የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
መስከረም 11 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 32 (70)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። መስከረም 25 በሚጀምር ሳምንት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለሚደረገው ውይይት ሁሉም የወጣቶች ጥያቄ—እውነተኛ ጓደኞች ማፍራት የምችለው እንዴት ነው? የተሰኘውን የቪዲዮ ፊልም ተመልክተው እንዲመጡ አበረታታ። በገጽ 8 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የነሐሴ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የነሐሴ 2006 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ ውይይቱን ለማስቆም “የራሴ ሃይማኖት አለኝ” ለሚል ሰው ምን መልስ መስጠት እንደሚቻል የሚያሳይ ይሁን።—ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 18-19ን ተመልከት።
20 ደቂቃ:- ከአገልግሎት ስብሰባና ከቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ጥቅም ማግኘት። የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ከገጽ 64 ንዑስ ርዕስ ጀምሮ እስከ ገጽ 69 ንዑስ ርዕስ ድረስ ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ።
15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
መዝሙር 93 (211) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 18 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 95 (213)
8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። ከአውራጃ ስብሰባው በፊት ባሉት ሦስት ሳምንታት ውስጥ ስብሰባውን ለማስተዋወቅ ልዩ የመጋበዣ ወረቀት እንደሚሰራጭ ሁሉንም አስታውሳቸው።—የሚያዝያ 2006 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 4ን ተመልከት።
15 ደቂቃ:- ያለፈው ዓመት የአገልግሎት እንቅስቃሴያችን ምን ይመስል ነበር? የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ጉባኤው ባከናወናቸው መልካም ነገሮች ላይ ትኩረት በማድረግ ያለፈውን የአገልግሎት ዓመት እንቅስቃሴ ይከልሳል። ለተደረጉት መልካም ነገሮች አመስግናቸው። በያዝነው የአገልግሎት ዓመት ጉባኤው ትኩረት ሊያደርግባቸው የሚገቡ አንድ ወይም ሁለት ነጥቦችን ጥቀስ። አቅኚዎች ያከናወኑትን ትጋት የታከለበት ሥራ በመጥቀስ አመስግናቸው። አገልግሎት ያቆሙ አስፋፊዎችን ለመርዳት የተደረገው ጥረት ያስገኘውን መልካም ውጤት ተናገር።
22 ደቂቃ:- “ከጥቅምት 16 እስከ ኅዳር 12 የሚደረግ ልዩ ዘመቻ!” አንድ ሽማግሌ ቀስቃሽ በሆነ መንገድ በውይይት ያቀርበዋል። ሰኔ 6, 2006 ለሽማግሌዎች አካላት በተላከው ደብዳቤ ላይ የሚገኘውን ማስታወቂያ ካነበብክ በኋላ በስብሰባው ላይ ለተገኙ ሁሉ የመንግሥት ዜና ቁ. 37 አንድ አንድ ቅጂ እንዲታደል አድርግ። ከዚያም ክፍሉን በጥያቄና መልስ በሚደረግ ውይይት አቅርበው። ጉባኤው ክልሉን ሙሉ በሙሉ ለመሸፈን ምን ዝግጅት እንዳደረገ ተናገር። ሁሉም አስፋፊዎች በዚህ ዘመቻ ሙሉ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አበረታታ። አንድ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 24 (50) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 25 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 49 (114)
15 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የመስከረም ወር ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። “በዘመቻ የሚሰራጭ የንቁ! መጽሔት ልዩ እትም” ከሚለው ርዕስ ሥር ዋና ዋና ነጥቦችን ከልስ። (የነሐሴ 2006 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 4ን ተመልከት) በገጽ 8 ላይ የሚገኘውን ሐሳብ ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆነ ሌላ አቀራረብ በመጠቀም የነሐሴ 15 መጠበቂያ ግንብ እና የመስከረም 2006 ንቁ! መጽሔቶችን መንገድ ላይ በምናገለግልበት ወቅት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
25 ደቂቃ:- “በቁም ነገር ሊታሰብበት የሚገባ የቪዲዮ ፊልም።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በአንቀጽ አንድ ላይ ስትወያዩ አድማጮች የወጣቶች ጥያቄ—እውነተኛ ጓደኞች ማፍራት የምችለው እንዴት ነው? የተሰኘውን የቪዲዮ ፊልም በተመለከተ በግል ምን እንደሚሰማቸው በአጭሩ እንዲናገሩ ጋብዝ። ከዚያም ከአንቀጽ 2-7 በቀረቡት ጥያቄዎች ላይ መወያየት ጀምር። በመጨረሻም በቅርቡ ቤተሰቦች አንድ ላይ ሆነው በዲቪዲ የተዘጋጀውን የወጣቶች ጥያቄ—ሕይወቴን እንዴት ብጠቀምበት ይሻላል? የሚለውን ፊልም እንዲመለከቱ አበረታታቸው።
5 ደቂቃ:- ከጉባኤው የተገኙ ተሞክሮዎች። አስፋፊዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ ሲያበረክቱ ያገኙት ተሞክሮ ካለ በተለይ ሰዎችን ባነጋገሩበት በመጀመሪያው ቀን ጥናት ያስጀመሩ ካሉ እንዲናገሩ ጋብዝ። አንድ ወይም ሁለት ተሞክሮዎች በሠርቶ ማሳያ እንዲቀርቡ አድርግ።
መዝሙር 82 (183) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥቅምት 2 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 23 (48)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። “የአውራጃ ስብሰባ ማሳሰቢያዎች” ከሚለው ላይ አንዳንድ ጠቃሚ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።
18 ደቂቃ:- “ይሖዋን በከፍተኛ ጉጉት ተጠባበቁ” የሚለውን ተወያዩበት።
17 ደቂቃ:- “ከቤት ወደ ቤት እየሄዱ መመሥከር።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አድማጮች ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ በተሰጡት ጥቅሶች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።
መዝሙር 51 (127) እና የመደምደሚያ ጸሎት።