የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/06 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
  • ንዑስ ርዕሶች
  • የካቲት 13 የሚጀምር ሳምንት
  • የካቲት 20 የሚጀምር ሳምንት
  • የካቲት 27 የሚጀምር ሳምንት
  • መጋቢት 6 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
km 2/06 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

የካቲት 13 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 80 (180)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የታኅሣሥ 1 መጠ​በቂያ ግንብ እና የታኅሣሥ 2005 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ አስፋፊው ሰው በሚበዛባቸው አካባቢዎች ሲመሠክር የሚያሳይ ይሁን።

10 ደቂቃ:- ከይሖዋ ድርጅት ጋር እኩል እየተራመድህ ነው? የይሖዋን ፈቃድ ለማ​ድረግ የተደራጀ ሕዝብ ከሚለው መጽሐፍ ገጽ 7-10 ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር።

25 ደቂቃ:- “ሰዎች ትኩረታቸውን ‘በዓለም ብርሃን’ ላይ እንዲያደርጉ እርዷቸው።” በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ። አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ረዳት አቅኚ ሆነው እያገለገሉ ያሉትን አስፋፊዎች ስም ዝርዝር ተናገር። ተጨማሪ የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎችን ለማካሄድ የተደረገውን ዝግጅት ግለጽ። ከየካቲት 2005 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ገጽ 5 ላይ ካለው የረዳት አቅኚነት የናሙና ፕሮግራም ላይ ተጨማሪ ሐሳብ ስጥ።

መዝሙር 74 (168) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

የካቲት 20 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 41 (89)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ:- “ለመስበክ የሚያስችሉ አጋጣሚዎችን ፍጠሩ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኝ አንድ አስፋፊ (እህትም ልትሆን ትችላለች) ምሥክርነት ለመስጠት የሚያስችለውን አጋጣሚ እንዴት እንደፈጠረ ሐሳብ እንዲሰጥ ጋብዝ።

20 ደቂቃ:- “የቅርብ ረዳት” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በሽማግሌ የሚቀርብ። ከኅዳር 1998 እና ከኅዳር 2000 የመንግሥት አገልግሎታችን የጥያቄ ሣጥኖች ላይ ጥቂት ሐሳቦችን አክለህ አቅርብ።

መዝሙር 35 (79) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

የካቲት 27 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 93 (211)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። አስፋፊዎች የየካቲት ወር ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በገጽ 8 ላይ የሚገኘውን ሐሳብ ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆነ ሌላ አቀራረብ በመጠቀም የታኅሣሥ 15 መጠበቂያ ግንብ ሲበረከት የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።

10 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

25 ደቂቃ:- የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ ማበርከት የሚቻልበት መንገድ። በመጋቢት ወር አዲሱን መጽሐፍ እናበረክታለን። በጥር 2006 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ውስጥ ከገጽ 3-6 ያሉትን የመግቢያ ሐሳቦች ከልስ፤ ከዚያም ለአገልግሎት ክልሉ ይበልጥ ተስማሚ የሆኑት መግቢያዎች በሠርቶ ማሳያ እንዲቀርቡ አድርግ። ይህን መጽሐፍ ተጠቅመው ጥሩ ውጤት ያገኙ በተለይ ደግሞ ጥናት ያስጀመሩ ካሉ ያገኙትን ተሞክሮ እንዲናገሩ ጋብዝ።

መዝሙር 63 (148) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

መጋቢት 6 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 94 (212)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ትራክቶች ለመያዝ አመቺ ከመሆናቸውም ሌላ ትኩረት የሚስቡ ስለሆኑ ከቤት ወደ ቤት፣ ሕዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች እንዲሁም መደበኛ ባልሆነ መንገድ ስንሰብክ ውይይት ለመጀመር ተስማሚ ናቸው። መከራና ሥቃይ ሁሉ በቅርቡ ይወገዳል! የተባለውን አዲሱን ትራክት በመጠቀም እንዴት ውይይት መጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ አንድ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። በትራክቱ ገጽ 2 ላይ ሐሳባቸው በቀጥታ ከተቀመጡት ጥቅሶች መካከል አንዱን አብራራ።

15 ደቂቃ:- “ዝግጅት በማድረግ ለሰዎች ልባዊ አሳቢነት አሳዩ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ሁለት አስፋፊዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ ለማበርከት ዝግጅት ሲያደርጉ የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ከጥር 2006 የመንግሥት ኣገልግሎታችን አባሪ ላይ መግቢያ ከመረጡ በኋላ እንዴት በራሳቸው አባባል መናገር እንደሚችሉና ከአገልግሎት ክልሉ አንጻር ምን ማስተካከያ እንደሚያደርጉበት ይወያያሉ። ከዚያም አቀራረባቸውን ለመለማመድ ሲዘጋጁ ሠርቶ ማሳያው ይደመደማል።

20 ደቂቃ:- “የቪዲዮ ፊልሞቻችንን ተጠቅማችሁ አስተምሩ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በክፍሉ ውስጥ የተጠቀሱትን የቪዲዮ ፊልሞች ስትወያዩባቸው የቪዲዩ ካሴቱን የውጪ ሽፋን አሳያቸው። እንዲሁም ይዘቱን በተመለከተ የተሰጠውን መግለጫ አንብብላቸው። የቪዲዮ ፊልሞችን ለአገልግሎት ተጠቅመው የሚያውቁ አድማጮች ካሉ ተሞክሯቸውን እንዲናገሩ ጠይቅ።​—⁠የ1997 የዓመት መጽሐፍ ገጽ 54ን እንዲሁም የ1995 የዓመት መጽሐፍ ገጽ 50-51ን ተመልከት።

መዝሙር 29 (62) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ