ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ሚያዝያ 26, 2004 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ በቃል መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከመጋቢት 1 እስከ ሚያዝያ 26, 2004 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል። [ማሳሰቢያ:- ከጥያቄው ቀጥሎ መልሱ የሚገኝበት ጽሑፍ ካልተጠቀሰ መልሱን ለማግኘት በግልህ ምርምር ማድረግ ይኖርብሃል።—የአገልግሎት ትምህርት ቤት ገጽ 36-7ን ተመልከት።]
የንግግር ባሕርይ
1. ንግግር ስናቀርብ ሐሳቡን አንድ በአንድ ጽፈን ከማንበብ ይልቅ አስተዋጽኦ መጠቀማችን የተሻለ የሚሆነው ለምንድን ነው? [be ገጽ 166 አን. 3]
2. ለአገልግሎት ዝግጅት በምናደርግበት ጊዜ መናገር የምንፈልገው ሐሳብ በአእምሯችን ቁልጭ ብሎ እንዲታየን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? [be ገጽ 167 አን. 2]
3. የሐዋርያት ሥራ 13:16-41ን እና 17:2, 3 ተጠቅመህ ጳውሎስ “ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ መሆኑን ማስረጃ እያቀረበ” ያስረዳው እንዴት እንደሆነ ግለጽ። (ሥራ 9:22) [be ገጽ 170 አን. 2]
4. በራስ አባባል መናገር ከሚያስገኛቸው ጥቅሞች መካከል አንዳንዶቹ ምንድን ናቸው? [be ገጽ 175 አን. 2-5]
5. በራስ አባባል በመናገር ረገድ ልንጠነቀቅባቸው የሚገቡ ጉዳዮች የትኞቹ ናቸው? እነዚህን አደጋዎች ለማስወገድ ምን ሊረዳን ይችላል? [be ገጽ 175 አን. 6 እስከ ገጽ 176 አን. 3]
ክፍል ቁ. 1
6. በዘፍጥረት 32:24-32 ላይ በሚገኘው ዘገባ መሠረት የ97 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ የነበረው ያዕቆብ የይሖዋን በረከት ለማግኘት ምን አድርጓል? ከዚህስ ምን ትምህርት እናገኛለን? [w 02 8/1 ገጽ 29-31]
7. “የማመዛዘን ችሎታ” ምንድን ነው? ሚዛናችንን እንዳንስትና በክርስቲያን ወንድሞቻችን እንዳንጎዳ የሚጠብቀን እንዴት ነው? (ምሳሌ 1:4 NW ) [w02 8/15 ገጽ 21-2]
8. ንግግር አቅራቢዎች ንግግራቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ማድረግ የሚችሉት እንዴት ነው? [be ገጽ 52 አን. 6 እስከ ገጽ 53 አን. 5]
9. አንድ ተናጋሪ መሠረታዊ ነጥቦችን ብቻ የያዘውን አስተዋጽኦ በማዳበር ጥቅሶችን በጥልቀት የሚያብራራ ሕያው ንግግር አድርጎ ለማቅረብ ምን ውሳኔዎችን ማድረግ ይኖርበታል? [be ገጽ 54 አን. 2-4]
10. ይሖዋ እስራኤላውያንን በምድረ በዳ ከሳምንት እስከ ሳምንት ከወር እስከ ወር መና የመገባቸው ለምን ነበር? ከዚህስ ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን? (ዘዳ. 8:16) [w 02 9/1 ገጽ 30 አን. 3-4]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. በዘፍጥረት 37:12-17 ላይ በተጠቀሰው ታሪክ መሠረት በዮሴፍና በኢየሱስ መካከል ምን ተመሳሳይነት እናገኛለን? [w 87 5/1 ገጽ 12 አን. 12]
12. በዘፍጥረት 42:25-35 ላይ ዮሴፍ ከኢየሱስ ጋር የሚመሳሰል ርኅራኄ ያሳየው እንዴት ነው? [w87 5/1 ገጽ 18 አን. 10፤ ገጽ 19 አን. 17]
13. በዘመናችን የባሪያው ክፍል መንፈሳዊ ምግብ የሚያቀርብበት መንገድ በዮሴፍ ጊዜ እህል ይከፋፈል ከነበረበት መንገድ ጋር የሚመሳሰለው እንዴት ነው? (ዘፍ. 47:21-25)
14. ይሖዋ “መሆን የምፈልገውን እሆናለሁ” ሲል ስለ ስሙ ምን እየተናገረ ነበር? (ዘፀ. 3:14, 15 NW )
15. በዘፀአት 16:2, 3 ላይ ማጉረምረም የሚያስከትላቸው ምን ሁለት አደጋዎች ተጠቅሰዋል? [w 93 3/15 ገጽ 21]