ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ኅዳር፦ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለው ብሮሹር። ታኅሣሥ፦ ታላቁ ሰው። በአማራጭነት መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው ወይም ለዘላለም መኖር የተባሉትን መጻሕፍት ማበርከት ይቻላል።
◼ ታኅሣሥ 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ አሊያም እርሱ የወከለው ሌላ ወንድም የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። ለእድሳት ወይም ለግንባታ ተብሎ ለብቻ የሚቀመጥ የባንክ ሒሳብ ካለ ይህንንም ለመመርመር ዝግጅት መደረግ አለበት። የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከቀረበ በኋላ የሒሳብ ምርመራው ውጤት ለጉባኤው መነበብ አለበት።
◼ ጉባኤዎች በታኅሣሥ ወር ከሚልኩት የጽሑፍ ትእዛዝ ጋር የ2004 የመጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! ጥራዞችን ማዘዝ መጀመር ይኖርባቸዋል። ጥራዞቹ ደርሰውን እስክንልክላችሁ ድረስ በጉባኤያችሁ የተላኩ ጽሑፎች ማሳወቂያ ላይ “Pending” (በቅርቡ የሚላኩ) ይባላሉ። እነዚህ ጥራዞች በልዩ ትእዛዝ የሚገኙ ጽሑፎች ናቸው።
◼ ቅርንጫፍ ቢሮው የሁሉንም ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቾችና ጸሐፊዎች ወቅታዊ አድራሻና ስልክ ቁጥር ማግኘት ይፈልጋል። የአድራሻ ለውጥ በሚኖርበት ጊዜ የጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ የሰብሳቢ የበላይ ተመልካች/የጸሐፊ የአድራሻ ለውጥ ማሳወቂያ ቅጽ (S-29) ሞልቶና ፈርሞ በፍጥነት ለቅርንጫፍ ቢሮው መላክ አለበት። የስልክ ቁጥር ለውጥ ሲኖርም እንደዚህ መደረግ አለበት።
◼ አዲስ የደረሱን ጽሑፎች:- እንግሊዝኛ፦ የመጠበቂያ ግንብ ጽሑፎች ማውጫ 2003፤ ኦሮምኛ፦ T-26፤ ስፓንኛ፦ ወደ ይሖዋ ቅረብ፤ ትግርኛ፦ የአምላክ ወዳጅ።
◼ እንደገና የደረሱን ጽሑፎች:- አረብኛ፦ በደስታ ኑር፣ ሮድ ቱ ፓራዳይዝ (ትራክት)፤ እንግሊዝኛ፦ የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም bi-12, T-13, T-15, T-23 እና T-24፤ ፈረንሳይኛ፦ የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም bi-12፤ ትግርኛ፦ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው።