የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/06 ገጽ 8
  • እንደ ከዋክብት የሚያበሩ ወጣቶች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • እንደ ከዋክብት የሚያበሩ ወጣቶች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘ብርሃን አብሪ መሆን’
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • ብርሃናችን ሳያቋርጥ እንዲበራ ማድረግ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • “ብርሃናችሁ ይብራ”
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
  • ይሖዋ እንዲከበር ‘ብርሃናችሁ ይብራ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
km 1/06 ገጽ 8

እንደ ከዋክብት የሚያበሩ ወጣቶች

1. መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያኖች ከሌሎች ለየት ብለው እንደሚታዩ የገለጸው እንዴት ነው? እነዚህ ቃላት በዛሬው ጊዜ በሚገኙት ወጣት ክርስቲያኖች ላይ የሚሠሩትስ እንዴት ነው?

1 ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ” ብሏቸው ነበር። (ማቴ. 5:14, 16) በተራራ ላይ ያለ ከተማ የፀሐይ ብርሃን ሲያርፍበት እንደሚያንጸባርቅ ሁሉ እነርሱም ከሌሎች ለየት ብለው ይታያሉ። በዛሬው ጊዜ የሚገኙ ብዙ ወጣት ክርስቲያኖች ጥሩ ጠባይ በማሳየትና ቅንዓት የተሞላበት ምሥክርነት በመስጠት ‘በዓለም ሁሉ እንደ ከዋክብት ያበራሉ።’​—⁠ፊልጵ. 2:15፤ ሚል. 3:18

2. ለአስተማሪዎቻችሁና ለክፍል ጓደኞቻችሁ ምሥክርነት ለመስጠት የሚያስችሏችሁ አንዳንድ መንገዶች ምንድን ናቸው?

2 በትምህርት ቤት:- በትምህርት ቤት ምሥክርነት መስጠት የምትችሉት እንዴት ነው? አንዳንድ ወጣቶች በክፍል ውስጥ አደገኛ ዕጾችንና ዝግመተ ለውጥን የመሳሰሉ ርዕሰ ጉዳዮች ሲነሱ አጋጣሚውን ምሥክርነት ለመስጠት ይጠቀሙበታል። አንዲት እህት ስለ ሽብርተኝነት ጽሑፍ እንድታዘጋጅ የቤት ሥራ ሲሰጣት አጋጣሚውን በመጠቀም የአምላክ መንግሥት ለሰው ልጆች የተሰጠ እርግጠኛ ተስፋ መሆኑን መሥክራለች። አስተማሪዋ በደንብ ታስቦበት በቀረበው የእህት ሪፖርት ስለተደነቀች ተጨማሪ ውይይት ለማድረግ ፈቃደኛ ሆናለች።

3. መልካም ጠባይ በማሳየት ብርሃናችሁን ማብራት የምትችሉት እንዴት ነው?

3 ጠባያችሁ፣ አለባበሳችሁና አጋጌጣችሁ እንደ ከዋክብት እንድታበሩ የሚያስችላችሁ ሌላው መንገድ ነው። (1 ቆ⁠ሮ. 4:9፤ 1 ጢ⁠ሞ. 2:9) ተማሪዎችም ሆኑ አስተማሪዎች ከሌሎች የተለየ ባሕርይ እንዳላችሁ ሲመለከቱ ከመካከላቸው አንዳንዶቹ በመልካም ጠባያችሁ አማካኝነት ወደ እውነት ተስበው የመጽሐፍ ቅዱስን እውነቶች እንድታካፍሏቸው መንገድ ሊከፍቱላችሁ ይችላሉ። (1 ጴ⁠ጥ. 2:12፤ 3:1, 2) አምላካዊ ባሕርይ ማሳየት ቀላል ባይሆንም እንኳ ይሖዋ አትረፍርፎ ይባርካችኋል። (1 ጴ⁠ጥ. 3:16, 17፤ 4:14) ሰዎች ለምሥራቹ ፍላጎት እንዲያድርባቸው ለማድረግ ከፈለጋችሁ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ አንድ ጽሑፍ በእረፍት ሰዓታችሁ ማንበብ አሊያም ሌሎች በሚያዩት ቦታ ላይ ማስቀመጥ ትችላላችሁ።

4. ትምህርት ቤት ውስጥ መስበክ የሚያስገኛቸው አንዳንድ ጥቅሞች ምንድን ናቸው?

4 ብርሃናችሁን በትምህርት ቤት ማብራታችሁ እምነታችሁን ከማጠንከሩም በላይ ይሖዋን በማገልገላችሁ ተገቢ ኩራት እንዲሰማችሁ ይረዳችኋል። (ኤር. 9:24) በተመሳሳይም ጥበቃ ይሆንላችኋል። አንዲት እህት እንዲህ ብላለች:- “ስለ እምነቴ መናገሬ ካስገኘልኝ ጥቅሞች አንዱ ተማሪዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚጋጩ ነገሮችን እንድፈጽም ተጽዕኖ አያደርጉብኝም።”

5. (ሀ) አንዳንድ ወጣቶች አገልግሎታቸውን ያሰፉት እንዴት ነው? (ለ) ምን መንፈሳዊ ግቦች አውጥተሃል?

5 አገልግሎታችሁን አስፉ:- ብዙ ወጣቶች እንደ ከዋክብት የሚያበሩበት ሌላው መንገድ አገልግሎታቸውን በማስፋት ነው። አንድ ወንድም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት ቦታ ሄዶ ለማገልገል ወሰነ። በሄደበት ቦታ አንድ ሽማግሌ ብቻ ያለው አነስተኛ ጉባኤ ነበር። “በጣም አስደሳች ሕይወት እየመራሁ ነው” በማለት ለአንድ ጓደኛው ጽፎለታል። አክሎም “አገልግሎት መንፈስን የሚያድስ ሆኖልኛል! ሰዎቹ የምትነግራቸውን ሁሉ ለማዳመጥ ፈቃደኞች ስለሆኑ በእያንዳንዱ ቤት ለ20 ደቂቃ ያህል እንቆያለን። እያንዳንዱ ወጣት እንዲህ ቢያደርግና እንደኔ ዓይነት ስሜት ቢሰማው ደስ ይለኛል። ባለን ነገር ሁሉ ይሖዋን ከማገልገል የበለጠ ምንም ነገር የለም” ብሏል።

6. በጉባኤህ ውስጥ በሚገኙት ወጣቶች እንድትኮራ የሚያደርግህ ነገር ምንድን ነው?

6 በዓለም ላይ እንደ ከዋክብት የምታበሩ እናንት ወጣቶች እንኮራባችኋለን! (1 ተ⁠ሰ. 2:20) በፍጹም ልባችሁ፣ ነፍሳችሁ፣ ሐሳባችሁና ኃይላችሁ ይሖዋን ስታገለግሉ “በዚህ ዘመን . . . መቶ ዕጥፍ . . . በሚመጣውም ዓለም የዘላለም ሕይወት” ታገኛላችሁ።​—⁠ማር. 10:29, 30፤ 12:30

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ