ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ሰኔ 26, 2006 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ በቃል መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከግንቦት 1 እስከ ሰኔ 26, 2006 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል። [ማሳሰቢያ:- ከጥያቄው ቀጥሎ መልሱ የሚገኝበት ጽሑፍ ካልተጠቀሰ መልሱን ለማግኘት በግልህ ምርምር ማድረግ ይኖርብሃል።—የአገልግሎት ትምህርት ቤት ገጽ 36-37ን ተመልከት።
የንግግር ባሕርይ
1. ድምፅን መለዋወጥ ሲባል ምን ማለት ነው? አስፈላጊ የሆነውስ ለምንድን ነው? [be ገጽ 111፣ ሣጥኖች]
2. ንግግር ስንሰጥ ፍጥነታችንን መለዋወጥ የምንችለው እንዴት ነው? [be ገጽ 112 አን. 3 እስከ ገጽ 113 አን. 1፣ ሣጥን]
3. ንግግራችንን በጋለ ስሜት ለማቅረብ ምን ሊረዳን ይችላል? በጋለ ስሜት መናገር አስፈላጊ የሆነውስ ለምንድን ነው? [be ገጽ 115 አን. 1 እስከ ገጽ 116 አን. 2፣ ሣጥኖች]
4. ሌሎችን ስናስተምር ወዳጃዊ ስሜት ማሳየት ያለብን ለምንድን ነው? ይህን ለማድረግ ምን ሊረዳን ይችላል? [be ገጽ 118 አን. 2 እስከ ገጽ 119 አን. 5]
5. ሐሳብን ለመግለጽ አካላዊ መግለጫዎች አስፈላጊ የሆኑት ለምን እንደሆነ አብራራ። (ማቴ. 12:48, 49) [be ገጽ 121፣ ሣጥኖች]
ክፍል ቁጥር 1
6. የኢዮብ መጽሐፍ ይሖዋን ከፍ ከፍ የሚያደርገውና እርሱ ያወጣቸውን ለሕይወት መመሪያ የሚሆኑ የጽድቅ መሥፈርቶች የሚያጎላው እንዴት ነው? [bsi ገጽ 13 አን. 39, 41]
7. የመዝሙርን መጽሐፍ ትክክለኛነት የሚያረጋግጥልን ምንድን ነው? [bsi ገጽ 16, 17 አን. 10, 11]
8. ምሳሌ 13:16 አስተዋይ ሰው ሲል ምን ማለቱ ነው? አስረዳ። [w04 7/15 ገጽ 28 አን. 3-4]
9. መንፈስ ቅዱስ ረዳት የሚሆንልን እንዴት ነው? ይህን ማወቃችንስ ምን እንድናደርግ ያበረታታናል? (ዮሐ. 14:25, 26) [be ገጽ 19 አን. 1-2]
10. በማቴዎስ 16:28 ላይ በተገለጸው መሠረት ኢየሱስ የመጣው እንዴት ነው? በዚህ ጥቅስ ላይ ስለ የትኛው ‘መምጣት’ መናገሩ ነበር? [w04 3/1 ገጽ 16 ሣጥን]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. በኢዮብ 42:1-6 ላይ ኢዮብ ለይሖዋ ከሰጠው መልስ ምን እንማራለን?
12. ብሔራት የሚያውጠነጥኑት “ከንቱ ነገር” ምንድን ነው? (መዝ. 2:1, 2)
13. የተናዱት መሠረቶች የትኞቹ ናቸው? (መዝ. 11:3)
14. ዳዊት ጠላቶቹ በዐይናቸው እንዳይጣቀሱበት ሲለምን ምን ማለቱ ነበር? (መዝ. 35:19)
15. አለፍጽምና እና ይህ ሥርዓት የሚያመጡብንን የተለያዩ መከራዎች መቋቋም እንድንችል ከመዝሙር 40 ምን ማጽናኛ ማግኘት እንችላለን? (መዝ. 40:1, 2, 5, 12)