ተስማሚ የሆነ መግቢያ ለመጠቀም ሞክር
ለሰዎች ያለን ከልብ የመነጨ አሳቢነት ምን እንደሚያሳስባቸው አስተውለን የአምላክ መንግሥት ለችግሮቻቸው እንዴት ዘላቂ መፍትሔ እንደሚያመጣላቸው ለማስረዳት ያስችለናል። (ፊልጵ. 2:4) አብዛኞቹ አስፋፊዎች የቤቱ ባለቤት በዚህ ገጽ በስተቀኝ በኩል ባለው አምድ ላይ ተዘርዝረው እንደሚገኙት ያሉ ጽሑፎቻችን ይዘዋቸው በሚወጡት የገነትን ገጽታ የሚያሳዩ ሥዕሎች ላይ ሐሳብ እንዲሰጥ ማድረግ ውጤታማና ተስማሚ መግቢያ ሆኖ አግኝተውታል። ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት መግቢያዎች ውስጥ አንዱን በመጠቀም ይህን ልታደርግ ትችላለህ:-
◼ “እዚህ ሥዕል ላይ እንደሚመለከቱት ባለ አስደሳች ሁኔታ የሚኖር የሰው ዘር ቤተሰብ የምናይበት ጊዜ ይመጣል ብለው አስበው ያውቃሉ?”
◼ “ሁላችንም ልጆቻችን በዚህ ሥዕል ላይ እንደሚታየው ባለ ዓለም ውስጥ ተደስተው እንዲኖሩ እንፈልጋለን። እንደዚህ ያለ ሁኔታ እንዲፈጠር ምን ነገር ያስፈልጋል ብለው ያስባሉ?”
◼ “ይህ ሥዕላዊ መግለጫ አምላክ ፈቃዱ በሰማይ እንደሆነ ሁሉ በምድርም በሚሆንበት ጊዜ ምድር ምን እንደምትመስል ያሳያል። በዚህ ሥዕላዊ መግለጫ ላይ ዛሬ ከምንኖረው ሕይወት የተለየ ያስተዋሉት ነገር ይኖራል?”
◼ “እዚህ ሥዕል ላይ በሚታየው ዓይነት ሁኔታ ሥር መኖር ይፈልጋሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] በእኛ ዕድሜ ውስጥ እንዲህ ያለ ነገር ይከሰታል ብለው አስበው ያውቃሉ?”
የምታነጋግረው ሰው የሚሰጠውን መልስ በጥሞና አዳምጥ እንዲሁም አመለካከቱን ለማወቅ ጥቂት ተጨማሪ ጥያቄዎች ጠይቀው። አንዳንዶች ምናልባት በሥዕሉ ላይ ባለው ዓይነት ሁኔታ ሥር መኖር አልፈልግም ወይም እንዲህ ያለው ሁኔታ ፈጽሞ የማይሆን ነገር ነው ቢሉ ፍላጎት የላቸውም ብለህ ለመደምደም አትቸኩል። ለምን እንደዚህ ብለው እንደመለሱ በዘዴ ጠይቃቸው። ምናልባት የሚሰጡት መልስ የሰው ልጅ የገጠሙት መፍትሔ የሚገኝላቸው የማይመስሉ ችግሮች ከልብ እንደሚያሳስቧቸው የሚገልጽ ሊሆን ይችላል።—ሕዝ. 9:4
የቤቱ ባለቤት የሚያሳስበውን ነገር እንዳስተዋልክ አቀራረብህ ከእሱ ሁኔታ ጋር እንዲስማማ አድርግ። በቀጥታ የእሱን ፍላጎት የሚነካውን የመንግሥቱን መልእክት ገጽታ ጎላ አድርገህ ግለጽ። እሱን ስለሚያሳስበው ጉዳይ የሚገልጹ አንድ ወይም ሁለት ጥቅሶች አሳየው። (በስተቀኝ በኩል ባለው አምድ ላይ የተሰጡትን ሐሳቦች ተመልከት።) የአምላክ ቃል የሚሰጠውን ሐሳብ እንዲመለከት አድርግ። ፍላጎት ካሳየ ጽሑፉን አበርክትለት ከዚያም ሌላ ቀን መገናኘት እንድትችሉ ቀጠሮ ያዝ። በመጀመሪያ የተወያያችሁበትን ሐሳብ መሠረት በማድረግ ፍላጎቱን ለማሳደግ ጥረት አድርግ።
[ገጽ 4 ላይ የሚገኝ ሣጥን]
የገነትን ገፅታ የሚያሳዩ ሥዕላዊ መግለጫዎች
ፍጥረት መጽሐፍ:- ገጽ 237, 243, 251
አስተማሪ መጽሐፍ:- ገጽ 251-4
እውቀት መጽሐፍ:- ገጽ 4-5, 188-9
አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ብሮሹር:- ገጽ 11, 13
እውነተኛ ሰላም መጽሐፍ:- ገጽ 98
አምላክን አምልክ መጽሐፍ:- ገጽ 92-3
[ገጽ 4 ላይ የሚገኝ ሣጥን]
ሰዎችን የሚያሳስቧቸው ነገሮች
ሙስና፣ የፍትህ መጓደል
ምድርን ማበላሸት
ሞት፣ ሐዘን
በሽታ፣ የአካል ጉዳተኝነት
በእንስሶች ላይ የሚፈጸም በደል
ወንጀል፣ ዓመጽ
ውጤታማ ያልሆነ አገዛዝ
የመንፈስ ጭንቀት
የምግብ እጥረት፣ የተመጣጠነ ምግብ ዕጦት
የሥነ ምግባር ዝቅጠት
የቤትና የኢኮኖሚ ችግር
ድህነት፣ ጭቆና
ጦርነት፣ ሽብርተኝነት
ጭፍን ጥላቻ፣ አድልዎ