የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ግንቦት 9 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 97 (217)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ የሚገኙትን የመግቢያ ሐሳቦች (ለጉባኤያችሁ ክልል የሚስማማ ከሆነ) በመጠቀም የመጋቢት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የመጋቢት 2005 ንቁ! መጽሔቶችን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ሌሎች ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ መግቢያዎችን መጠቀም ይቻላል። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ በሕዝብ መጓጓዣ ላይ መደበኛ ባልሆነ መንገድ መጽሔት ሲበረከት የሚያሳይ ይሁን።
15 ደቂቃ:- ልብ ለመንካት በአምላክ ቃል ተጠቀሙ። በየካቲት 1, 2005 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 28-31 ላይ የተመሠረተ ንግግር። ኢየሱስ ጴጥሮስን ለመርዳት ጥቅሶችን እንዴት እንደተጠቀመባቸው አብራራ። የልጆቻችንን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችንን እንዲሁም የራሳችንን አስተሳሰብና ስሜት ማስተካከል አስፈላጊ ሆኖ ስናገኘው የኢየሱስን ምሳሌ እንዴት መከተል እንደሚቻል አብራራ።
20 ደቂቃ:- “ለቤተሰባችሁ ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ፕሮግራም አውጡ።” ከሁለት ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ በምታቀርበው የንግግሩ መግቢያ ላይ በጽሑፍ የሰፈረ ፕሮግራም ያለውን ጥቅም በማጉላት በገጽ 6 ላይ ያለውን ፕሮግራም እንዴት መሙላት እንደሚቻል ግለጽ። ቀጥሎም “የቤተሰብ ፕሮግራም ይኑራችሁ—ለጉባኤ ስብሰባዎች” የሚለውን ርዕስ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አድማጮች ሌሎች ጉዳዮች ከጉባኤ ስብሰባዎች ጋር እንዳይጋጩባቸው ያደረጉት እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ ጠይቃቸው። የቤተሰብ ፕሮግራማችሁ ምን ሌሎች ነገሮችን ሊያካትት እንደሚችል በቀጣዮቹ ሳምንታት ይቀርባል።
መዝሙር 47 (112) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ግንቦት 16 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 89 (201)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በልዩ የአገልግሎት ዘመቻው ወቅት ገና ያልተሸፈኑ ክልሎች ካሉ ተናገር።
15 ደቂቃ:- “የቤተሰብ ፕሮግራም ይኑራችሁ—አብሮ ለማገልገል።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አድማጮች በቤተሰብ መልክ አዘውትሮ በአገልግሎት መካፈል ያለውን ጥቅም እንዲናገሩ ጋብዝ።
20 ደቂቃ:- “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን እድገት እንዲያደርጉ መርዳት—ክፍል 9።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንቀጽ ሁለትን ስትወያዩ ከታኅሣሥ 2004 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 5 ላይ አንድ ወይም ሁለት ነጥቦችን አጉላ። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሲመራ የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያም አቅርብ። አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ከተባለው ብሮሹር ላይ ትምህርት ሁለትን አጥንተው ሲጨርሱ አስጠኚው ተማሪውን “የአምላክ ስም ማን እንደሆነ ለጓደኛህ እንዴት ታስረዳዋለህ?” ብሎ ይጠይቀዋል። ተማሪው ዘፀአት 6:3ን (የ1879 ትርጉም ) እንዴት እንደሚጠቀምበት ይገልጻል፤ ከዚያም አስጠኚው ያመሰግነዋል።
መዝሙር 43 (98) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ግንቦት 23 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 57 (136)
12 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። በገጽ 8 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም (ለአገልግሎት ክልላችሁ የሚስማማ ከሆነ) የመጋቢት 15ን መጠበቂያ ግንብ እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ሌሎች መግቢያዎችን መጠቀም ይቻላል።
18 ደቂቃ:- “የይሖዋ ቀን ቀርቧል።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ይህንን ክፍል ስትዘጋጅ የዳንኤል ትንቢት የተባለውን መጽሐፍ ገጽ 59 አንቀጽ 28ን ተመልከት።
15 ደቂቃ:- “የቤተሰብ ፕሮግራም ይኑራችሁ—ለቤተሰብ ጥናት።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ለቤተሰብ ጥናት ምን ዓይነት ፕሮግራም እንዳወጡና አዘውትሮ ለማድረግም ምን ጥረት እንደጠየቀባቸው የሚናገሩ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች አስቀድመህ አዘጋጅ።
መዝሙር 65 (152) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ግንቦት 30 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 84 (190)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የግንቦት ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በሰኔ የሚበረከተውን ጽሑፍ ተናገር። በጥር 2005 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይ የወጡትን አንድ ወይም ሁለት የናሙና አቀራረቦች በመጠቀም (ለጉባኤያችሁ የአገልግሎት ክልል የሚስማማ ከሆነ) እንዴት ጽሑፎችን ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ሌሎች አቀራረቦችን መጠቀም ይቻላል።
20 ደቂቃ:- “የቤተሰብ ፕሮግራም ይኑራችሁ—የዕለቱን ጥቅስ ለመመርመር።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ቤተሰባቸው አንድ ላይ ሆኖ የዕለቱን ጥቅስ መመርመሩ ምን ጥቅም እንዳስገኘላቸውና እንዲህ ለማድረግ ተግባራዊ ሆኖ ያገኙት ምን ዓይነት ፕሮግራም እንደሆነ አድማጮች ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።
15 ደቂቃ:- በመጋቢት፣ በሚያዝያና በግንቦት ወር ከመስክ አገልግሎት ያገኟቸውን አበረታች ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ወይም በሠርቶ ማሳያ እንዲቀርቡ አድርግ። በመታሰቢያው በዓል ሰሞን አገልግሎታቸውን ከፍ ለማድረግ ሲሉ ያደረጉትን ጥረት እንዲሁም ያገኙትን በረከት እንዲናገሩ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች አስቀድመህ አዘጋጅ።
መዝሙር 51 (127) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሰኔ 6 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 66 (155)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
20 ደቂቃ:- “የመጽሔት ደንበኞችን ፍላጎት ለመቀስቀስ ጥረት አድርጉ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንቀጽ 3ን ስትወያዩ ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 228-232 ላይ እንዲያተኩሩ አድርግ። ለመጽሔት ደንበኛችን መጽሔት ባበረከትን ቁጥር አንድ ጥቅስ በመጥቀስ የአምላክ መንግሥት ወደፊት ምን ነገሮችን እንደምታከናውን ለማስረዳት በዚህ ጽሑፍ ላይ የሰፈረውን ሐሳብ መጠቀም እንችላለን። አስፋፊው የመጽሔት ደንበኛው የሆነ ሰውን አንድ ጥቅስ ተጠቅሞ ሲያወያየው የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። አስፋፊው የቤቱ ባለቤት ጥቅሱን በትክክል መረዳት እንዲችል ብሎም በሕይወቱ ውስጥ ምን ተግባራዊ ጠቀሜታ እንዳለው እንዲገነዘብ ጥቅሱ የያዘውን ትምህርት በአጭሩ ያብራራለታል።
መዝሙር 46 (107) እና የመደምደሚያ ጸሎት።