የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ኅዳር 8 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 80 (180)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች፤ እንዲሁም ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ ከአገልግሎት ስብሰባው የተሟላ ጥቅም አግኙ። አገልግሎታችን በተባለው መጽሐፍ ገጽ 71-72 ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት። የአገልግሎት ስብሰባ በየትኞቹ አምስት መንገዶች ክርስቲያናዊ አገልግሎታችንን እንድናሻሽል ይረዳናል? በዚህ ወር ከወጣው የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም ላይ ምሳሌዎች ጥቀስ። አስቀድሞ መዘጋጀት ምን ጥቅሞች አሉት? በዚህ ስብሰባ ላይ አዘውትረን መገኘት ያለብን ለምንድን ነው? እንደዚህ ያለ ስብሰባ ጥንትም ይደረግ እንደነበረ የሚጠቁም ምን ቅዱስ ጽሑፋዊ ምሳሌ አለ?
20 ደቂቃ፦ “የጥድፊያ ስሜታችሁን አታጥፉ!” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በጥር 15, 2000 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 12-13 ላይ የወጣውን ሐሳብ ጨምረህ አቅርብ።
መዝሙር 7 (19) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ኅዳር 15 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 21 (46)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 6 ላይ የቀረቡት የመግቢያ ሐሳቦች ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ ከሆኑ በእነዚህ መግቢያዎች በመጠቀም የመስከረም 1 መጠበቂያ ግንብ እና የመስከረም 2004 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ሌሎች መግቢያዎችንም መጠቀም ይቻላል።
15 ደቂቃ፦ በመስጠት የሚገኘውን ደስታ ቀምሰህ ታውቃለህ? በኅዳር 1, 2004 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 19-23 ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር።
20 ደቂቃ፦ “የአውራጃ ስብሰባው ከአምላክ ጋር እንድንሄድ አበረታቶናል።” በሽማግሌ የሚቀርብ። በአንድ ደቂቃ ወይም ከዚያ ባነሰ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ካቀረብህ በኋላ በርዕሱ ውስጥ ከቀረቡት ጥያቄዎች ከ1-6 ያሉትን በመጠቀም የስብሰባውን የመጀመሪያ ቀን ፕሮግራም ከአድማጮች ጋር ተወያዩበት። በእያንዳንዱ ጥያቄ ላይ በደንብ ለመወያየት እንዲቻል የተመደበልህን ጊዜ ከፋፍለው። ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ የተገለጹ ጥቅሶች የቀረቡት መልሱን ለማግኘት እንዲቀል ተብሎ ነው። በተመደበልህ ጊዜ ውስጥ ሁሉንም ጥቅሶች ማንበብ አትችል ይሆናል። አድማጮች የሚሰጧቸው መልሶች የተማሯቸውን ነገሮች ተግባራዊ ማድረጋቸው በሚያስገኛቸው ጥቅሞች ላይ ያተኮሩ ሊሆኑ ይገባል።
መዝሙር 65 (152) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ኅዳር 22 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 69 (160)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
15 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
20 ደቂቃ፦ “የአውራጃ ስብሰባው ከአምላክ ጋር እንድንሄድ አበረታቶናል።” በሽማግሌ የሚቀርብ። ለመጀመሪያዎቹ ስድስት ጥያቄዎች የተሰጠውን መመሪያ በመከተል ከ7-14 ባሉት ጥያቄዎች ተጠቅመህ በአውራጃ ስብሰባው የሁለተኛ ቀን ፕሮግራም ላይ ከአድማጮች ጋር ተወያዩ።
መዝሙር 28 (58) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ኅዳር 29 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 85 (191)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የኅዳር ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። የመስከረም 15 መጠበቂያ ግንብን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ የጥያቄ ሣጥን። በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።
25 ደቂቃ፦ “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን እድገት እንዲያደርጉ መርዳት—ክፍል 3።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ለአንቀጹ በቀረቡት ጥያቄዎች ተጠቀም። በአንቀጽ 3 ላይ ከተወያያችሁ በኋላ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው በተባለው ብሮሹር ትምህርት 5 አንቀጽ 1ን በመጠቀም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሲመራ የሚያሳይ አጠር ያለ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ሠርቶ ማሳያው የሚጀምረው ቀደም ብለው አንቀጹን እንዳነበቡና በጥያቄው ላይ እንደተወያዩ በማሰብ ነው። ጥናቱን የሚመራው ወንድምና ተማሪው ኢሳይያስ 45:18ንና መክብብ 1:4ን ያነብቡና ይወያዩበታል። አስጠኚው ቀላል ጥያቄዎችን በመጠየቅ ጥቅሶቹ ከሚወያዩበት ሐሳብ ጋር ያላቸውን ተዛምዶ ተማሪው እንዲያብራራ ያበረታታዋል።
መዝሙር 29 (62) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 6 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 23 (48)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በታኅሣሥ ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ተናገር። ታላቁ ሰው የተባለውን መጽሐፍ ለማበርከት የሚያስችሉ አንድ ወይም ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
20 ደቂቃ፦ “ሌሎችን ለመርዳት ዝግጁ ናችሁ?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ላገኙት ድጋፍ ወይም ማበረታቻ አመስጋኝ ለሆኑ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች ቃለ መጠይቅ አድርግ።
15 ደቂቃ፦ “የአውራጃ ስብሰባው ከአምላክ ጋር እንድንሄድ አበረታቶናል።” በሽማግሌ የሚቀርብ። ለመጀመሪያዎቹ ስድስት አንቀጾች የተሰጠውን መመሪያ በመከተል ከ15-18 ባሉት ጥያቄዎች ተጠቅመህ በአውራጃ ስብሰባው የሦስተኛ ቀን ፕሮግራም ላይ ከአድማጮች ጋር ተወያዩ።
መዝሙር 95 (213) እና የመደምደሚያ ጸሎት።