው ለመጋበዝና ስብሰባው ተጀምሮ እስኪያበቃ በዚያ ለመገኘት ጥረት እንዲያደርጉ አበረታታ።

23 ደቂቃ:- “‘እናንተ ቅዱሳኑ ሁሉ፣ ይሖዋን ውደዱት።’” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በአንቀጽ 3 ላይ ስትወያዩ አድማጮች ሰዎችን ወደ መታሰቢያው በዓል እንዴት እንደጋበዙ ሐሳብ እንዲሰጡ ጠይቅ።

መዝሙር 34 (77) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

መጋቢት 15 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 35 (79)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። “የመታሰቢያውን በዓል የሚመለከቱ ማሳሰቢያዎች” ከሚለው ርዕስ ዋና ዋና ሐሳቦችን ተናገር። የመታሰቢያው በዓል በሚከበርበት ሳምንት የመጠበቂያ ግንብ ጥናት መቼ እንደሚደረግ ተናገር።

15 ደቂቃ:- በመታሰቢያው በዓል ሰሞን ለማድረግ ስለታቀደው ልዩ የአገልግሎት እንቅስቃሴ ተናገር። የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት ያቀርበዋል። የተደረጉትን ልዩ ዝግጅቶች ግለጽ። ከዚህ በፊት የተገኙ አበረታች የሆኑ ጥቂት ተሞክሮዎች ተናገር። ሁኔታቸው የሚፈቅድላቸው ሁሉ በሚያዝያና በግንቦት ረዳት አቅኚ እንዲሆኑ አበረታታ። ከየካቲት የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ አንዳንድ ነጥቦችን በአጭሩ ከልስ።

20 ደቂቃ:- “መልካሚቱን ምድር ተመልከቱ” ከተባለው ብሮሹር ተጠቀሙ። አዲሱ ብሮሹር የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባችንና ጥናታችን ይበልጥ ትርጉም ያለው እንዲሆን ሊረዳን ይችላል። በዚህ ረገድ በማውጫው መጠቀም ወሳኝ ነገር ነው። ይሖዋ ከባሶራ እንደሚመጣ የሚገልጸውን ኢሳይያስ 63:​1ን አንብብ። የብሮሹሩን ማውጫ በመመልከት ባሶራ (Bozrah) የሚለውን ቃል ፈልገው እንዲያገኙ ጠይቃቸው። ገጽ 34 ላይ የሚገኘውን ሣጥን ተጠቅመህ “Bozrah 11 G11” ምን ማለት እንደሆነ አብራራ፣ ከዚያም በተጠቀሰው ካርታ ላይ ባሶራና ኤዶም የሚገኙበትን ቦታ አመልክት። ማውጫውን ተጠቅመህ ኢየሱስ ከኢየሩሳሌም ወደ ሲካር የተጓዘበትን መንገድ ፈልግ። (ዮሐ. 4:​3-5) በተመሳሳይ መንገድ በቤተ ሳይዳ ያለው የውኃ ገንዳ የሚገኝበትን ቦታ ፈልግ። (ዮሐ. 5:​1-3) ከቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ላይ አንድ ወይም ሁለት ተጨማሪ ምሳሌዎችን ጥቀስ። እነዚህ ቦታዎች ብሮሹሩ ላይ የሚገኙበትን ቦታ እንዲሁም ካርታዎቹን ማየታችን እንዴት እንደሚጠቅመን አድማጮች እንዲናገሩ ጋብዝ። የሚሸፍኑትን የጊዜ ርዝመት ጠቅሰህ በብሮሹሩ ላይ የሠፈሩትን አንዳንድ ካርታዎች በአጭሩ ግለጽ። በገጽ 18-19 ላይ ያለው ካርታ ከሌሎቹ ሁሉ የበለጠ የመጽሐፍ ቅዱስ ቦታዎችን ይዟል። ወንድሞችና እህቶች “መልካሚቱን ምድር ተመልከቱ” በተባለው ብሮሹር በሚገባ እንዲጠቀሙ አበረታታቸው።

መዝሙር 30 (63) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

መጋቢት 22 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 85 (191)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር​—⁠2004 እና የ2004 ቀን መቁጠሪያ ላይ የወጣውን ከመጋቢት 30 እስከ ሚያዝያ 4 ባለው ጊዜ ውስጥ የሚሸፈነውን የመታሰቢያውን በዓል የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ በፕሮግራሙ መሠረት እንዲያነቡ ሁሉንም አስታውሳቸው።

15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

20 ደቂቃ:- “አንተም የተሰለፍክበት የፈረሰኛ ሰራዊት።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።

መዝሙር 81 (181) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

መጋቢት 29 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 52 (129)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የመጋቢት ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በሚያዝያ የሚበረከተውን ጽሑፍ ተናገር። በገጽ 4 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የጥር 15 መጠበቂያ ግንብ እና የጥር 22 ንቁ! (እንግሊዝኛ) መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።

25 ደቂቃ:- ከዓመት መጽሐፍ የተሟላ ጥቅም ማግኘት። በንግግርና ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። በየካቲት 2004 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የወጣው “ከአስተዳደር አካል የተላከ ደብዳቤ” የያዛቸውን ዋና ዋና ነጥቦች ጥቀስ። እንዲሁም በዓመት መጽሐፉ ውስጥ ከሚገኘው የዓለም አቀፉ ሪፖርት ላይ ጎላ ያሉትን አኃዞችና እምነት የሚያጠናክሩ ጥቂት ተሞክሮዎችን ተናገር። በዓመቱ ውስጥ መጽሐፉን አንብበው እንዲጨርሱ አበረታታ።

10 ደቂቃ:- እውነት በቤተሰብ መካከል ያለውን አንድነት ያጠናክራል። በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ለእውነት ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች አንዳንድ ጊዜ የቤተሰብ አባሎቻቸው የሚሰነዝሩባቸውን ተቃውሞ በመፍራት ይሖዋን ከማገልገል ወደኋላ ይላሉ። ቀጥሎ ከቀረቡት ተሞክሮዎች መካከል አንዳንዶቹን እንዲናገሩ ጋብዝ:- የጥር 1, 2002 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 14-15፤ የታኅሣሥ 1, 2000 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 8፤ የመስከረም 1, 1999 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 32፤ የጥር 1, 1999 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 4 እና የየካቲት 22, 1998 ንቁ! (እንግሊዝኛ) ገጽ 31። የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች ተግባራዊ የሚያደርገው አንድ የቤተሰብ አባል ብቻ ቢሆንም አብዛኛውን ጊዜ የቤተሰቡ ሕይወት እንደሚሻሻል ግለጽ።

መዝሙር 53 (130) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሚያዝያ 5 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 8 (21)

5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

20 ደቂቃ:- አካላዊ ንጽሕና ያስመሰግነናል። በሰኔ 1, 2002 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 19-21 ላይ የተመሠረተ ንግግር። በተጨማሪም አምላክ ከእኛ የሚፈልገው በተባለው ብሮሹር ትምህርት 9 አንቀጽ 5ን በመጠቀም መኖሪያ ቤቱንና ግቢውን በንጽሕና የመያዝን አስፈላጊነት ለመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪው እንዴት በዘዴ መንገር እንደሚችል አንድ ሽማግሌ ለአንድ አቅኚ ሲያስረዳው የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ።

12 ደቂቃ:- ትራክቶች በመጠቀም ውይይት መክፈት። ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። ከምሥክርነቱ ሥራ ከባዱ ክፍል ውይይት መክፈት መቻል ነው። ከበር ወደ በር፣ በንግድ አካባቢዎችና በሕዝብ ማዘውተሪያ ቦታዎች ስናገለግል ውይይት ለመክፈት በትራክት መጠቀም እንችላለን። በክልላችሁ ውስጥ የሰዎችን ትኩረት ሊስቡ የሚችሉ ሁለት ወይም ሦስት ትራክቶችን በአጭሩ ከልስ። እነዚህን ትራክቶች ለማበርከት ምን መግቢያ መጠቀም እንችላለን? በሥዕሎቹ እንዴት መጠቀም እንችላለን? የሰዎቹን ስሜት ሳንጎዳ ምን ዓይነት ጥያቄዎች ማንሳት ይቻላል? ፍላጎት ያለው ሰው ካጋጠማቸው ውይይታቸውን ለመቀጠል የሚያስችላቸው አንድ አንቀጽ ከትራክቶቹ ላይ ጥቀስ። ውይይት ለመክፈት እንዴት በትራክት መጠቀም እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ፤ በአንድ አንቀጽ ላይ አጠር ያለ ውይይት ካደረጉ በኋላ እውቀት መጽሐፍ ይበረከታል።

8 ደቂቃ:- ከመታሰቢያው በዓልና በመጋቢት ወር ከነበረው ልዩ የአገልግሎት እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ የተገኙ ተሞክሮዎችን ተናገር።

መዝሙር 7 (19) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ