የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 7/06 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ሐምሌ 10 የሚጀምር ሳምንት
  • ሐምሌ 17 የሚጀምር ሳምንት
  • ሐምሌ 24 የሚጀምር ሳምንት
  • ሐምሌ 31 የሚጀምር ሳምንት
  • ነሐሴ 7 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
km 7/06 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ሐምሌ 10 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 2 (4)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የሰኔ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የሰኔ 2006 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ ውይይቱን ለማስቆም “እኛ ክርስቲያኖች ነን” ለሚል ሰው ምን መልስ መስጠት እንደሚቻል የሚያሳይ ይሁን።—ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 19ን ተመልከት።

15 ደቂቃ:- ጉባኤው የተደራጀውና የሚመራው እንዴት ነው? የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 4 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ።

20 ደቂቃ:- “ወደር የለሽ ለሆኑት የይሖዋ ባሕርያት አድናቆት እንዲያሳዩ እርዷቸው።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 1 መጨረሻ ላይ የክለሳ ሣጥኑ በያዘው ነጥብ ላይ እንዲያሰላስሉ ለመርዳት ጥያቄዎችን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።

መዝሙር 84 (190) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሐምሌ 17 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 87 (195)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በነሐሴ 15, 2000 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 32 ላይ ያለውን ሐሳብ በአጭሩ አቅርብ። እረፍት ላይ ወይም ከዘወትር ልማዳችን በተለየ ሁኔታ ውስጥ በምንሆንበት ጊዜም እንኳ የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባችን እንዳይቋረጥ ማድረጋችን ያለውን ጥቅም አጉላ።

15 ደቂቃ:- ፍቅርና ትሕትና—ለአገልግሎት የሚረዱ ወሳኝ ባሕርያት። በነሐሴ 15, 2002 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 18-20 አንቀጽ 13-20 ላይ ተመሥርቶ በንግግር የሚቀርብ።

20 ደቂቃ:- “‘ደስተኛ የሆነውን አምላካችንን’ ይሖዋን ምሰሉ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ወንድሞች በአገልግሎት ክልላቸው በሚሰብኩበት ጊዜ የደስተኝነት ስሜታቸውንም ሆነ አዎንታዊ አመለካከታቸውን ጠብቀው እንዲቆዩ የረዳቸው ነገር ምን እንደሆነ እንዲናገሩ አድርግ።

መዝሙር 11 (29) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሐምሌ 24 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 98 (220)

12 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የሰኔ 15 መጠበቂያ ግንብ እና የሰኔ 2006 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ከእያንዳንዱ ሠርቶ ማሳያ በኋላ አስፋፊው የቤቱን ባለቤት ፍላጎት ለመቀስቀስ የተጠቀመበትን የመግቢያ ሐሳብ ደግመህ ተናገር።

20 ደቂቃ:- “‘መዳናችን ቀርቧል’—የ2006 የይሖዋ ምሥክሮች አውራጃ ስብሰባ።” በጉባኤው ጸሐፊ የሚቀርብ። አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንቀጽ 1ን ከተወያያችሁበት በኋላ ጉባኤው የተመደበበትን የአውራጃ ስብሰባ ፕሮግራም ተናገር። ሁሉም ለአውራጃ ስብሰባው ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አበረታታ።

13 ደቂቃ:- ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። (1 ቆሮ. 15:58) ይሖዋን ለረጅም ዓመታት በታማኝነት ላገለገሉ ሁለት ወይም ሦስት አስፋፊዎች ወይም አቅኚዎች ቃለ ምልልስ አድርግላቸው። እውነትን የሰሙት እንዴት ነው? አገልግሎት በጀመሩበት ጊዜ የስብከቱ ሥራ ምን ይመስል ነበር? ምን ችግሮችስ አጋጥመዋቸዋል? በእውነተኛው አምልኮ ውስጥ ጸንተው በመቆማቸው ምን በረከቶችን አግኝተዋል?

መዝሙር 14 (34) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሐምሌ 31 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 51 (127)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የሐምሌ ወር ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በነሐሴ ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ተናገር።

15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

20 ደቂቃ:- “ጥሩ ልማዶችን በማዳበር የተትረፈረፈ በረከት እጨዱ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አድማጮች ጥሩ መንፈሳዊ ልማድ ለማዳበርና ጠብቀው ለማቆየት ምን ጥረት እንዳደረጉ እንዲሁም ይህን በማድረጋቸው ያገኟቸውን በረከቶች እንዲናገሩ ጋብዝ።

መዝሙር 53 (130) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 7 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 92 (209)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የሚቀርቡትን የናሙና አቀራረቦች ከጉባኤው ክልል ጋር እንደሚስማማ አድርጎ መጠቀም እንዴት እንደሚቻል በአጭሩ ተናገር።—የጥር 2005 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 6ን ተመልከት።

15 ደቂቃ:- ለፍቅርና ለመልካም ሥራ የሚያነቃቁ ስብሰባዎች። በመጋቢት 15, 2002 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 24-25 ላይ ተመሥርቶ በንግግር የሚቀርብ። አንድ አስፋፊ (እህትም ልትሆን ትችላለች) አዘውትሮ በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ ለመገኘት ያደረገውን ጥረት እንዲሁም ይህን በማድረጉ ያገኘውን ጥቅም የሚያሳይ አጭር ቃለ ምልልስ አክለህ አቅርብ።

20 ደቂቃ:- በአገልግሎታችሁ ዘዴኞችና እንደ ሁኔታው አቀራረባችሁን የምትለውጡ ሁኑ። በታኅሣሥ 1, 2005 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 28-30 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ከአንቀጽ 6-11 ላይ ተመሥርተህ ንግግር ስታቀርብ ጳውሎስ አስተዋይ፣ እንደ ሁኔታው አቀራረቡን የሚለውጥ እንዲሁም በስብከቱና በማስተማሩ ሥራ ዘዴኛ እንደነበር አጉላ። ከዚያም አድማጮች ከአንቀጽ 12-14 ሥር በቀረቡት ጥያቄዎች ላይ ከአገልግሎት ክልሉ ጋር የሚስማማ ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ። አስፋፊዎች በአገልግሎት ክልላቸው የሚያገኟቸው ሰዎች የሚስፈልጋቸውን ነገር፣ ያሉበትን ሁኔታ እንዲሁም ባሕላቸውን ግምት ውስጥ አስገብተው መግቢያቸውን ሲያስተካክሉ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።

መዝሙር 83 (187) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ