የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
መስከረም 12 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 11 (29)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች በመጠቀም (ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ ከሆኑ) የሐምሌ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የሐምሌ 2005 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ሌሎች ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ መግቢያዎችንም መጠቀም ይቻላል። አንደኛውን ሠርቶ ማሳያ የጉባኤ ሽማግሌ፣ ሁለተኛውን ሠርቶ ማሳያ ደግሞ አንድ ወጣት እንዲያቀርቡት አድርግ። ከእያንዳንዱ ሠርቶ ማሳያ በኋላ የአቀራረቡን ጥሩ ጎኖች ተናገር።
20 ደቂቃ:- “ጊዜያችሁን በጥበብ ተጠቀሙበት።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አድማጮች መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ ለማንበብ የሚያስችል ፕሮግራም ለማውጣት ምን ዝግጅት እንዳደረጉ እንዲናገሩ አድርግ። በቤተሰብም ሆነ በግለሰብ ደረጃ ለመንፈሳዊ እንቅስቃሴያቸው ፕሮግራም ለማውጣት የግንቦት 2005ን የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ እንዲጠቀሙበት አበረታታ።
15 ደቂቃ:- “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን እድገት እንዲያደርጉ መርዳት።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ክፍል 1ና 2 ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። የነሐሴ 2004 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 1ንም መጠቀም ይቻላል። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ከመምራትህ በፊት በሚገባ መዘጋጀት የሚያስፈልገው ለምንድን ነው? ይህስ ምን ማድረግን ይጨምራል? አድማጮች በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ወጥተው የነበሩትን ሐሳቦች እንዴት ተግባራዊ እንዳደረጓቸው እንዲናገሩ አድርግ። በአባሪው የመጀመሪያ ገጽ አናት ላይ ያለውን ሣጥን በተመለከተ ሐሳብ በመስጠት ክፍልህን ደምድም።
መዝሙር 95 (213) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 19 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 74 (168)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
20 ደቂቃ:- ያለፈው ዓመት የአገልግሎት እንቅስቃሴያችን ምን ይመስል ነበር? የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ባለፈው የአገልግሎት ዓመት በአገልግሎት በተከናወኑት መልካም ነገሮች ላይ ትኩረት በማድረግ ያለፈውን ዓመት እንቅስቃሴ ይከልሳል። ለመልካም ጥረታቸው አመስግናቸው። በያዝነው የአገልግሎት ዓመት ጉባኤው ትኩረት ሊያደርግባቸው የሚገቡ አንድ ወይም ሁለት ዘርፎች ጥቀስ። አቅኚዎች ያከናወኑትን ትጋት የታከለበት ሥራ በመጥቀስ አመስግናቸው። አገልግሎት ያቆሙ አስፋፊዎችን ለመርዳት የተደረገው ጥረት ያስገኘውን መልካም ውጤት ተናገር።
15 ደቂቃ:- “እርስ በርሳችሁ መተናነጻችሁን ቀጥሉ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አድማጮች ሌሎች ባሳይዋቸው ፍቅራዊ አሳቢነት እንዴት እንደተጠቀሙ ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ።
መዝሙር 69 (160) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 26 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 95 (213)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። አስፋፊዎች የመስከረም ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው።
15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
20 ደቂቃ:- በመጽሔቶች በመጠቀም ምሥራቹን መስበክ። በጥቅምት ወር መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን እናበረክታለን። በየካቲት 2005 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 8 አንቀጽ 3-6 ላይ የሚገኙትን የሚከተሉትን ሐሳቦች ከአድማጮች ጋር ተወያዩባቸው:- (1) ሁለቱንም መጽሔቶች አንድ ላይ አበርክቱ። (2) በሳምንቱ ውስጥ መጽሔት የምታበረክቱበት አንድ ቀን እንዲኖራችሁ ፕሮግራም አውጡ። (3) በየወሩ ምን ያህል መጽሔት እንደምታበረክቱ ግብ ይኑራችሁ። (4) መጽሔቶችን ለማበርከት የሚያስችሉ አጋጣሚዎች አያምልጧችሁ። (5) የቆዩ መጽሔቶችን በደንብ ተጠቀሙባቸው። እነዚህን ሐሳቦች ለጉባኤው ክልል በሚስማማ ሁኔታ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ግለጽ። ከዚያም በገጽ 8 ላይ የሚገኘውን ሐሳብ በመጠቀም (ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ ከሆነ) የሐምሌ 15 መጠበቂያ ግንብ ሲበረከት የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ሌሎች ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ መግቢያዎችንም መጠቀም ይቻላል። በተጨማሪም በመጽሔቶቹ ላይ የሚገኙ በክልላችሁ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ትኩረት ሊስቡ የሚችሉ ሌሎች ርዕሶች መርጠህ ተናገር፤ ከዚያም ከእነዚህ ርዕሶች በአንዱ ላይ የተመሠረተ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ከእያንዳንዱ ሠርቶ ማሳያ በኋላ የአቀራረቡን ጠቃሚ ጎኖች ተናገር።
መዝሙር 1 (3) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥቅምት 3 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 54 (132)
5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
20 ደቂቃ:- “‘በሙሉ ልብ’ እንዲታዘዙ ሌሎችን መርዳት።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አድማጮች ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ በተጠቀሱት ጥቅሶች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።
20 ደቂቃ:- የይሖዋን ልብ ማስደሰት። (ምሳሌ 27:11) ይሖዋን ለረጅም ዓመታት በታማኝነት ካገለገሉ ሁለት ወይም ሦስት አስፋፊዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርግ። እያንዳንዳቸው ለይሖዋ ታዛዥ ሆነው እንዲቀጥሉ የረዷቸውን አንድ ወይም ሁለት ነጥቦች እንዲናገሩ አድርግ። ከሚጠቀሱት ነገሮች መካከል ትጋት የተሞላበት የግል ጥናትን፣ አዘውትሮ በጉባኤ መገኘትን፣ ከሌሎች ታማኝ ክርስቲያኖች ጋር መወዳጀትን፣ በመስክ አገልግሎት በሙሉ ልብ መካፈልን፣ ከልብ በመነጨ ስሜት መጸለይንና ጎጂ ከሆኑ መዝናኛዎች መራቅን ማካተት ይቻላል። ታዛዥነታቸውን የሚፈታተኑ ምን ነገሮች ገጥመዋቸዋል? በተሳካ ሁኔታ ሊወጡት የቻሉት እንዴት ነው? ታዛዥ በመሆናቸው የተባረኩትስ እንዴት ነው?
መዝሙር 44 (105) እና የመደምደሚያ ጸሎት።