ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ነሐሴ:- ብሮሹሮች፤ መስከረም:- የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፤ ጥቅምት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ግለሰቡ ፍላጎት ካሳየ ነቅተህ ጠብቅ! የተባለውን ብሮሹር በማበርከት ይበልጥ ፍላጎቱን ለማሳደግ ጥረት አድርጉ። ኅዳር:- ትራክቶች።
◼ በእጅ ያሉ ጽሑፎችና መጽሔቶች ዓመታዊ ቆጠራ በተቻለ መጠን ነሐሴ 31, 2006 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይርቅ መደረግ ይኖርበታል። ይህ ቆጠራ የጽሑፍ አስተባባሪው በየወሩ ከሚያካሂደው ቆጠራ ጋር ተመሳሳይ ነው። የጽሑፎቹ ጠቅላላ ድምር የጽሑፍ ቆጠራ ቅጽ (S-18) ላይ መሞላት አለበት። በእጅ ያሉ መጽሔቶችን ጠቅላላ ድምር ከመጽሔት አገልጋዩ(ዮቹ) ማግኘት ይቻላል። የአስተባባሪው ጉባኤ ጸሐፊ ቆጠራውን በበላይነት መከታተል ይኖርበታል። እርሱና የአስተባባሪው ጉባኤ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካች ቅጹ ላይ ይፈርማሉ። እያንዳንዱ አስተባባሪ ጉባኤ ሦስት የጽሑፍ ቆጠራ ቅጾች (S-18) ይደርሱታል። እባካችሁ ዋናውን ቅጂ እስከ መስከረም 6 ድረስ ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው ላኩ። አንድ የካርቦን ቅጂ ፋይላችሁ ውስጥ አስቀምጡ። ሦስተኛው ቅጂ ጊዜያዊ መሙያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል።
◼ መስከረም 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ አሊያም እርሱ የወከለው ሌላ ወንድም የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። ለእድሳት ወይም ለግንባታ ተብሎ ለብቻ የሚቀመጥ የባንክ ሒሳብ ካለ ይህንንም ለመመርመር ዝግጅት መደረግ አለበት። የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከቀረበ በኋላ የሒሳብ ምርመራው ውጤት ለጉባኤው መነበብ አለበት።
◼ “በእርግጥ ፈጣሪ አለ?” የሚል ርዕስ ያለው የመስከረም 2006 ንቁ! መጽሔት ልዩ እትም ነው። ጽሑፉ ስለ ዝግመተ ለውጥ የሚናገር ሲሆን የአስተማሪዎችንና የተማሪዎችን ትኩረት ይስባል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ጉባኤዎች የዚህን እትም ተጨማሪ የእንግሊዝኛም ሆነ የአማርኛ መጽሔቶችን ለማግኘት M-202 የተባለውን ቅጽ ተጠቅመው ልዩ ትዕዛዝ መላክ ይችላሉ።
◼ ለዘወትር አቅኚነት የሚቀርብ ማመልከቻ፣ አስፋፊው አቅኚነት መጀመር ከሚፈልግበት ቀን ቢያንስ ከ30 ቀናት በፊት ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው መላኩ አስፈላጊ ነው። የጉባኤው ጸሐፊ የማመልከቻ ቅጾቹ በሚገባ መሞላታቸውን ማረጋገጥ ይኖርበታል። አመልካቾች የተጠመቁበትን ትክክለኛ ቀን ማስታወስ ካልቻሉ ቀኑን ገምተው ለማወቅ መጣርና ይህን ቀን መዝግበው መያዝ ይኖርባቸዋል። የጉባኤው ጸሐፊ ይህን ቀን የጉባኤ አስፋፊ ካርድ (S-21) ላይ ሊመዘግበው ይገባል።
◼ የጉባኤ ጸሐፊዎች በጉባኤያችሁ ያለ እያንዳንዱ የዘወትር አቅኚ የዘወትር አቅኚ የሹመት ደብዳቤ (S-202) እንዳለው አረጋግጡ። ከሌለው ቅርንጫፍ ቢሮውን መጠየቅ ትችላላችሁ።
◼ ጉባኤዎች በሚቀጥለው ወር በሚልኩት የጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ ላይ የ2007 የይሖዋ ምሥክሮች የቀን መቁጠሪያ፣ ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር—2007 እና የ2007 የይሖዋ ምሥክሮች የዓመት መጽሐፍ ማዘዝ ይኖርባቸዋል።
◼ አዲስ የደረሱን ጽሑፎች:- ቻይንኛ:- ክሪኤሽን፣ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ ነቅተህ ጠብቅ!፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት፣ T-20 (ማጽናኛ)፣ አዲስ ዓለም ትርጉም (bi-12)፤ እንግሊዝኛ:- የ2005 የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔቶች ጥራዝ፣ አዲስ ዓለም ትርጉም በኤም ፒ3፤ ፈረንሳይኛ:- የ2006 የዓመት መጽሐፍ፤ ትግርኛ:- ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው (የጥምቀት ጥያቄዎችን የያዘ ቡክሌት)።
◼ በድጋሚ የደረሱን ጽሑፎች:- አማርኛ:- ወደ ይሖዋ ቅረብ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፣ የሙታን መናፍስት፤ እንግሊዝኛ:- ወደ ይሖዋ ቅረብ፣ ክሪኤተር፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፣ ራእይ፣ ኮንኮርዳንስ፣ የመጠበቂያ ግንብ ጽሑፎች ማውጫ 30-85፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ፣ የሰው ዘር አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ፣ ጋይዳንስ ኦፍ ጎድ፣ የይሖዋ ምሥክሮችና ትምህርት፣ ነቅተህ ጠብቅ!፣ ኤ ሳትስፋይንግ ላይፍ፣ ሮድ ቱ ላይፍ፣ በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም፣ የመዝሙር መጽሐፍ (ትንሹ)፤ ፈረንሳይኛ:- አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?፣ አዲስ ዓለም ትርጉም (bi-12)፤ ስዋሂሊ:- T-27 (መከራና ሥቃይ ሁሉ በቅርቡ ይወገዳል!)፤ ትግርኛ:- የዳንኤል ትንቢት፣ ወደ ይሖዋ ቅረብ፣ hw (ሃው ቱ ስታርት ኤንድ ኮንቲኒው ባይብል ዲስከሽንስ)፣ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?፣ sb-29 (የመዝሙር መጽሐፍ)።