የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ጥር 10 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 57 (136)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 6 ላይ የቀረቡት የመግቢያ ሐሳቦች ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ ከሆኑ በእነዚህ መግቢያዎች በመጠቀም የኅዳር 1 መጠበቂያ ግንብ እና የኅዳር 2004 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። እንዲሁም ነቅተህ ጠብቅ! የተባለውን ብሮሹር የይሖዋ ምሥክር ላልሆነ የቅርብ ዘመድ እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ አንድ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
15 ደቂቃ:- “የእምነትን ቃል መመገብ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ የተሰጡትን ጥቅሶች አንብብና ተወያዩባቸው።
20 ደቂቃ:- “ተስማሚ የሆነ መግቢያ ለመጠቀም ሞክር።” በገጽ 4 ላይ በሚገኘው አባሪ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። እነዚህን አቀራረቦች ተጠቅሞ በወሩ ውስጥ የሚሰራጨውን ጽሑፍ እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። በእያንዳንዱ ሠርቶ ማሳያ ላይ አስፋፊው የቤቱ ባለቤት ለሚያሳስበው ጉዳይ መልስ የሚሰጥ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ያነብባል።
መዝሙር 60 (143) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥር 17 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 14 (34)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ:- ነቅተህ ጠብቅ! የተባለውን ብሮሹር ለማሰራጨት በተደረገው ዘመቻ የተገኙ ተሞክሮዎች። በጉባኤው ክልል ውስጥ አዲሱን ብሮሹር ለማበርከት ውጤታማ ሆኖ የተገኘ አንድ አቀራረብ በሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
20 ደቂቃ:- “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን እድገት እንዲያደርጉ መርዳት—ክፍል 5።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን በማስጠናት ተሞክሮ ያካበተ አንድ አስፋፊ በአንቀጽ 4ና 5 ላይ የተጠቀሱትን አንዳንድ ልማዶች እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል ከአንድ አዲስ አስፋፊ ጋር ሲወያይ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 81 (181) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥር 24 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 71 (163)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። “በዲቪዲ የተዘጋጁ የቪዲዮ ፊልሞች” የሚለውን ሣጥን በአጭሩ ከልስ።
10 ደቂቃ:- የጥያቄ ሣጥን። በንግግር የሚቀርብ።
25 ደቂቃ:- አዲሱን ብሮሹር በመጠቀም የሰዎችን ፍላጎት ለማሳደግ ጥረት አድርጉ። የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት ያቀርበዋል። ነቅተህ ጠብቅ! የተባለውን ብሮሹር ያበረከትንላቸውን ሰዎች ፍላጎት ለማሳደግ ተመላልሶ መጠየቅ ልናደርግላቸው ይገባል። በገጽ 2 ላይ የሚገኘውን የርዕስ ማውጫ በመጠቀም የብሮሹሩን ዋና ዋና ሐሳቦች በአጭሩ አቅርብ። በብሮሹሩ ውስጥ በሣጥን መልክ በተቀመጡት አጫጭር ሐሳቦች ላይ ትኩረት አድርግ። (በማውጫው ላይ ደመቅ ተደርገው ከተጻፉት ዋና ዋና ርዕሶች ሥር ተዘርዝረዋል።) በእነዚህ ሐሳቦች በመጠቀም ቀደም ሲል ያደረግነውን ውይይት የሚያጠናክር ትምህርት ሰጪና አጠር ያለ ተመላልሶ መጠየቅ ማድረግ እንችላለን። ለምሳሌ በመጀመሪያው ቀን በገጽ 3ና 4 ላይ ባለው ሐሳብ ተወያይታችሁ ከነበረ ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርግለት በገጽ 5 ላይ “አምላክ በእርግጥ ያስብልናል?” የሚለውን ርዕስ በመጠቀም ማወያየት ይቻላል። ይህን እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚቻል አብራራ። በገጽ 6-8 እንዲሁም 17ና 18 ላይ ያሉትን ወይም ለጉባኤው ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች ሐሳቦችን የያዙትን ሣጥኖች በአጭሩ ከልሱ። ከሣጥኖቹ አንዱን በመጠቀም ተመላልሶ መጠየቅ ሲደረግ የሚያሳይ አንድ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። በሠርቶ ማሳያው ላይ ምዕራፋቸውና ቁጥራቸው ብቻ ከተሰጡት ጥቅሶች ውስጥ አንድ ወይም ሁለቱን ማንበብና ማብራራት ያስፈልጋል። አስፋፊው በሚቀጥለው ጉብኝቱ ወቅት የሚወያዩበትን ሣጥን ለሰውየው በመንገር ሠርቶ ማሳያውን ይደመድማል።
መዝሙር 88 (200) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥር 31 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 68 (157)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የጥር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በገጽ 6 ላይ የቀረበው የመግቢያ ሐሳብ ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ ከሆነ በዚህ መግቢያ በመጠቀም የኅዳር 15 መጠበቂያ ግንብ ሲበረከት የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ሌሎች ተግባራዊ የሆኑ አቀራረቦችንም መጠቀም ይቻላል።
15 ደቂቃ:- እናንት ወጣቶች መንፈሳዊ እድገት እያደረጋችሁ ነውን? አንድ ሽማግሌ በሚያዝያ 1, 2003 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 8-10 ላይ ተመሥርቶ በንግግር ያቀርበዋል። ሊደረስባቸው የሚችሉ አንዳንድ ግቦችን ጥቀስ፤ እንዲሁም ወጣቶች ተጨባጭ የሆኑ ግቦችን ለራሳቸው እንዲያወጡ አበረታታ።
20 ደቂቃ:- ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ ትመረምራለህ? ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር—2005 በተባለው ቡክሌት መቅድም ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ሁላችንም በየቀኑ ጥቂት ደቂቃዎች መድበን የዕለቱን ጥቅስና በዚያ ላይ የተሰጠውን ሐሳብ ማንበብ እንደሚያስፈልገን ተናገር። የዕለቱን ጥቅስ ስለሚያነቡበት ፕሮግራምና እንዲህ ማድረጋቸው ያስገኘላቸውን ጥቅም የሚናገሩ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎችን አስቀድመህ አዘጋጅ። በ2005 የዓመት ጥቅስ ላይ አጠር ያለ ውይይት በማድረግ ደምድም።
መዝሙር 66 (155) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 7 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 49 (114)
5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ:- አዲሶች አምላክንና ባልንጀሮቻቸውን መውደድ እንዲማሩ እርዷቸው። በሐምሌ 1, 2004 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 16 አንቀጽ 7-9 ላይ ተመሥርቶ በንግግር የሚቀርብ። አዲሶች የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እንዲሆኑ በመርዳት ረገድ እያንዳንዱ የጉባኤው አባል ምን ኃላፊነት እንዳለበት ጎላ አድርገህ ተናገር።
25 ደቂቃ:- “የናሙና አቀራረቦችን እንዴት ልንጠቀምባቸው ይገባል?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን እትም አባሪ ገጽ 3 ላይ ወደፊት የምናበረክታቸውን ጽሑፎች ለማስተዋወቅ የሚረዱ አቀራረቦች እንደወጡ ጥቀስ። አባሪውን ዓመቱን ሙሉ ስለምንጠቀምበት በቅርብ ቦታ አስቀምጡት። በርዕሱ ላይ ከተወያያችሁበት በኋላ በየካቲት ወር ወደ ይሖዋ ቅረብ የተባለውን መጽሐፍ እንዴት ማበርከት እንደምንችል ተናገር። ሁለት አቀራረቦች በሠርቶ ማሳያ እንዲቀርቡ አድርግ። ለሠርቶ ማሳያው በገጽ 3 ላይ ያሉትን የናሙና አቀራረቦች ወይም ለጉባኤው ክልል ውጤታማ የሆነ ሌላ አቀራረብ መጠቀም ይቻላል።
መዝሙር 75 (169) እና የመደምደሚያ ጸሎት።