ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ነሐሴ 28, 2006 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ በቃል መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከሐምሌ 3 እስከ ነሐሴ 28, 2006 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል። [ማሳሰቢያ:- ከጥያቄው ቀጥሎ መልሱ የሚገኝበት ጽሑፍ ካልተጠቀሰ መልሱን ለማግኘት በግልህ ምርምር ማድረግ ይኖርብሃል።—የአገልግሎት ትምህርት ቤት ገጽ 36-37ን ተመልከት።]
የንግግር ባሕርይ
1. አድማጮችን እያየን መናገር የተሻልን አስተማሪዎች እንድንሆን የሚረዳን እንዴት ነው? (ማቴ. 19:25, 26፤ ሥራ 14:9, 10) [be ገጽ 124 አን. 3 እስከ ገጽ 125 አን. 3]
2. የራስን ተፈጥሯዊ አነጋገር መጠቀም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? በመስክ አገልግሎት በምንካፈልበት ጊዜ በዚህ ችሎታ ለመጠቀም ምን ሊረዳን ይችላል? [be ገጽ 128 አን. 1-5፣ ሣጥን]
3. ልብሳችን ያልተዝረከረከና ንጹሕ መሆን ያለበት ለምንድን ነው? [be ገጽ 131 አን. 1-3]
4. በአለባበሳችንና በአጋጌጣችን ረገድ ጨዋነትንና ጤናማ አስተሳሰብን ማንጸባረቅ የምንችለው እንዴት ነው? (1 ጢሞ. 2:9) [be ገጽ 131 አን. 4 እስከ ገጽ 132 አን. 1]
5. አለባበሳችንና አበጣጠራችን ዓለምን እንደምንወድ የሚያሳይ እንዳይሆን የትኞቹን የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ተግባራዊ ማድረግ አለብን? [be ገጽ 133 አን. 2-3]
ክፍል ቁጥር 1
6. ከማንበብ የሚገኘው ከሁሉ የላቀ ጥቅም ምንድን ነው? [be ገጽ 21 አን. 3]
7. አንድን ሰው ጠቢብ ወይም ተላላ የሚያስብለው ምንድን ነው? (ምሳሌ 14:2) [w04 11/15 ገጽ 26 አን. 5]
8. ‘ዕውቀት ለአስተዋይ ሰው በቀላሉ የምትገኘው’ ለምንድን ነው? (ምሳሌ 14:6) [w04 11/15 ገጽ 28 አን. 3-4]
9. ጥናት ምንድን ነው? [be ገጽ 27 አን. 3]
10. በይሖዋ የፍጥረት ሥራዎች ላይ ማሰላሰላችን የሚጠቅመን እንዴት ነው? [w04 11/15 ገጽ 8 አን. 4]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. ይሖዋ ‘ብዙ ሴቶች ዜናውን እንዲያሰራጩ’ በጥንት ዘመን ‘ትእዛዝ የሰጠው’ እንዴት ነበር? ይህስ በዛሬው ጊዜ እየተፈጸመ ያለው እንዴት ነው? (መዝ. 68:11 የ1980 ትርጉም)
12. አሳፍ ቅን የሆነውን ነገር ማድረጉን እንዲያቆም ሊያደርገው የነበረው ምንድን ነው? አስተሳሰቡስ የተስተካከለው እንዴት ነው? (መዝ. 73:2, 3, 17)
13. እስራኤላውያን ይመገቡ የነበሩት መና ‘የሰማይ መብል’ እና ‘የመላእክት እንጀራ’ ተብሎ የተጠራው ለምንድን ነው? (መዝ. 78:24, 25)
14. ‘የልዑል መጠጊያ [“ምሥጢራዊ ቦታ፣” NW]’ የተባለው ምንድን ነው? በዚያ ‘መኖር’ የምንችለውስ እንዴት ነው? (መዝ. 91:1, 2)
15. ይሖዋ የታማኝ አገልጋዮቹ ሞት በፊቱ የከበረ የሆነው በምን መንገድ ነው? (መዝ. 116:15 NW)