የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 12/04 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ታኅሣሥ 13 የሚጀምር ሳምንት
  • ታኅሣሥ 20 የሚጀምር ሳምንት
  • ታኅሣሥ 27 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥር 3 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
km 12/04 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ታኅሣሥ 13 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 22 (47)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ሁሉም በሚቀጥለው ወር በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለሚካሄደው ውይይት ደም አልወስድም—የሕክምናው መስክ መፍትሔ አስገኝቷል የተባለውን የቪዲዮ ፊልም ተመልክተው እንዲመጡ አበረታታ። በወሩ ውስጥ ባሉት የበዓል ቀናት ሊካሄድ የታቀደውን የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ ተናገር። በገጽ 6 ላይ የቀረቡት የመግቢያ ሐሳቦች ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ ከሆኑ በእነዚህ መግቢያዎች በመጠቀም የጥቅምት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የጥቅምት 2004 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ሌሎች መግቢያዎችንም መጠቀም ይቻላል። ሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ውይይት ለማስቆም “የእናንተን ሃይማኖት በሚገባ አውቀዋለሁ” ለሚል ሰው በተለያየ መንገድ እንዴት መልስ መስጠት እንደሚቻል የሚያሳዩ ይሁኑ።—ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 20ን ተመልከት።

15 ደቂቃ:- “የበኩልህን እርዳታ ማበርከት ትችላለህ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ከአንድ የጉባኤ ሽማግሌ ጋር አጭር ቃለ ምልልስ አድርግ። ጉባኤውን የማገልገል ግብ እንዲኖረውና ብቃቱን ለማሟላት እንዲችል የረዳው ምን እንደሆነ እንዲናገር ጋብዘው።

20 ደቂቃ:- “ለዘመዶቻችን ምሥራቹን እንዴት መንገር እንችላለን?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ለአንቀጾቹ የቀረቡትን ጥያቄዎች ተጠቀም። አድማጮች ዘመዶቻቸው ምሥራቹን የመስማት ፍላጎት እንዲያድርባቸው በማድረግ ምሥክርነት መስጠት የቻሉት እንዴት እንደሆነ በአጭሩ እንዲናገሩ ጋብዝ።

መዝሙር 27 (57) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ታኅሣሥ 20 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 65 (152)

5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከደም እንድንርቅ ለመርዳት ታስቦ የተደረገውን አዲስ ዝግጅት አስመልክቶ በሚቀጥለው ሳምንት በሚቀርበው ክፍል ላይ ሁሉም እንዲገኙ አበረታታ።

15 ደቂቃ:- “ከቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ምን ጥቅም እናገኛለን?” በትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች የሚቀርብ ንግግር። ከጥቅምት 2004 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ። ከትምህርት ቤቱ ያገኙትን ጥቅም የሚናገሩ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎችን አስቀድመህ አዘጋጅ።

25 ደቂቃ:- “አዲሱን ብሮሹር ለማሰራጨት የሚደረግ ልዩ ዘመቻ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ። በርዕሱ ውስጥ ያሉት አቀራረቦች በሠርቶ ማሳያ መልክ እንዲቀርቡ አድርግ። በአንዱ ሠርቶ ማሳያ ላይ አስፋፊው ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ሲያነብለት ብዙም ፍላጎት ላላሳየ አንድ ግለሰብ ትራክት ያበረክትለታል።

መዝሙር 24 (50) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ታኅሣሥ 27 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 71 (163)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። አስፋፊዎች የታኅሣሥ ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በገጽ 6 ላይ የቀረቡት ሐሳቦች ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ ከሆኑ በእነዚህ መግቢያዎች በመጠቀም የጥቅምት 15 መጠበቂያ ግንብን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል አሳይ። ብሮሹሩን ለማሰራጨት የሚደረገው ልዩ ዘመቻ እንደሚጀመር አስታውሳቸው።

25 ደቂቃ:- አምላክ ከደም እንድንርቅ የሰጠንን ትእዛዝ መጠበቅ። ከቅርንጫፍ ቢሮ የተላከውን ጽሑፍ በመጠቀም አንድ ሽማግሌ በንግግር ያቀርበዋል። የሕክምና መመሪያ የተባለው ካርድ የሚሞላው በዚያን ዕለት ምሽት እንዳልሆነ አስቀድመህ ተናገር። ተናጋሪው ወንድም ክፍሉን በንባብ በሚያቀርብበት ወቅት አንዳንድ ቁልፍ ነጥቦችን ጎላ ለማድረግ አጫጭር ሐሳቦችን ማከል የሚችል ቢሆንም ተጨማሪ ምሳሌዎችንና ጥቅሶችን መጥቀስ አያስፈልገውም። ጊዜ በፈቀደ መጠን ምዕራፋቸውና ቁጥራቸው ብቻ የተጠቀሱትን ጥቅሶች ማንበብ ወይም ሐሳባቸውን መናገር ይቻላል። አስፈላጊ ነጥቦችን ለማጉላት “ከደም እንድንርቅ ለመርዳት የተደረገ አዲስ ዝግጅት” ከሚለው ሣጥን አንዳንድ ዓረፍተ ነገሮችን አንብብ። ክፍሉ በሚቀርብበት ወቅት የራሳቸውን ቅጂ ይዘው መከታተል እንዲችሉ የጉባኤው ፀሐፊ የሕክምና መመሪያውን ካርድና “የሕክምና መመሪያ ካርድ አሞላል” የሚለውን ቅጽ ለሁሉም የተጠመቁ አስፋፊዎች አስቀድሞ ማከፋፈል አለበት። እንዲሁም ለይሖዋ ምሥክሮች ልጆች የተዘጋጀው የመታወቂያ ካርድ በጉባኤው ውስጥ በበቂ መጠን መኖሩን ማረጋገጥ አለበት።

10 ደቂቃ:- ሕሊና የሚጫወተው ሚና። አንድ ሽማግሌ በሰኔ 15, 2004 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 23-24 አንቀጽ 16-19 ላይ ተመሥርቶ በንግግር ያቀርበዋል። ለሕሊና በተተዉ ጉዳዮች ላይ የምናደርጋቸው ውሳኔዎች ከይሖዋ ጋር ያለንን ዝምድና ስለሚነኩ አቅልለን ልንመለከታቸው እንደማይገባ አበክረህ ግለጽ።

መዝሙር 4 (8) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥር 3 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 10 (27)

5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በጥር ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ተናገር።

15 ደቂቃ:- “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን እድገት እንዲያደርጉ መርዳት—ክፍል 4።” በአንቀጽ አንድ ላይ ተመሥርተህ ከአንድ ደቂቃ የማይበልጥ መግቢያ ከተናገርክ በኋላ በአንቀጽ 2ና 3 ላይ ያለውን ሐሳብ በመጠቀም አንድ አስፋፊ ተማሪውን ለጥናቱ እንዴት መዘጋጀት እንደሚችል ሲያስረዳው የሚያሳይ የ5 ደቂቃ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ከእውቀት መጽሐፍም ሆነ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ከተባለው ብሮሹር አንድ አንቀጽ መርጦ በሠርቶ ማሳያው ላይ መጠቀም ይቻላል። ከዚያም ከሠርቶ ማሳያው ላይ አንዳንድ ቁልፍ ነጥቦችን እያጎላህ ከ2-5 ድረስ ያሉትን አንቀጾች በጥያቄና መልስ አቅርብ።

25 ደቂቃ:- “ደም አልወስድም—የሕክምናው መስክ መፍትሔ አስገኝቷል ከተባለው ፊልም ተጠቀሙ።” በገጽ 3 ላይ የቀረቡትን ጥያቄዎች በመጠቀም ደም አልወስድም በተባለው የቪዲዮ ፊልም ላይ ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት። ከውይይቱ በኋላ የመጨረሻውን አንቀጽ አንብብ።

መዝሙር 35 (79) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ