ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች የካቲት:- ወደ ይሖዋ ቅረብ፤ መጋቢት:- ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለው አዲስ መጽሐፍ የሚበረከት ሲሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመርም ልዩ ጥረት አድርጉ። ሚያዝያ:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች ይበረከታሉ። ተመላልሶ መጠየቅ በምታደርጉበት ወቅት ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ አበርክቱ።
◼ የሚያዝያ ወር አምስት ቅዳሜና እሁዶች ስለሚኖሩት ረዳት አቅኚ ሆኖ ለማገልገል አመቺ ነው።
◼ በመታሰቢያው በዓል ሰሞን የሚቀርበው የ2006 ልዩ የሕዝብ ንግግር ርዕስ “አምላክ በአሁኑ ጊዜም ምድርን እየተቆጣጠረ ነው?” የሚል ይሆናል። ይህ ልዩ የሕዝብ ንግግር እሁድ ሚያዝያ 30 ይቀርባል። በዚያ ሳምንት የወረዳ የበላይ ተመልካች ጉብኝት ወይም የወረዳ አሊያም የልዩ ስብሰባ ያላቸው ጉባኤዎች ልዩ የሕዝብ ንግግሩን በቀጣዩ ሳምንት ማቅረብ ይችላሉ። በየትኛውም ጉባኤ ልዩ የሕዝብ ንግግሩ ከሚያዝያ 30, 2006 በፊት መቅረብ አይኖርበትም።
◼ መጋቢት 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ አሊያም እርሱ የወከለው ሌላ ወንድም የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። ለእድሳት ወይም ለግንባታ ተብሎ ለብቻ የሚቀመጥ የባንክ ሒሳብ ካለ ይህንንም ለመመርመር ዝግጅት መደረግ አለበት። የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከቀረበ በኋላ የሒሳብ ምርመራው ውጤት ለጉባኤው መነበብ አለበት።
◼ ጸሐፊውና የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሁሉንም የዘወትር አቅኚዎች የአገልግሎት እንቅስቃሴ መመርመር ይኖርባቸዋል። የሰዓት ግባቸው ላይ መድረስ ያልቻሉ አቅኚዎች ካሉ ሽማግሌዎቹ እርዳታ መስጠት የሚቻልበትን መንገድ መቀየስ ይኖርባቸዋል። ተጨማሪ ሐሳብ ለማግኘት ዓመታዊ S-201 ደብዳቤዎችን ተመልከቱ።