ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ግንቦት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ተመላልሶ መጠየቅ በምታደርጉበት ወቅት ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ አበርክቱ። ሰኔ:- ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? ሐምሌና ነሐሴ:- ብሮሹሮች።
◼ የሐምሌ ወር አምስት ቅዳሜና እሁዶች ስለሚኖሩት ረዳት አቅኚ ሆኖ ለማገልገል አመቺ ነው።
◼ ሰኔ 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ አሊያም እርሱ የወከለው ሌላ ወንድም የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። ለእድሳት ወይም ለግንባታ ተብሎ ለብቻ የሚቀመጥ የባንክ ሒሳብ ካለ ይህንንም ለመመርመር ዝግጅት መደረግ አለበት። የሒሳብ ምርመራው ውጤት የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከቀረበ በኋላ ለጉባኤው መነበብ አለበት።
◼ አንዳንድ ጊዜ ልትጠቀሙባቸው የምትችሏቸው ብዛት ያላቸው ጽሑፎች አሉን። ከእነርሱም መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል:- የአዲሲቱ ዓለም የግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎች ትርጉም በአረብኛ፤ በደስታ ኑር ብሮሹር በሶማሊኛ፤ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? እና ሌሎች ብሮሹሮች በሂንዲ፤ እውቀት እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በኑዌር፤ እውቀት፣ ማን ካይንድስ ሰርች ፎር ጎድ፣ የቤተሰብ ደስታ በስፓንኛ፤ ክሪኤሽን እና ሌሎች ጽሑፎች በቻይንኛ። ጽሑፎቹን ስትፈልጉ ማዘዝ ትችላላችሁ።
◼ እንግሊዝኛ ማንበብ ለሚችሉ ማየት የተሳናቸው ሰዎች የምናበረክታቸው በብሬይል የተዘጋጁ አንዳንድ ጽሑፎች አሉን። ዝርዝሩን ለማወቅ መጠየቅ ትችላላችሁ።
◼ አዳዲስ አስፋፊዎች በእጃችን ከሚገኙት ከሚከተሉት ጽሑፎች መካከል የሚፈልጉትን ለግል ቤተ መጻሕፍታቸው እንዲያዙ እናበረታታቸዋለን። የ2003 የዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ)፣ የይሖዋ ምሥክሮች በኢትዮጵያ—ነፃነት አፍቃሪዎች (በአማርኛ የተዘጋጀ ታሪካዊ ዘገባ) እንዲሁም ትምህርት ቤትና የይሖዋ ምሥክሮች (አማርኛ)። ተማሪዎች ትምህርት ቤትና የይሖዋ ምሥክሮች የተባለው ብሮሹር የግል ቅጂ እንዲኖራቸው እናበረታታቸዋለን። የጉባኤ ጸሐፊዎች አስፋፊዎቹ የፈለጓቸውን ጽሑፎች ማዘዝ ይችላሉ።
◼ ለዘወትር አቅኚነት የሚቀርብ ማመልከቻ፣ አስፋፊው አቅኚነት መጀመር ከሚፈልግበት ቀን ቢያንስ ከ30 ቀናት በፊት ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው መላኩ አስፈላጊ ነው። የጉባኤው ጸሐፊ የማመልከቻ ቅጾቹ በሚገባ መሞላታቸውን ማረጋገጥ ይኖርበታል። አመልካቾች የተጠመቁበትን ትክክለኛ ቀን ማስታወስ ካልቻሉ ቀኑን ገምተው ለማወቅ መጣርና ይህን ቀን መዝግበው መያዝ ይኖርባቸዋል። የጉባኤው ጸሐፊ ይህን ቀን የጉባኤ አስፋፊ ካርድ (S-21) ላይ ሊመዘግበው ይገባል።