ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች የካቲት:- ወደ ይሖዋ ቅረብ። መጋቢት:- ነቅተህ ጠብቅ! ሚያዝያና ግንቦት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች።
◼ መጋቢት 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ አሊያም እርሱ የወከለው ሌላ ወንድም የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። ለእድሳት ወይም ለግንባታ ተብሎ ለብቻ የሚቀመጥ የባንክ ሒሳብ ካለ ይህንንም ለመመርመር ዝግጅት መደረግ አለበት። የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከቀረበ በኋላ የሒሳብ ምርመራው ውጤት ለጉባኤው መነበብ አለበት።
◼ ጸሐፊውና የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሁሉንም የዘወትር አቅኚዎች የአገልግሎት እንቅስቃሴ መመርመር ይኖርባቸዋል። የሰዓት ግባቸው ላይ መድረስ ያልቻሉ አቅኚዎች ካሉ ሽማግሌዎቹ እርዳታ መስጠት የሚቻልበትን መንገድ መቀየስ ይኖርባቸዋል። ተጨማሪ ሐሳብ ለማግኘት የማኅበሩን ዓመታዊ S-201 ደብዳቤዎች ተመልከቱ።
◼ በመታሰቢያው በዓል ሰሞን የሚሰጠው የ2005 ልዩ የሕዝብ ንግግር ርዕስ “ኢየሱስ መሠቃየትና መሞት ያስፈለገው ለምንድን ነው?” የሚል ይሆናል። ከዚህ ጋር የተያያዙ ሌሎች ጉዳዮችን በሚመለከት በመስከረም 2004 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የወጣውን ማስታወቂያ ተመልከት።
◼ ለአስፋፊዎች የተደረገውን አዲስ ዝግጅት በሚመለከት እሑድ መጋቢት 20 ቀን በሚደረገው የሕዝብ ስብሰባ ላይ የሚነገረው ልዩ ማስታወቂያ እንዳያመልጣቸው ሁሉም ወንድሞችና እህቶች በስብሰባው ላይ እንዲገኙ እናበረታታቸዋለን።
◼ በታኅሣሥ የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የወጣው ከሰኔ 27, 2005 ጀምሮ የዳንኤል ትንቢት መጽሐፍ በመጽሐፍ ጥናት እንደሚጠና የሚገልጸው ማስታወቂያ ለእንግሊዝኛ ጉባኤ እንጂ አማርኛን የሚመለከት አይደለም።
◼ ቅርንጫፍ ቢሮው አስፋፊዎች በግል የሚልኩትን የጽሑፍ ትእዛዝ አያስተናግድም። የጉባኤው ወርኃዊ የጽሑፍ ትእዛዝ ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው ከመላኩ በፊት በግል የሚታዘዙ ጽሑፎችን ማግኘት የሚፈልጉ ሁሉ ለጽሑፍ አገልጋዩ ማሳወቅ እንዲችሉ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ በየወሩ ማስታወቂያ እንዲነገር ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል። የትኞቹ ጽሑፎች በልዩ ትእዛዝ እንደሚገኙ እባካችሁ አትርሱ።