ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
የካቲት 27, 2006 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ በቃል መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከጥር 2 እስከ የካቲት 27, 2006 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል። [ማሳሰቢያ:- ከጥያቄው ቀጥሎ መልሱ የሚገኝበት ጽሑፍ ካልተጠቀሰ መልሱን ለማግኘት በግልህ ምርምር ማድረግ ይኖርብሃል።—የአገልግሎት ትምህርት ቤት ገጽ 36-37ን ተመልከት።]
የንግግር ባሕርይ
1. ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ‘ለእግዚአብሔር የምሥጋና መስዋዕት እንድናቀርብና ለስሙ እንድንመሰክር’ የሚረዳን በየትኞቹ መንገዶች ነው? (ዕብ. 13:15 የ1954 ትርጉም ) [be ገጽ 5 አን. 3 እስከ ገጽ 6 አን. 1]
2. ጥርት አድርጎ ለማንበብ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ያለብን ለምንድን ነው? [be ገጽ 83 አን. 1 እስከ ገጽ 84 አን. 1]
3. በምናስተምርበትም ሆነ በምንናገርበት ወቅት አጥርቶ መናገር አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? [be ገጽ 86 አን. 1-6]
4. የቃላትን ትክክለኛ አጠራር መጠቀም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ግምት ውስጥ ልናስገባቸው የሚያስፈልጉ ጉዳዮችስ ምንድን ናቸው? [be ገጽ 89 አን. 1 እስከ ገጽ 90 አን. 2፣ ሣጥን]
5. በምንናገርበት ወቅት ቅልጥፍና እንዲኖረን ሊረዱን የሚችሉ አንዳንድ ነጥቦች ምንድን ናቸው? [be ገጽ 94 አን. 4-5፣ ሣጥን]
ክፍል ቁጥር 1
6. 2 ዜና መዋዕል 36:17-23 የመጽሐፍ ቅዱስን ትንቢት እውነተኝነት የሚያረጋግጠው እንዴት ነው? [bsi ገጽ 4 አን. 35]
7. በ537 ከክርስቶስ ልደት በፊት አይሁዳውያን ወደ ትውልድ አገራቸው ተመልሰው የይሖዋን ቤት መገንባት እንዲችሉ ያስቻሏቸው የትኞቹ በተከታታይ የተፈጸሙ ክስተቶች ናቸው? [bsi ገጽ 5 አን. 1-3]
8. የዕዝራ መጽሐፍ ይሖዋ እውነተኛ አምላክ መሆኑን የሚያረጋግጠውና በእርሱ ላይ እምነት እንድናሳድር የሚያደርገን እንዴት ነው? [bsi ገጽ 6ና 7 አን. 14, 18]
9. ‘የንጉሥ አርጤክስስ ዘመነ መንግሥት ሃያኛው ዓመት’ በመጽሐፍ ቅዱስ የዘመን ስሌት ውስጥ ያለው ጠቀሜታ ምንድን ነው? (ነህ. 2:1, 5, 6, 11, 17, 18) [bsi ገጽ 7ና 8 አን. 2, 5]
10. ነህምያ ዛሬ ላሉት የአምላክ አገልጋዮች ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው እንዴት ነው? [bsi ገጽ 8 አን. 16-17]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. ከስደት የተመለሱት አይሁዳውያን፣ ከይሖዋ መልስ ለማግኘት የሚያገለግሉት ኡሪምና ቱሚም ነበሯቸው? (ዕዝራ 2:61-63)
12. በባቢሎን ይኖሩ የነበሩ ብዙ አይሁዳውያን ከዕዝራ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም መመለስ ያልፈለጉት ለምንድን ነው? (ዕዝራ 7:28 እስከ 8:20)
13. ቅጥሩን ዳግም የመገንባቱ ሥራ እንዴት በአንድ እጅ ብቻ ሊከናወን ይችላል? (ነህ. 4:17, 18)
14. አብዛኛውን ጊዜ ምስጢራዊ ደብዳቤዎች የሚላኩት ታሽገው ሆነው ሳለ ሰንባላጥ ለነህምያ “ያልታሸገ ደብዳቤ” የላከው ለምንድን ነው? (ነህ. 6:5)
15. ነህምያ ቀደም ብሎ በገዢዎቹና በመኳንንቱ ላይ እንዳደረገው ሁሉ ወደ ኃጢአት የተመለሱትን አይሁዳውያን ‘ከመገሠጽም’ አልፎ ምን ሌሎች እርምጃዎች ወስዷል? (ነህ. 13:25, 28)