የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 10/05 ገጽ 9
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
km 10/05 ገጽ 9

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ጥቅምት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች፤ ኅዳር:- እውቀት፤ ታኅሣሥ:- ታላቅ ሰው፤ ጥር:- ነቅተህ ጠብቅ!

◼ የጥቅምት ወር አምስት ቅዳሜና እሁዶች ስላሉት ረዳት አቅኚ ሆኖ ለማገልገል ግሩም አጋጣሚ ይከፍታል።

◼ በዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን ውስጥ “የ2006 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም” አባሪ ሆኖ የወጣ ሲሆን ዓመቱን ሙሉ ልንጠቀምበት እንድንችል በጥሩ ሁኔታ ልንይዘው ይገባል።

◼ በዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 6 ላይ የሚገኘውን ክፍል በ2006 የአገልግሎት ዓመት ከምናደርገው የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም ጋር በተያያዘ የምንጠቀምበት ስለሆነ በጥሩ ቦታ ልታስቀምጡት ይገባል።

◼ ከኅዳር 28, 2005 ጀምሮ በጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት ላይ የሚጠናው የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን የተባለው መጽሐፍ ጥራዝ 2 ይሆናል።

◼ የመጋበዣ ወረቀቶችን ማዘዝና ማተምን አስመልክቶ ያለውን አሠራር ለማቅለል አዲስ የመጋበዣ ወረቀት ተዘጋጅቷል። በዚህ ቅጽ የፊት ገጽ ላይ ሁሉንም የጉባኤ ስብሰባዎች አስመልክቶ አጭር መግለጫ ሰፍሯል። በጀርባው በኩል ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስን በነፃ እንዲማሩ የቀረበ ግብዣና አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የሚለውን ብሮሹር ለማግኘት የሚሞላ መጠየቂያ ቅጽ አለው። ቅጹ የመንግሥት አዳራሹ የሚገኝበትን አድራሻ እንዲሁም የስብሰባውን ቀንና ሰዓት የሚገልጽ መረጃ ስላልያዘ የመጋበዣ ወረቀቱን ፍላጎት ላለው ሰው ስትሰጡ ቦታውንና ሰዓቱን ልትነግሩት ትችላላችሁ። የመጋበዣ ወረቀቱ የጉባኤውን አድራሻና ተጨማሪ መረጃዎች ለመጻፍ ወይም ለማተም የሚያስችል በቂ ቦታ አለው። ከዚህ በኋላ የጉባኤ ጸሐፊዎች የመጋበዣ ወረቀቶችን ለማዘዝ የመጋበዣ ወረቀት ማዘዣ (S-16) የተባለውን ቅጽ መጠቀም አይኖርባቸውም። ከዚህ ይልቅ የጽሑፍ አስተባባሪው በጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S-14-AM) በመጠቀም የመጋበዣ ወረቀቶችን ማዘዝ ይችላል። የመጋበዣ ወረቀት ምኅፃረ ቃሉ sf ነው።

◼ ከጥር 2006 ጀምሮ የእንግሊዝኛው ንቁ! መጽሔት በወር አንዴ የሚታተም ስለሆነ አማርኛውም ከእንግሊዝኛው ጋር አንድ ዓይነት ይዘት ይኖረዋል። ስለዚህ የእንግሊዝኛ ንቁ! መጽሔት ትእዛዝ ያላችሁ ጉባኤዎችና ቡድኖች የመጽሔት ትእዛዛችሁን መቀነስ ያስፈልጋችሁ እንደሆነና እንዳልሆነ አመዛዝናችሁ እንድትወስኑ እናበረታታችኋለን።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ