ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
የካቲት 28, 2005 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ በቃል መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከጥር 3 እስከ የካቲት 28, 2005 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል። [ማሳሰቢያ:- ከጥያቄው ቀጥሎ መልሱ የሚገኝበት ጽሑፍ ካልተጠቀሰ መልሱን ለማግኘት በግልህ ምርምር ማድረግ ይኖርብሃል።—የአገልግሎት ትምህርት ቤት ገጽ 36-7ን ተመልከት።]
የንግግር ባሕርይ
1. የምንናገረው ነገር ለሰዎች በቀላሉ የሚገባ እንዲሆን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? [be ገጽ 226 አን. 1–ገጽ 227 አን. 1]
2. ተጨማሪ ማብራሪያ የሚፈልጉት እንዴት ዓይነት ቃላት ናቸው? [be ገጽ 227 አን. 2-5]
3. የምናቀርበው ትምህርት የአድማጮችን ግንዛቤ የሚያሰፋ እንዲሆን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? [be ገጽ 231 አን. 1-3]
4. አድማጮች የሚያውቁትን ጥቅስ ትምህርት ሰጪ አድርገን ማቅረብ የምንችለው እንዴት ነው? [be ገጽ 231 አን. 4-5]
5. አድማጮቻችን የሚያውቁትን የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ጠለቅ ብለው እንዲመለከቱት ማድረግ ምን ጥቅም አለው? [be ገጽ 232 አን. 2-4]
ክፍል ቁጥር 1
6. ሰዎች “እግዚአብሔርን ፍራ፤ ትእዛዛቱንም ጠብቅ” የሚለውን መመሪያ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ማስተማር ምን ነገሮችን ይጨምራል? (መክ. 12:13) [be ገጽ 272 አን. 3–ገጽ 273 አን. 1]
7. ሰዎች ይሖዋ የሚለውን ስም ከማወቅም በላይ ማንነቱን እንዲገነዘቡ ልንረዳቸው የምንችለው እንዴት ነው? (ኢዩ. 2:32) [be ገጽ 274 አን. 3-5]
8. ስለ ኢየሱስ ማወቅና ስለ እርሱ መመሥከር ምን ያህል አስፈላጊ ነው? (ዮሐ. 17:3) [be ገጽ 276 አን. 1]
9. ከአምላክ ጋር ጥሩ ዝምድና መመሥረትና መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት ኢየሱስ የሚጫወተውን ሚና ከመገንዘብ ጋር ቀጥተኛ ተዛምዶ የሚኖረው እንዴት ነው? [be ገጽ 276 አን. 2]
10. ኢየሱስ ክርስቶስ ንጉሥ መሆኑን ከልባችን እንደምናምን እንዴት ማሳየት እንችላለን? [be ገጽ 277 አን. 4]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. የአብርሃም አባት ታራ ጣዖት አምላኪ ነበር? (ኢያሱ 24:2)
12. ጌዴዎን ይሖዋ የሰጠውን ኃላፊነት ለመወጣት ድፍረት አንሶት ነበር? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው? (መሳ. 6:25-27)
13. ጌዴዎን ለኤፍሬም ነገድ መልስ ከሰጠበት መንገድ ምን ትምህርት እናገኛለን? (መሳ. 8:1-3)
14. የጊብዓ ነዋሪዎች እንግዶችን ለመቀበል ፈቃደኞች አለመሆናቸው ምን ያመለክታል? (መሳ. 19:14, 15)
15. ‘እያንዳንዱ ሰው መልካም መስሎ የታየውን ማድረጉ’ ትርምስ እንዲፈጠር አላደረገም? (መሳ. 21:25)