ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ሚያዝያ 25, 2005 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ በቃል መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከመጋቢት 7 እስከ ሚያዝያ 25, 2005 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል። [ማሳሰቢያ:- ከጥያቄው ቀጥሎ መልሱ የሚገኝበት ጽሑፍ ካልተጠቀሰ መልሱን ለማግኘት በግልህ ምርምር ማድረግ ይኖርብሃል።—የአገልግሎት ትምህርት ቤት ገጽ 36-7ን ተመልከት።]
የንግግር ባሕርይ
1. አንድ ክፍል ለማቅረብ ስንዘጋጅ በተመደበልን ጽሑፍ በሚገባ መጠቀም የምንችለው እንዴት ነው? እንዲህ ማድረጋችን አስፈላጊ የሆነውስ ለምንድን ነው? [be ገጽ 234 አን. 1-3፣ ሣጥኖቹ]
2. ክፍል ስናቀርብ በተመደበልን ጽሑፍ ላይ ካለው ሐሳብ ምን ያህሉን ልንጠቀምበት ይገባል? [be ገጽ 234 አን. 4 እስከ ገጽ 235 አን. 1]
3. በመስክ አገልግሎት ላይ ውይይት ለመጀመር በጥያቄዎች መጠቀም የምንችለው እንዴት ነው? (ሥራ 8:30) [be ገጽ 236 አን. 2-5]
4. የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎቻችን ‘የማመዛዘን ችሎታቸውን’ እንዲጠቀሙ ለማበረታታት ጥያቄዎች እንዴት ይረዱናል? (ሮሜ 12:1 NW) [be ገጽ 238 አን. 1]
5. በሮሜ 8:31, 32 እና በኢሳይያስ 14:27 ላይ የሚገኙት ጥያቄዎች ዓላማ ምንድን ነው? [be ገጽ 239 አን. 1-2]
ክፍል ቁጥር 1
6. ደቀ መዛሙርት በማድረጉ ሥራችን ‘ክርስቶስን መሠረት በማድረግ’ መገንባት የምንችለው እንዴት ነው? (1 ቆሮ. 3:11) [be ገጽ 278 አን. 1-2]
7. ይሖዋ በ1914 ለልጁ ሙሉ ሥልጣን የሰጠው በመሆኑ “መንግሥትህ ትምጣ” ብለን መጸለያችን ምን ትርጉም አለው? (ማቴ. 6:9, 10) [be ገጽ 279 አን. 4]
8. ሁሉም ክርስቲያኖች ማንበብ መቻልን ትኩረት ሊሰጡት የሚገባው ለምንድን ነው? ኢየሱስ በዚህ ረገድ ምሳሌ የተወልን እንዴት ነው? [w03 3/15 ገጽ 10 አን. 5፤ ገጽ 12 አን. 2]
9. ኢዮስያስና ኢየሱስ የተዉት ምሳሌ ወጣቶች መንፈሳዊ እድገት እንዲያደርጉ የሚረዳቸው እንዴት ነው? [w03 4/1 ገጽ 8 አን. 3-4፤ ገጽ 10 አን. 3]
10. በአምላክ መተማመን የምንችለው ለምንድን ነው? (ምሳሌ 3:5, 6) [w03 11/1 ገጽ 4 አን. 6 እስከ ገጽ 5 አን. 1]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. ሐና በወቅቱ በእስራኤል ሰብዓዊ ንጉሥ ባይኖርም “[ይሖዋ] ለንጉሡ ኀይልን ይሰጣል” በማለት የጸለየችው ለምን ነበር? (1 ሳሙ. 2:10)
12. እስራኤላውያን የቃል ኪዳኑን ታቦት ቢይዙም በጦርነቱ መሸነፋቸው ምን ያስተምረናል? (1 ሳሙ. 4:3, 4, 10)
13. አንደኛ ዜና መዋዕል 2:13-15 ዳዊት የእሴይ ሰባተኛ ልጅ እንደሆነ ሲናገር 1 ሳሙኤል 16:10, 11 ደግሞ ስምንተኛ ልጅ እንደሆነ አድርጎ የሚናገረው ለምንድን ነው? [w02 9/15 ገጽ 31]
14. ሳኦልን ያሠቃየው “ክፉ መንፈስ” ምንድን ነው? (1 ሳሙ. 16:14)
15. በዓይንዶር በነበረችው ሙታን ሳቢ አማካኝነት “ሳሙኤል” እንደተናገረ የተገለጸው ትንቢት በትክክል ተፈጽሟል? (1 ሳሙ. 28:16-19) [w88 1/15 ገጽ 3 አን. 3-4]