ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ጥቅምት 31, 2005 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ በቃል መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከመስከረም 5 እስከ ጥቅምት 31, 2005 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል። [ማሳሰቢያ:- ከጥያቄው ቀጥሎ መልሱ የሚገኝበት ጽሑፍ ካልተጠቀሰ መልሱን ለማግኘት በግልህ ምርምር ማድረግ ይኖርብሃል።—የአገልግሎት ትምህርት ቤት ገጽ 36-7ን ተመልከት።]
የንግግር ባሕርይ
1. የአምላክን ቃል በምናስተምርበት ጊዜ ትምህርቱ በሰዎች ምሳሌያዊ ልብ ውስጥ ጠልቆ እንዲገባ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? (ማቴ. 13:19) [be ገጽ 258 አን. 1-2፣ ሣጥን]
2. በአንድ ሰው ልብ ውስጥ ያለውን ሐሳብ እንድናስተውል ምን ሊረዳን ይችላል? ሆኖም ምን ነገር መዘንጋት የለብንም? [be ገጽ 259 አን. 1-2]
3. በምናስተምርበት ወቅት የይሖዋን ግሩም ባሕርያት ጎላ አድርገን መግለጽ ያለብን ለምንድን ነው? [be ገጽ 260 አን. 1]
4. የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎቻችን ማስተካከያ ማድረግ የሚጠይቁባቸውን ሁኔታዎች እንዲያስተውሉ እንዴት ልንረዳቸው እንችላለን? [be ገጽ 260 አን. 4-5]
5. የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎቻችን ወይም አድማጮቻችን አንድን ነገር ለማድረግ የሚያነሳሳቸውን ውስጣዊ ዝንባሌ እንዲመረምሩ ለመርዳት ምን ማድረግ እንችላለን? [be ገጽ 261 አን. 5–ገጽ 262 አን. 1]
ክፍል ቁጥር 1
6. ይሖዋን ‘ከልብ መሻት’ ሲባል ምን ማለት ነው? እንዲህ እያደረግን መሆኑን ማሳየት የምንችለውስ እንዴት ነው? (ዕብ. 11:6) [w03 8/15 ገጽ 25 አን. 2፤ ገጽ 26 አን. 1-2፤ ገጽ 27 አን. 2]
7. ‘የጤናማው ቃል ምሳሌ’ ምንድን ነው? ሽማግሌዎች ይህን ቃል መያዛቸውን እንዴት ማሳየት ይችላሉ? (2 ጢሞ. 1:13, 14 የ1954 ትርጉም) [w03 1/1 ገጽ 29 አን. 3–ገጽ 30 አን. 1]
8. አንድ መጽሐፍ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መካተት ይገባው እንደሆነና እንዳልሆነ የሚወስኑት ነገሮች ምንድን ናቸው? [si ገጽ 299 አን. 5-6]
9. በሁለተኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ገደማ የተጻፈው የሙራቶሪያን ፍራግመንት የተባለው ጽሑፍ የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል መሆናቸውን የሚያረጋግጠው እንዴት ነው? [si ገጽ 302 አን. 19]
10. ቅዱሳን ጽሑፎች ራሳቸው ለመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች ምን ዓይነት ሥልጣን ይሰጣሉ? ጥንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ምን ነገር አከናውነዋል? [si ገጽ 307 አን. 9]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. ሁለተኛ ነገሥት 13:21 እንደ ቅዱስ ተደርገው ለሚታዩ ነገሮች ክብር መስጠትን ይደግፋል?
12. ሕዝቅያስ ከግብጾች ጋር ወታደራዊ ጥምረት ፈጥሮ ነበር? (2 ነገ. 18:19-21, 25)
13. የአሦራውያን የታሪክ መዛግብት ይሖዋ በሰናክሬም ላይ የተቀዳጀውን አስደናቂ ድል በቀጥታ ባይጠቅሱም ከእነዚህ ዘገባዎች ምን ጠቃሚ ትምህርት ታገኛለህ? (2 ነገ. 19:35, 36)
14. የሰላትያል አባት ማን ነበር? (1 ዜና 3:16-18)
15. በንጉሥ ሳኦል ዘመን ይኖሩ የነበሩት የሮቤልና የጋድ ልጆች እንዲሁም የምናሴ ነገድ እኩሌታ በዛሬው ጊዜ ለሚገኙ የይሖዋ አገልጋዮች ምን ግሩም ምሳሌ ትተውላቸዋል? (1 ዜና 5:18-22)