የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 9/04 ገጽ 7
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
km 9/04 ገጽ 7

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች መስከረም፦ ጉባኤው ያሉትን እንደ መንግሥትህ ትምጣ እና የአምልኮ አንድነት ያሉ የቆዩ መጽሐፎች። ጥቅምት፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ኅዳር፦ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለው ብሮሹር። ታኅሣሥ፦ ታላቁ ሰው። መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው ወይም ለዘላለም መኖር የተባሉትን መጽሐፍት በአማራጭነት ማበርከት ይቻላል።

◼ በታኅሣሥ ወር ደም አልወስድም—የሕክምናው መስክ መፍትሔ አስገኝቷል የተሰኘውን የቪዲዮ ፊልም እንከልሳለን። ይህ ፊልም በደም ምትክ የሚሰጡ ሕክምናዎች —⁠ተከታታይ ጥናታዊ ፊልሞች በሚል ርዕስ በተዘጋጀው የዲቪዲ ፊልም ውስጥ ተካትቷል። በዚህ ዲቪዲ ውስጥ በደም ምትክ የሚሠራባቸው የሕክምና ዘዴዎች​—⁠ቀላል፣ አስተማማኝና ውጤታማ፤ በደም ምትክ የሚሰጥ ሕክምና​—⁠የሕሙማንን መብትና ፍላጎት ማክበር እንዲሁም ደም አልወስድም​—⁠የሕክምናው መስክ መፍትሔ አስገኝቷል የተባሉት ፊልሞች ይገኛሉ። በእንግሊዝኛ፣ በፈረንሳይኛና በሌሎች ቋንቋዎች ይህን ዲቪዲ ማግኘት ይቻላል።

◼ በ2005 በሚከበረው የመታሰቢያው በዓል ሰሞን የሚሰጠው ልዩ የሕዝብ ንግግር እሁድ ሚያዝያ 10 ይቀርባል። የንግግሩ ርዕስ ወደፊት ይገለጻል። በዚያ ሳምንት የወረዳ የበላይ ተመልካች ጉብኝት ወይም የወረዳ አሊያም የልዩ ስብሰባ በሚኖራቸው ጉባኤዎች ልዩ የሕዝብ ንግግሩ በቀጣዩ ሳምንት መቅረብ ይችላል። በየትኛውም ጉባኤ ልዩ የሕዝብ ንግግሩ ከሚያዝያ 10, 2005 በፊት መቅረብ አይኖርበትም።

◼ ሽማግሌዎች የመመለስ ዝንባሌ ያላቸውን የተወገዱ ወይም ራሳቸውን ያገለሉ ግለሰቦችን በተመለከተ በሚያዝያ 15, 1991 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 21-3 ላይ የተሰጡትን መመሪያዎች እንዲሠሩባቸው ልናስታውሳቸው እንወዳለን።

◼ ጉባኤዎች መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች እንደደረሷቸው ወዲያውኑ ለወንድሞች ማከፋፈል አለባቸው። እንዲህ ማድረጉ አስፋፊዎች መጽሔቶቹን በመስክ አገልግሎት ላይ ከማበርከታቸው በፊት እንዲያነቧቸው ያስችላቸዋል።

◼ የጥቅምት ወር አምስት ቅዳሜና እሁዶች ስለሚኖሩት ረዳት አቅኚ ሆኖ ለማገልገል አመቺ ነው።

◼ አዲስ የደረሱን ጽሑፎች:- አማርኛ፦ ወደ ይሖዋ ቅረብ፤ አረብኛ፦ የ2004 የዓመት መጽሐፍ፤ ቻይንኛ፦ እውቀት፣ አንዳንድ ብሮሹሮች፤ እንግሊዝኛ፦ ንቁ! የ2003 ጥራዝ፤ በሲዲ የተዘጋጀ የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ጽሑፎች ቤተ መጻሕፍት 2003፤ ኑዌር፦ እውቀት፤ ትግርኛ፦ ወጣቶች—በሕይወታችሁ ምን ለማድረግ አስባችኋል?

◼ በድጋሚ የደረሱን ጽሑፎች:- አማርኛ፦ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው፤ አረብኛ፦ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች፤ እንግሊዝኛ፦ ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ፤ ፈረንሳይኛ፦ ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ