የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 5/06 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ግንቦት 8 የሚጀምር ሳምንት
  • ግንቦት 15 የሚጀምር ሳምንት
  • ግንቦት 22 የሚጀምር ሳምንት
  • ግንቦት 29 የሚጀምር ሳምንት
  • ሰኔ 5 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
km 5/06 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ግንቦት 8 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 54 (132)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የመጋቢት 15 መጠበቂያ ግንብ እና የሚያዝያ 2006 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ አስፋፊው፣ የመጋቢት 15 መጠበቂያ ግንብ በሆነ ምክንያት ላልደረሰው የመጽሔት ደንበኛው የመጋቢት 15 እና የሚያዝያ 1 መጠበቂያ ግንብ እንዲሁም የሚያዝያ 2006 ንቁ! መጽሔቶችን አንድ ላይ ሲያበረክት የሚያሳይ ይሁን። ሦስቱን መጽሔቶች በሚያበረክትበት ወቅት የሚያስተዋውቀው አንዱን መጽሔት ብቻ ነው። አስፋፊዎች ለመጽሔት ደንበኞቻቸው በወር አንድ ወይም ሁለት ጊዜ መጽሔት ሊያደርሱላቸው ይገባል።

20 ደቂቃ:- “ያለማቋረጥ ‘ይከተለኝ’።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። የግል ሕይወቱን ለማሻሻል ከመሯሯጥ ይልቅ ኑሮውን ቀላል በማድረግ መንግሥቱን ለማስቀደምና ሌሎችን ለመርዳት ጥረት ለሚያደርግ ምሳሌ ሊሆን ለሚችል አስፋፊ አጭር ቃለ ምልልስ አድርግ። እንዲህ በማድረጉ ያገኘውን ጥቅም ጎላ አድርገህ ግለጽ።

15 ደቂቃ:- ከጉባኤው የተገኙ ተሞክሮዎች። አስፋፊዎች በመጋቢትና በሚያዝያ በስብከቱ ሥራ ሲካፈሉ ያገኙትን ውጤት እንዲናገሩ አድርግ። በተለይ ጥናት ያስጀመሩ እንዲሁም አዲሶች በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኙ መርዳት የቻሉ ካሉ ተሞክሯቸውን እንዲናገሩ ጋብዝ። አንድ ወይም ሁለት ተሞክሮዎች በሠርቶ ማሳያ እንዲቀርቡ አድርግ።

መዝሙር 91 (207) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ግንቦት 15 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 3 (6)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ግንቦት 29 በሚጀምር ሳምንት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለሚደረገው ውይይት ሁሉም ኖህ—አካሄዱን ከአምላክ ጋር አደረገ የተባለውን የቪዲዮ ፊልም አይተው እንዲመጡ አበረታታ።

15 ደቂቃ:- በክርስቶስ አመራር ሥር ሆኖ በአንድነት ማገልገል። የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ገጽ 13-15 ላይ በሚገኘው “የክርስቶስን ሚና መቀበል ሲባል ምን ማለት ነው?” በሚለው ንዑስ ርዕስ ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር።

20 ደቂቃ:- ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ተመልሶ ማነጋገር አጣዳፊ ነው። በሰኔ 1995 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 8 ላይ ተመሥርቶ በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በንግግር የሚቀርብ።

መዝሙር 55 (133) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ግንቦት 22 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 39 (86)

12 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የሚያዝያ 1 እና 15 መጠበቂያ ግንብ መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ሠርቶ ማሳያዎቹ የአንድ ቤተሰብ አባላት መጽሔቶቹን ለማበርከት ሲለማመዱ የሚያሳዩ ይሁኑ።

15 ደቂቃ:- “ጨዋና ሰው አክባሪ በመሆን ለሰዎች ልባዊ አሳቢነት አሳዩ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።

18 ደቂቃ:- ንጹሕና ሥርዓታማ አለባበስ። የአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 131-133 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። አለባበሳችንንና አበጣጠራችንን በተመለከተ ልብ ልንላቸው የሚገቡንን አምስት መሠረታዊ ሥርዓቶች ተናገር። ይህን ሐሳብ በጉባኤ ስብሰባዎች ስንገኝ ሊኖረን የሚገባው ትክክለኛ አለባበስ ምን ዓይነት እንደሆነ ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን በዘዴ ለማስረዳት ልንጠቀምበት እንደምንችል ጥቀስ።

መዝሙር 96 (215) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ግንቦት 29 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 18 (42)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የግንቦት ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው።

10 ደቂቃ:- በሰኔ ወር የቤተሰብ ደስታ የተባለውን መጽሐፍ አበርክቱ። በየካቲት 1999 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 8 ላይ በሚገኘው “በሁሉም የዕድሜ ክልል ለሚገኙ ሰዎች የቤተሰብ ደስታ የተባለውን መጽሐፍ አበርክቱ” በሚለው ርዕስ ሥር የወጡትን የመግቢያ ሐሳቦች አሊያም ለአገልግሎት ክልላችሁ ተስማሚ የሆነ ሌላ መግቢያ በመጠቀም የቤተሰብ ደስታ የተባለውን መጽሐፍ እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አስፋፊዎች መጽሐፉን በአገልግሎት ላይ ወይም በቤተሰባቸው ውስጥ በሚጠቀሙበት ወቅት ያገኙትን ተሞክሮ እንዲናገሩ አድርግ።

25 ደቂቃ:- “በሁሉም የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎች ሊከተሉት የሚገባ አርዓያ።” ከአንድ ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ ኖኅ የተሰኘውን የቪዲዮ ፊልም ለመከለስ እንዲያገለግሉ ታስበው የተዘጋጁትን በሁለተኛው አንቀጽ ውስጥ ያሉትን ጥያቄዎች በመጠቀም ከአድማጮች ጋር ተወያይ። ከዚያም ቤተሰቦች በዲቪዲው ውስጥ በሚገኘው “ለርኒንግ አክቲቪቲስ” በሚለው ሥር ምርምር ለማድረግ ከቀረቡት ጥያቄዎች ያገኙትን ጥቅም ጠይቃቸው። በመጨረሻም በሦስተኛው አንቀጽ ውስጥ በሚገኘው ጥያቄ እንዲሁም በጥቅሶቹ ላይ ተወያዩባቸው።

መዝሙር 81 (181) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሰኔ 5 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 56 (135)

7 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

18 ደቂቃ:- “ክርስቲያኖች ስለ ግርዘት ያላቸው አመለካከት።” ጊዜ በፈቀደልህ መጠን ከጥቅምት 1993 ንቁ! መጽሔት ገጽ 12-15 ላይ ተጨማሪ ነጥቦችን ጥቀስ።

20 ደቂቃ:- ተመላልሶ መጠየቅ በማድረግ ረገድ ስኬታማ መሆን የሚቻልበት መንገድ። በኅዳር 15, 2003 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 16 ላይ በሚገኘው ሣጥን ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። በሣጥኑ ውስጥ ያሉትን ሰባት ነጥቦች ተናገር። እንዲሁም አድማጮች እነዚህን ነጥቦች በአገልግሎት ክልላቸው ውስጥ እንዴት ሊሠሩባቸው እንደሚችሉ ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ። አስፋፊዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ግብ ይዘው ጽሑፍ ለወሰዱ ወይም ፍላጎት ላሳዩ ሰዎች ተመላልሶ መጠየቅ እንዲያደርጉ አበረታታ። በጥር 2006 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 6 ላይ ከቀረቡት የመግቢያ ሐሳቦች መካከል አንዱን በመጠቀም ተመላልሶ መጠየቅ በሚደረግበት ጊዜ ጥናት እንዴት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።

መዝሙር 27 (57) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ