የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 11/05 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ኅዳር 14 የሚጀምር ሳምንት
  • ኅዳር 21 የሚጀምር ሳምንት
  • ኅዳር 28 የሚጀምር ሳምንት
  • ታኅሣሥ 5 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
km 11/05 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ኅዳር 14 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 98 (220)

10 ደቂቃ:-የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች በመጠቀም (ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ ከሆኑ) የመስከረም 1 መጠበቂያ ግንብ እና የመስከረም 2005 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ሌሎች ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ መግቢያዎችንም መጠቀም ይቻላል። ሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ውይይቱን ለማስቆም “ለሃይማኖት ግድ የለኝም” ለሚል ሰው በተለያየ መንገድ መልስ መስጠት እንደሚቻል የሚያሳዩ ይሁኑ።—ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 17ን ተመልከት።

15 ደቂቃ:-የይሖዋን ልብ ደስ የሚያሰኝ ልግስና። በኅዳር 1, 2005 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 26-30 ላይ ተመሥርቶ በአንድ ሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።

20 ደቂቃ:-“የይሖዋን ክብር አውጁ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንቀጽ 4ን ስትወያዩ መልካም ባሕርይ ምሥክርነት ለመስጠት በር የሚከፍተው እንዴት እንደሆነ አድማጮች አጠር ያለ ተሞክሮ እንዲናገሩ ጋብዝ።

መዝሙር 69 (160) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ኅዳር 21 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 91 (207)

10 ደቂቃ:-የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

20 ደቂቃ:-ይሖዋን አምላክህ አድርገው። በሚያዝያ 1, 2005 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 25-28 ላይ ተመሥርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። አብርሃም፣ ዳዊትና ኤልያስ ከተዉት ምሳሌ ምን ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ትምህርት ልናገኝ እንደምንችል ተናገር።

15 ደቂቃ:-“አስተዋይ በመሆን ለሰዎች ልባዊ አሳቢነት አሳዩ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንድ አስፋፊ የቤቱ ባለቤት ለምን ጉዳይ ትኩረት እንደሚሰጥ የሚጠቁም ነገር ተመልክቶ የመግቢያ ሐሳቡን ከዚያ ጋር በሚስማማ ሁኔታ ሲያቀርብ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።

መዝሙር 31 (67) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ኅዳር 28 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 2 (4)

12 ደቂቃ:-የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። አስፋፊዎች የኅዳር ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በገጽ 8 ላይ የሚገኘውን ሐሳብ በመጠቀም (ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ ከሆነ) የመስከረም 15 መጠበቂያ ግንብ ሲበረከት የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ሌሎች ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ መግቢያዎችንም መጠቀም ይቻላል። ለዓለም አቀፉ ሥራ የገንዘብ መዋጮ መጠየቅ እንዳለባቸው አስታውሳቸው።

15 ደቂቃ:-“እርዳታ ማበርከት የምንችለው እንዴት ነው?” በንግግር የሚቀርብ። የይሖዋ ሕዝቦች ወንድሞቻቸው ችግር በገጠማቸው ወቅት እርዳታ ለማበርከት ያደረጉትን ጥረት የሚያሳዩ ጥቂት ምሳሌዎች ጥቀስ። (ንቁ! ኅዳር 2003 ገጽ 10-15፣ ንቁ! ታኅሣሥ 2002 ገጽ 21-26፣ ንቁ! ኅዳር 2001 ገጽ 13-17 ተመልከት። ሌሎች ጽሑፎችንም መጠቀም ይቻላል።) ከዚያም በዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 7 ላይ ከሚገኘው ክፍል ዋና ዋና ነጥቦችን ጨምረህ አቅርብ። አስፋፊዎች አደጋ ለደረሰባቸው ወንድሞች ሰብዓዊ እርዳታና ለመልሶ ማቋቋም ሥራ ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ ከሆነ ለዓለም አቀፉ ሥራ ብሎ መዋጮ ማድረጉ ተመራጭ መሆኑን አጉላ።

18 ደቂቃ:-በታኅሣሥ ወር ምሥራቹን መስበክ። በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ከጥር 2005 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 6 ላይ “የናሙና አቀራረቦችን እንዴት ልንጠቀምባቸው ይገባል?” ከሚለው ክፍል ላይ የሚከተሉትን ነጥቦች በአምስት ደቂቃ ውስጥ ከልስ:- (1) የናሙና አቀራረቦችን በራሳችን አባባል ብንናገራቸው ይበልጥ ውጤታማ እንሆናለን። (2) የማመዛዘን ችሎታችንን በመጠቀም አቀራረባችንን እንደ አካባቢው ሁኔታ ማስተካከል አለብን። (3) በክልላችን ውስጥ ያሉትን ሰዎች ሁኔታና አስተሳሰብ ግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርብናል። (4) ልናበረክተው ካሰብነው ጽሑፍ ላይ አንድ ምዕራፍ በጥሞና በማንበብ የሰዎችን ትኩረት ሊስቡ የሚችሉ ነጥቦች መፈለግ አለብን። (5) ለናሙና በቀረቡት መግቢያዎች ብቻ መወሰን አይኖርብንም። ከዚያም በታኅሣሥ ወር የዘመቻውን ጽሑፍ ስናበረክት እነዚህን ነጥቦች እንዴት ተግባራዊ ልናደርጋቸው እንደምንችል አብራራ። ምናልባትም በጥር 2005 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይ ካሉት የናሙና አቀራረቦች ወይም ለአገልግሎት ክልሉ ይበልጥ ተስማሚ የሆነ ሌላ መግቢያ ተጠቅመህ ማስረዳት ትችላለህ። ከዚያም አንድ ወይም ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።

መዝሙር 50 (123) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ታኅሣሥ 5 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 17 (38)

10 ደቂቃ:-የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ:-ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

20 ደቂቃ:-“አገልግሎታችን ምን ውጤት ያስገኛል።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንቀጽ 5ን ስትወያዩ ከየካቲት 15, 2004 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 32 ላይ አንዳንድ ሐሳቦችን አክለህ አቅርብ።

መዝሙር 9 (26) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ