ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ሰኔ 28, 2004 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ በቃል መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከግንቦት 3 እስከ ሰኔ 28, 2004 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል። [ማሳሰቢያ:- ከጥያቄው ቀጥሎ መልሱ የሚገኝበት ጽሑፍ ካልተጠቀሰ መልሱን ለማግኘት በግልህ ምርምር ማድረግ ይኖርብሃል።—የአገልግሎት ትምህርት ቤት ገጽ 36-7ን ተመልከት።]
የንግግር ባሕርይ
1. ከመድረክ ስንናገር ከአንድ ሰው ጋር እንደምናወራ ሆነን እንዳንናገር ወይም አነጋገራችን ድርቅ ያለ እንዲሆን ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች ምንድን ናቸው? [be ገጽ 179 አን. 4]
2. የድምፃችንን ጥራት ማሻሻል አተነፋፈስን ከመቆጣጠር እንዲሁም የተወጠሩ ጡንቻዎችን ዘና ከማድረግ ጋር ብቻ የተያያዘ ያልሆነው ለምንድን ነው? [be ገጽ 181 አን. 2]
3. የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ለሌሎች በምናካፍልበት ጊዜ “ከሁሉ ጋር በሁሉ ነገር እንደ እነርሱ” ለመሆን ምን ተግባራዊ እርምጃዎችን መውሰድ እንችላለን? (1 ቆሮ. 9:20-23 የ1954 ትርጉም ) [be ገጽ 186 አን. 2-4]
4. በአገልግሎት ላይ የምናነጋግራቸውን ሰዎች በጥሞና ማዳመጥ ምን ነገሮችን ይጨምራል? [be ገጽ 187]
5. በአገልግሎት ላይ ለምናገኛቸው ሰዎች ሁሉ አክብሮት ማሳየታችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? [be ገጽ 190]
ክፍል ቁ. 1
6. ቲኦክራሲያዊ ትምህርቶችን ለሌሎች የሚያስተምሩ ሁሉ ግባቸው ምንድን ነው? እዚህ ግብ ላይ እንድንደርስ ምን ሊረዳን ይችላል? (ማቴ. 5:16፤ ዮሐ. 7:16-18) [be ገጽ 56 አን. 3 እስከ ገጽ 57 አን. 2]
7. በምናስተምርበት ጊዜ ነገሮችን እያነጻጸርን ማቅረባችን ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው? ኢየሱስ ይህን የማስተማሪያ ዘዴ የተጠቀመው እንዴት ነበር? [be ገጽ 57 አን. 3፤ ገጽ 58 አን. 2]
8. ከፈሪሳውያን በተቃራኒ ኢየሱስ የሚያስተምረው ትምህርት የሰዎችን ልብ መንካት የቻለው እንዴት ነበር? [be ገጽ 59 አን. 2-3]
9. የምናስተምራቸውን ሰዎች ውሳኔ ሳናደርግላቸው የተማሩትን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ልንረዳቸው የምንችለው እንዴት ነው? [be ገጽ 60 አን. 1-3]
10. ሌሎች በግል ውሳኔ ሊያደርጉባቸው የሚገቡ ጥያቄዎችን ቢጠይቁን መልስ መስጠት የሚኖርብን እንዴት ነው? [be ገጽ 69 አን. 4-5]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. ሙሴ “ማደሪያ ድንኳኑንና በውስጡ ያለውን ዕቃ ሁሉ” ለመሥራት ይሖዋ ያሳየውን ዕቅድ በጥብቅ መከተል የነበረበት ለምንድን ነው? (ዘፀ. 25:9) [w 03 2/15 ገጽ 29]
12. ብዙውን ጊዜ የሚቃጠል መሥዋዕት ከመቅረቡ በፊት የኃጢአት መሥዋዕት ወይም የበደል መሥዋዕት የሚቀርብ መሆኑ ምን ያመለክታል? (ዘሌ. 8:14, 18፤ 9:2, 3) [w00 8/15 ገጽ 16 አን. 16፤ ገጽ 19 አን. 8]
13. እስራኤላውያን ይሖዋ በዘፀአት 34:23, 24 ላይ የሰጣቸውን መመሪያ በመታዘዝ ካሳዩት እምነት ምን ትምህርት እናገኛለን?
14. የኅብረት መሥዋዕት የሚቀርብበት ዓላማ ምን ነበር? (ዘሌ. 3:1)
15. በዛሬው ጊዜ ቅዱስ አገልግሎት የምናቀርብበትን መንገድ በተመለከተ ከዘፀአት 30:9 ምን ትምህርት እናገኛለን? [w00 11/15 ገጽ 14 አን. 16]