ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ሰኔ:- ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? ሐምሌና ነሐሴ:- ብሮሹሮች፤ መስከረም:- የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት።
◼ በመስከረም ወር የአገልግሎት ስብሰባ ላይ የወጣቶች ጥያቄ—እውነተኛ ጓደኞች ማፍራት የምችለው እንዴት ነው? የተሰኘውን የቪዲዮ ፊልም እንከልሳለን። የቪዲዮ ክሩን ማግኘት የምትፈልጉ ከሆነ በተቻለ ፍጥነት በጉባኤያችሁ በኩል ማዘዝ ይኖርባችኋል።
◼ የሐምሌ ወር አምስት ቅዳሜና እሁዶች ስለሚኖሩት ረዳት አቅኚ ሆኖ ለማገልገል አመቺ ነው።