ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች መስከረም:- የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፤ ጥቅምት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ግለሰቡ ፍላጎት ካሳየ ነቅተህ ጠብቅ! የተባለውን ብሮሹር በማበርከት ይበልጥ ፍላጎቱን ለማሳደግ ጥረት አድርጉ፤ ኅዳር:- ትራክቶች።
◼ ጉባኤዎች በሚቀጥለው ወር ከሚልኩት የጽሑፍ ትእዛዝ ጋር የ2006 የመጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! ጥራዞችን ማዘዝ መጀመር ይኖርባቸዋል።
◼ ሽማግሌዎች የመመለስ ዝንባሌ ያላቸውን የተወገዱ ወይም ራሳቸውን ያገለሉ ግለሰቦችን በተመለከተ በሚያዝያ 15, 1991 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 21-23 ላይ የተሰጡትን መመሪያዎች እንዲሠሩባቸው ልናስታውሳቸው እንወዳለን።
◼ በዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 3-6 ላይ የሚገኘው አባሪ እያንዳንዱ አስፋፊ ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል! በተባለው መጽሐፍ የግል ቅጂው ውስጥ የሚያደርጋቸውን በርካታ ማስተካከያዎች ይዟል። ይህም ጥር 8, 2007 ለሚጀምረው የጉባኤ መጽሐፍ ጥናት ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ይረዳናል።