የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
የካቲት 14 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 77 (174)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ የሚገኙት ሐሳቦች ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ ከሆኑ በእነዚህ መግቢያዎች በመጠቀም የታኅሣሥ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የታኅሣሥ 2004 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ለናሙና የቀረቡትን መግቢያዎች ከጉባኤው ክልል ጋር እንዴት አስማምቶ መጠቀም እንደሚቻል በአጭሩ ተናገር።—የጥር 2005 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 8ን ተመልከት።
20 ደቂቃ:- አዲሱን ብሮሹር የወሰዱ ሰዎችን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር። የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት ያቀርበዋል። ባለፈው ወር በተወሰደው የአገልግሎት ስብሰባ ክፍል ላይ የቀረበውን ተመላልሶ መጠየቅ ሲደረግ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ በአጭሩ ከልስ፤ በተለይ ሠርቶ ማሳያው ሲደመደም በሚቀጥለው ጊዜ እንደሚወያዩበት በተገለጸው ሣጥን ላይ ትኩረት አድርግ። የሚቻል ከሆነ ባለፈው ጊዜ ይህንን ሠርቶ ማሳያ ያቀረበው አስፋፊ አሁንም በብሮሹሩ ተጠቅሞ ቀጣዩን ተመላልሶ መጠየቅ ሲያደርግ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርብ አድርግ። ከዚያም አስፋፊው በብሮሹሩ የጀርባ ገጽ ላይ በሰፈረው ሐሳብ በመጠቀም የሚያነጋግረው ሰው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲጀምር ይጠይቀዋል፤ በቀጣዩ ቀጠሯቸው አምላክ ከእኛ የሚፈልገው በተባለው ብሮሹር ትምህርት 1 ላይ ጥናት ለመጀመር ይስማማሉ። ሁሉም አስፋፊዎች ነቅተህ ጠብቅ! የተባለውን ብሮሹር ላበረከቱላቸው ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለመጀመር ትኩረት ሰጥተው ጥረት እንዲያደርጉ አበረታታ።
15 ደቂቃ:- “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን እድገት እንዲያደርጉ መርዳት—ክፍል 6።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በመታሰቢያው በዓል ላይ ከወይኑና ከቂጣው የሚካፈሉት በጣም ጥቂት የሆኑት ለምን እንደሆነ ሲጠይቅ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ በአራት ደቂቃ ውስጥ እንዲቀርብ አድርግ። አስጠኚው ጥሩ ጥያቄ መሆኑን በመናገር ተማሪውን ካመሰገነው በኋላ ጥያቄውን በወረቀት ላይ ይጽፍና ከጥናታቸው በኋላ እንዲወያዩበት ሐሳብ ያቀርባል። ከጥናታቸው በኋላ አስጠኚው በማመራመር መጽሐፍ ገጽ 267 ላይ “ከቂጣውና ከወይኑ የሚካፈሉት እነማን ናቸው?” በሚለው ጥያቄ ሥር ያለውን ሐሳብ ያሳየዋል። በጋራ ካነበቡት በኋላ ተማሪው ለጥያቄው ግልጽ የሆነ መልስ እንዳገኘ በመናገር ምስጋናውን ይገልጻል።
መዝሙር 53 (130) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 21 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 60 (143)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 6 ላይ ካለው “ተጨማሪ ምሥክርነት እንዲያገኙ እርዷቸው” ከሚለው ሣጥን ላይ ጎላ ያሉ ሐሳቦችን አቅርብ። ሁሉም ፍላጎት ያለው ሰው ሲያገኙ እባካችሁ ተከታትላችሁ እርዱት (S-43) የሚለውን ቅጽ ወዲያውኑ እንዲሞሉ አበረታታ።
35 ደቂቃ:- “የመታሰቢያው በዓል ሰሞን—የአገልግሎት እንቅስቃሴያችንን ከፍ የምናደርግበት ወቅት።” በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ። አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንቀጽ 6ን ስትወያዩ ከመስከረም 2004 ንቁ! መጽሔት ገጽ 12-13 ላይ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ። ረዳት አቅኚ ለመሆን የተመዘገቡትን አስፋፊዎች ስም ተናገር። ተጨማሪ የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎችን ለማካሄድ የተደረገውን ዝግጅት ግለጽ። ሁሉም በመታሰቢያው በዓል ወራት መንፈሳዊ እንቅስቃሴያቸውን ከፍ እንዲያደርጉ አበረታታቸው። የመታሰቢያው በዓል መጋበዣ ወረቀት እስካሁን ለአስፋፊዎች ካልታደለ ከዚህ ስብሰባ በኋላ መታደል ይኖርበታል።
መዝሙር 8 (21) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 28 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 18 (42)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። አስፋፊዎች የየካቲት ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በገጽ 8 ላይ የሚገኘው ሐሳብ ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ ከሆነ በዚህ መግቢያ በመጠቀም የታኅሣሥ 15 መጠበቂያ ግንብን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ሌሎች ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ መግቢያዎችንም መጠቀም ይቻላል።
20 ደቂቃ:- በመንፈሳዊ ለደከሙት አሳቢነት አሳዩ። (ሥራ 20:35) አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በሐምሌ 1, 2004 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 17-18 አንቀጽ 12-16 ላይ ያለውን ሐሳብ በመጠበቂያ ግንብ ጥናት መልክ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ጥሩ የንባብ ችሎታ ያለው ወንድም አንቀጾቹን እንዲያነብልህ አድርግ። በቅርቡ ከሚደረገው የመታሰቢያ በዓልና የልዩ ሕዝብ ንግግር ጋር በተያያዘ ትምህርቱን እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚቻል ተናገር።
15 ደቂቃ:- ነቅተህ ጠብቅ! የተባለውን ብሮሹር አበርክቱ። በመጋቢት ወር ይህን ብሮሹር ለማበርከት የሚያስችሉ አቀራረቦችን ተናገር፤ እንዲሁም በሠርቶ ማሳያ እንዲቀርቡ አድርግ። በጥር 2005 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይ የወጡትን የናሙና መግቢያዎች ወይም ለጉባኤው ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን መጠቀም ይቻላል።
መዝሙር 33 (72) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መጋቢት 7 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 24 (50)
8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። “የመታሰቢያውን በዓል የሚመለከቱ ማሳሰቢያዎች” ከሚለው ሣጥን ዋና ዋና ሐሳቦችን ከልስ።
20 ደቂቃ:- “ስለ ፍቅራዊ ደግነቱ ይሖዋን እናመስግነው።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። የመታሰቢያው በዓል የሚደረግበትን ቦታና ሰዓት እንዲሁም የተናጋሪውን ስምና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን ተናገር። አንቀጽ 4ን ስትወያዩ አንድ አስፋፊ የመጽሔት ደንበኛውን ለመታሰቢያው በዓል ሲጋብዘው የሚያሳይ አጠር ያለ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
17 ደቂቃ:- “በአገልግሎታችሁ ላይ መጽሔቶችን አበርክቱ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በአንቀጽ 3ና 4 ላይ ያለውን ሐሳብ ለጉባኤው እንደሚስማማ አድርገህ አቅርበው። በንግድ አካባቢዎች፣ በጎዳናዎች ላይ፣ ሕዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች ወይም መደበኛ ባልሆነ መንገድ ምሥክርነት በሚሰጡበት ወቅት መጽሔት በማበርከት ረገድ የተዋጣላቸውን አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች ቃለ መጠይቅ አድርግላቸው። በእነዚህ አጋጣሚዎች መጽሔቶችን የሚያበረክቱት እንዴት እንደሆነ ጠይቃቸው። አንድን አቀራረብ ወይም እውነተኛ ተሞክሮ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ በአጭሩ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 64 (151) እና የመደምደሚያ ጸሎት።