የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 7/05 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ሐምሌ 11 የሚጀምር ሳምንት
  • ሐምሌ 18 የሚጀምር ሳምንት
  • ሐምሌ 25 የሚጀምር ሳምንት
  • ነሐሴ 1 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
km 7/05 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ሐምሌ 11 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 38 (85)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች በመጠቀም (ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ ከሆኑ) የግንቦት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የግንቦት 2005 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ሌሎች ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ መግቢያዎችንም መጠቀም ይቻላል። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ ውይይቱን ለማስቆም “ሥራ አለብኝ” ለሚል ሰው በተለያየ መንገድ እንዴት መልስ መስጠት እንደሚቻል አሳይ።—ማመራመር መጽሐፍ ከገጽ 19-20ን ተመልከት።

15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

20 ደቂቃ:- “ምሥራቹን በተቻለ መጠን ለብዙ ሰዎች መስበክ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንቀጽ 5 ላይ ስትደርስ በሰኔ 2005 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 8 ላይ ከቀረቡት ሐሳቦች መካከል በአገልግሎት ክልሉ ውስጥ ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉትን ከልስ።

መዝሙር 94 (212) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሐምሌ 18 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 39 (86)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በነሐሴ 15, 2000 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 32 ላይ ያለውን ሐሳብ በአጭሩ አቅርብ። እረፍት ላይ ወይም ከዘወትር ልማዳችን በተለየ ሁኔታ ውስጥ ብንሆን እንኳ በየዕለቱ መጽሐፍ ቅዱስ የማንበብ ቋሚ ፕሮግራም መከተል ያለውን ጥቅም አጉላ።

15 ደቂቃ:- “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን እድገት እንዲያደርጉ መርዳት—ክፍል 11።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አስጠኚውና አንድ አዲስ አስፋፊ ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ አስቀድመው ሲዘጋጁ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። በመጀመሪያው ቀን ላይ ያደረጉትን ውይይት ከከለሱ በኋላ በተመላልሶ መጠየቁ ቀን የሚወያዩበትን ተስማሚ ነጥብ ይመርጣሉ። በተጨማሪም አጭር መግቢያና ተመላልሶ መጠየቁን የሚደመድሙበት ጥያቄ ያዘጋጃሉ። ከዚያም ሠርቶ ማሳያው የተዘጋጁትን አቀራረብ ለመለማመድ በዝግጅት ላይ እንዳሉ ይደመደማል።

20 ደቂቃ:- ሌሎች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲወዱት መርዳት። እውነተኛው አንድ አምላክ ያስገኘው የአምልኮ አንድነት በተባለው መጽሐፍ ገጽ 21-23 ከአንቀጽ 3-6 ላይ ያለውን ሐሳብ በጥያቄና መልስ አቅርብ። በመጽሐፉ ላይ ባሉት ጥያቄዎች ተጠቀም። ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ ከተባለው ብሮሹር ገጽ 32 ላይ ተጨማሪ ሐሳብ አቅርብ።

መዝሙር 5 (10) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሐምሌ 25 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 58 (138)

15 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። በገጽ 4 ላይ ያለውን ሐሳብ በመጠቀም (ለአገልግሎት ክልላችሁ የሚስማማ ከሆነ) የግንቦት 15ን መጠበቂያ ግንብ እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ተግ​ባራዊ ሊሆን የሚችል ሌላ መግቢያ መጠቀም ይቻላል። ሠርቶ ማሳያው ገበያ ወይም ሰው በሚበዛበት ሌላ ቦታ ላይ መደበኛ ባልሆነ መንገድ መጽሔት ሲያበረክቱ የሚ​ያሳይ ይሁን።

10 ደቂቃ:- በልጆቻችሁ ልብ ውስጥ እውነትን ቅረጹ። (ዘዳ. 6:​7) በነሐሴ 15, 2002 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 30-31 ላይ ተመስርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። የይሖዋ ምሥክር ያልሆነ የትዳር ጓደኛ ያለው አንድ ክርስቲያን ወላጅ፣ ልጆቹን ለማሠልጠን ምን ማድረግ እንዳለበት መመሪያ የሚሆኑትን ቅዱስ ጽሑፋዊ መሠረታዊ ሥርዓቶች አጉላ።

20 ደቂቃ:- “ለሰዎች ያለብን ዕዳ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ከሐምሌ 1, 2000 መጠበቂያ ግንብ ላይ ገጽ 11 አንቀጽ 13ን ጨምረህ አቅርብ።

መዝሙር 37 (82) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 1 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 83 (187)

15 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የሐምሌ ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። አድማጮች የአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 70ን እንዲያወጡ ጋብዛቸው። ከዚያም አንቀጽ 1ና 2ን እንዲሁም “በስብሰባ ላይ ሐሳብ ስትሰጥ” የሚለውን ሣጥን ከአድማጮች ጋር ተወያዩበት።

15 ደቂቃ:- “ልጆችህ በአገልግሎት እድገት እንዲያደርጉ እርዳቸው።” በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። አንድ ወላጅ ከልጁ ጋር ቀላል አቀራረብ ተጠቅመው ሲያነጋግሩ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ከዚያም ወላጁ አስተዋጽኦ ማድረግ የሚቻልበትን ዝግጅት በአጭሩ በማብራራት አቀራረቡን ይደመድማል።

15 ደቂቃ:- ተስማሚ የሆነ አቀራረብ ለመጠቀም ትሞክራለህ? በጥር 2005 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 6 ላይ ተመ​ሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። እዚያ ላይ ያሉትን አቀራረቦች ከልስ እንዲሁም በነሐሴ ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ለማበርከት አቀራረባችንን እንዴት ለሁኔታው እንደሚስማማ ማድረግ እንደምንችል ተናገር። አንድ ወይም ሁለት ሠርቶ ማሳያዎችን አቅርብ።

መዝሙር 44 (105) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ