ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት
ክለሳ ጥቅምት 30, 2006 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከመስከረም 4 እስከ ጥቅምት 30, 2006 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል። [ማሳሰቢያ:- ከጥያቄው ቀጥሎ መልሱ የሚገኝበት ጽሑፍ ካልተጠቀሰ መልሱን ለማግኘት በግልህ ምርምር ማድረግ ይኖርብሃል።—የአገልግሎት ትምህርት ቤት ገጽ 36-37ን ተመልከት።]
የንግግር ባሕርይ
1. ንግግር በምናቀርብበት ጊዜ መረጋጋት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ፍርሃትን መቀነስ የምንችለውስ እንዴት ነው? [be ገጽ 135 አን. 5 እስከ ገጽ 137 አን. 2፣ ሣጥኖቹ]
2. ስለ እምነታችን ጥያቄ ሲቀርብልን መልስ መስጠት ያለብን ከመጽሐፍ ቅዱስ መሆን ያለበት ለምንድን ነው? [be ገጽ 143 አን. 1-3]
3. በመጽሐፍ ቅዱስ በመጠቀም ረገድ የተዋጣልን መሆን የምንችለው እንዴት ነው? [be ገጽ 144፣ ሣጥኑ]
4. በመስክ አገልግሎት ላይ መጽሐፍ ቅዱስን አዘውትረን መጠቀም ያለብን ለምንድን ነው? በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ ሌሎች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲጠቀሙ ማበረታታት የምንችለውስ እንዴት ነው? [be ገጽ 145-146፣ ሣጥኖቹ]
5. ጥቅሶችን በምናስተዋውቅበት ወቅት ሊኖሩን የሚገቡ ሁለት ግቦች ምንድን ናቸው? [be ገጽ 147 አን. 2]
ክፍል ቁጥር 1
6. የመዝሙር መጽሐፍ ምን ጠቃሚ የሆነ ሐሳብ ይዟል? [bsi ገጽ 17 አን. 23]
7. የምሳሌ መጽሐፍ የተጻፈውና የተሰባሰበው መቼ ነው? [bsi ገጽ 20 አን. 5]
8. ምሳሌ ምንድን ነው? ለምሳሌ መጽሐፍ የተሰጠው የዕብራይስጥ ስያሜ ተስማሚ የሆነውስ ለምንድን ነው? [bsi ገጽ 20 አን. 6]
9. ምሳሌ 2:1-5 እውቀትንና ማስተዋልን ‘እንደ ብርና እንደተቀበረ ገንዘብ’ እንድንፈልግ ማበረታታቱ ምን ያመለክታል? [be ገጽ 38 አን. 4]
10. የምሳሌ መጽሐፍ በእርግጥ ጠቃሚ እንደሆነ መጽሐፉ ራሱ የሚያሳየው እንዴት ነው? [bsi ገጽ 21 አን. 19]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. ዳዊት ‘ጡት የጣለ ልጅ ዐርፎ እናቱ ላይ እንደሚቀመጥ ነፍሱን ጸጥ፣ ዝም ያሰኛት’ እንዴት ነበር? እኛስ እርሱን መኮረጅ የምንችለው እንዴት ነው? (መዝ. 131:1-3)
12. በመዝሙር 139:7-12 ላይ ከሚገኙት በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፉ ቃላት ምን ማጽናኛ እናገኛለን?
13. በጸሎታችንና በአገልግሎታችን ይሖዋን እንድናወድስ የሚገፋፉን በመዝሙር 145 ላይ የተገለጹ የይሖዋን ታላቅነት የሚያሳዩ አንዳንድ ምሳሌዎች የትኞቹ ናቸው? (መዝ. 145:3)
14. ይሖዋን መፍራት “የዕውቀት መጀመሪያ” እና “የጥበብ መጀመሪያ” የሆነው በምን መንገድ ነው? (ምሳሌ 1:7፤ 9:10)
15. በምሳሌ 7:1, 2 ላይ የሚገኙት “ቃሌን” እና “ትእዛዜን” የሚሉት ቃላት ምን ነገሮችን ይጨምራሉ?