ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ሚያዝያ እና ግንቦት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። በመታሰቢያው በዓል ወይም በሌሎች ስብሰባዎች ላይ ቢገኙም ወደ ጉባኤ ስብሰባዎች አዘውትረው ለማይመጡ ሰዎችና ፍላጎት ላሳዩ ሌሎች ሰዎች ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርጉ የአምልኮ አንድነት የተባለውን መጽሐፍ ለማበርከት ጥረት አድርጉ። በተለይ የምናነጋግራቸው ሰዎች እውቀት መጽሐፍንና አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር አጥንተው ከነበረ በዚህ መጽሐፍ ተጠቅሞ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ልዩ ጥረት መደረግ ይኖርበታል። ሰኔ:- አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለው ብሮሹር። ብሮሹሩን ስታበረክቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። ሐምሌ እና ነሐሴ:- ብሮሹሮች።
◼ በዚህ ዓመት ለሚደረገው የአውራጃ ስብሰባ የሚሆኑ ደረት ላይ የሚለጠፉ ካርዶች ከጽሑፎች ጋር ይላኩላችኋል። ጉባኤው ተጨማሪ ካርድ ካስፈለገው በጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S-14-AM) ማዘዝ ይኖርበታል። የካርድ መያዣ ፕላስቲክ ማግኘት የሚፈልግ ሰው ካለ ትእዛዙ መላክ ይኖርበታል።
◼ ቅርንጫፍ ቢሮው የሰብሳቢ የበላይ ተመልካቾችንና የጸሐፊዎችን ወቅታዊ አድራሻና ስልክ ቁጥር ማግኘት ይፈልጋል። የአድራሻ ለውጥ በሚኖርበት ጊዜ የጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ የሰብሳቢ የበላይ ተመልካች/የጸሐፊ የአድራሻ ለውጥ ማሳወቂያ ቅጽ (S-29) ሞልቶና ፈርሞ በፍጥነት ለቅርንጫፍ ቢሮው መላክ አለበት። የስልክ ቁጥር ለውጥ ሲኖርም እንደዚህ መደረግ አለበት።
◼ የጉባኤ ጸሐፊዎች የዘወትር አቅኚነት አገልግሎት ማመልከቻ ቅጽ (S-205-AM) እና የረዳት አቅኚነት አገልግሎት ማመልከቻ ቅጽ (S-205b-AM) በበቂ መጠን ሊኖራቸው ይገባል። እነዚህ ቅጾች እንዲላኩላችሁ በጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S-14-AM) መጠየቅ ይቻላል። ቢያንስ ለአንድ ዓመት የሚበቃ ቅጽ ይኑራችሁ። የዘወትር አቅኚነት ማመልከቻ ቅጾች አመልካቹ የተጠመቀበትን ቀን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ መሞላታቸውን ለማረጋገጥ በደንብ ተመልከቷቸው።
◼ አዲስ የደረሱን ጽሑፎች:- አረብኛ፦ የተለያዩ የቪዲዮ ካሴቶች፣ እንግሊዝኛ፦ ወደ ይሖዋ ቅረብ (በትላልቅ ፊደላት የተዘጋጀ)፣ ለርን ፍሮም ዘ ግሬት ቲቸር (በካሴት)።
◼ እንደገና የደረሱን ጽሑፎች:- አማርኛ፦ ማመራመር፣ ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ፣ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ ሥላሴ፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? እንግሊዝኛ፦ የውዳሴ መዝሙሮች (113 ካሴቶች የያዘ አልበም)፣ ጠለቅ ብሎ ማስተዋል፣ ማመራመር።
[በገጽ 2 ላይ የሚገኝ የሥዕል መግለጫ]
ማስታወቂያዎች
(ከገጽ 3 የቀጠለ)