ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ጥቅምት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ግለሰቡ ፍላጎት ካሳየ ነቅተህ ጠብቅ! የተባለውን ብሮሹር በማበርከት ይበልጥ ፍላጎቱን ለማሳደግ ጥረት አድርጉ፤ ኅዳር:- ትራክቶች፤ ታኅሣሥ:- እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው፤ ጥር:- እውቀት።
◼ የታኅሣሥ ወር አምስት ቅዳሜና እሁዶች ስለሚኖሩት ረዳት አቅኚ ሆኖ ለማገልገል አመቺ ነው።
◼ በዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን ውስጥ “የ2007 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም” አባሪ ሆኖ የወጣ ሲሆን ዓመቱን ሙሉ ልንጠቀምበት እንድንችል በጥሩ ሁኔታ ልንይዘው ይገባል።
◼ በጥር ወር የአገልግሎት ስብሰባ ላይ ደም አልወስድም—የሕክምናው መስክ መፍትሔ አስገኝቷል የተሰኘውን የቪዲዮ ፊልም እንከልሳለን። በዲቪዲ የተዘጋጀውን ወይም የቪዲዮ ክሩን ማግኘት የምትፈልጉ ከሆነ በተቻለ ፍጥነት በጉባኤያችሁ በኩል ማዘዝ ይኖርባችኋል።
◼ በ2007 በሚከበረው የመታሰቢያው በዓል ሰሞን የሚሰጠው ልዩ የሕዝብ ንግግር እሁድ ሚያዝያ 15, 2007 ይቀርባል። የንግግሩ ርዕስ ወደፊት ይገለጻል። በዚያ ሳምንት የወረዳ የበላይ ተመልካች ጉብኝት ወይም የወረዳ አሊያም የልዩ ስብሰባ ያላቸው ጉባኤዎች ልዩ የሕዝብ ንግግሩን በቀጣዩ ሳምንት ማቅረብ ይችላሉ። በየትኛውም ጉባኤ ልዩ የሕዝብ ንግግሩ ከሚያዝያ 15 በፊት መቅረብ አይኖርበትም።
◼ የሕዝብ ንግግር ለመስጠት ወደ ሌላ ጉባኤ ተጋብዘው የሚሄዱ ወንድሞች የሚቻል በሚሆንበት ጊዜ ሁሉ የመጠበቂያ ግንብ ጥናቱንም እዚያው ጉባኤ እንዲያደርጉ እናበረታታቸዋለን። ብዙውን ጊዜ ተናጋሪው ቤተሰቡን ጭምር ይዞ በመሄድ ከጉባኤው ጋር በአገልግሎት ለመካፈል ዝግጅት ማድረግ ይችላል።—2 ቆሮ. 6:13