የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 10/06 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ጥቅምት 9 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥቅምት 16 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥቅምት 23 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥቅምት 30 የሚጀምር ሳምንት
  • ኅዳር 6 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
km 10/06 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ጥቅምት 9 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 79 (177)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የመስከረም 1 መጠበቂያ ግንብ እና የመስከረም 2006 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ሠርቶ ማሳያዎቹ የመንግሥት ዜና ቁ. 37 ከመጽሔቶቹ ጋር አንድ ላይ ሲበረከት የሚያሳዩ ይሁኑ።

15 ደቂቃ:- “ሌሎች የአምላክ ወዳጅ እንዲሆኑ እርዷቸው።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። የሌሎች ምሳሌነት እንዲሁም ከልብ የመነጨ ጸሎት ወደ ጥምቀት እንዲደርሱ የረዳቸው እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።

20 ደቂቃ:- የመንግሥት ዜና ቁ. 37 ለማሰራጨት ተዘጋጁ። በንግግርና በውይይት የሚቀርብ። በመስከረም 2006 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ዘመቻውን አስመልክቶ የተደረገውን ዝግጅት ከልስ። ሁሉም በዘመቻው ሙሉ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አበረታታ። ጥሩ እድገት እያደረጉ ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ያሏቸው አስፋፊዎች ጥናቶቻቸው ያልተጠመቁ አስፋፊዎች ሆነው በማገልገል በዘመቻው ለመካፈል ብቃቱን ያሟሉ እንደሆነ እንዲያስቡበት አበረታታቸው። ወላጆችም ልጆቻቸው ብቃቱን ያሟሉ እንደሆነና እንዳልሆነ ሊያስቡበት ይችላሉ። የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ከገጽ 79-81 ያሉትን ብቃቶች በአጭሩ ተናገር።

መዝሙር 99 (221) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥቅምት 16 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 38 (85)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

20 ደቂቃ:- ከጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት ጥቅም ማግኘት። የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ገጽ 69 ላይ ከሚገኘው ንዑስ ርዕስ ጀምሮ እስከ ገጽ 72 የመጀመሪያ ንዑስ ርዕስ ድረስ ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ።

15 ደቂቃ:- “ቅድሚያ የምትሰጠው ነገር ምንድን ነው?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። የአምላክን መንግሥት ለማስቀደም ሲሉ ፕሮግራማቸውን ያስተካከሉት እንዴት እንደሆነና እንዲህ በማድረጋቸው ምን በረከቶች እንዳገኙ እንዲናገሩ አስቀድመህ የመረጥካቸውን አስፋፊዎች ጋብዝ።

መዝሙር 76 (172) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥቅምት 23 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 13 (33)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። በገጽ 8 ላይ የሚገኘውን ሐሳብ ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆነ ሌላ አቀራረብ በመጠቀም የመስከረም 15 መጠበቂያ ግንብ እና የጥቅምት 2006 ንቁ! መጽሔቶችን ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ ውይይቱን ለማስቆም “አዘውትራችሁ የምትመጡት ለምንድን ነው?” ለሚል ሰው ምን መልስ መስጠት እንደሚቻል የሚያሳይ ይሁን።—ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 20ን ተመልከት።

15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

20 ደቂቃ:- “ከመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎች የተሟላ ጥቅም ማግኘት።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በአንቀጽ 3 ላይ ስትወያዩ መስከረም 2001 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ከሚገኘው የጥያቄ ሣጥን አንቀጽ 4 ላይ ያለውን ስብሰባውን የሚመሩ ብቃት ያላቸው ወንድሞች የማይኖሩበት አጋጣሚ በሚፈጠርበት ጊዜ ምን ማድረግ እንደሚገባ የሚናገረውን ሐሳብ ጨምረህ አቅርብ።

መዝሙር 60 (143) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥቅምት 30 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 91 (207)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ እንዲሁም ያበረከቱትን የመንግሥት ዜና ቁ. 37 መጠን ከሪፖርቱ መመለሻ ቅጽ ጀርባ መጻፋቸውንም እንዳይረሱ አስታውሳቸው።

15 ደቂቃ:- አብረውኝ ለሚማሩት ልጆች መስበክ የምችለው እንዴት ነው? በሚያዝያ 2002 ንቁ! መጽሔት ከገጽ 14-16 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ተማሪዎች አብረዋቸው ለሚማሩ ልጆች በመስበክ ያገኙትን ጥሩ ተሞክሮ እንዲናገሩ ጋብዝ።

20 ደቂቃ:- የመንግሥት ዜና ቁ. 37ን በማበርከት የተገኙ ተሞክሮዎች። የመንግሥት ዜና ቁ. 37ን ሲያበረክቱ ያገኟቸውን አበረታች ውጤቶች እንዲናገሩ አስፋፊዎችን ጠይቅ። እስካሁን ምን ያህል ክልሎች እንደተሸፈኑና ቀሪዎቹን እስከ ኅዳር 12 ለመሸፈን ምን ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተናገር። የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ በመጠቀም ተመላልሶ መጠየቅ ሲደረግ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ። አስፋፊዎች የወሰዱትን የመንግሥት ዜና የዘመቻው ወቅት ከማለቁ በፊት አሰራጭተው የማይጨርሱ ከሆነ ትራክቱን ሌሎች እንዲያበረክቱት መመለስ እንዳለባቸው አስታውሳቸው።

መዝሙር 57 (136) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ኅዳር 6 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 62 (146)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በሐምሌ 2004 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 4 አንቀጽ 5 ላይ ያለውን አጭር አቀራረብ ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም በኅዳር ወር ሁለተኛ አጋማሽ ላይ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ማወቅ ትፈልጋለህ? የተባለውን ትራክት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አድማጮች ይህን ትራክት በመጠቀም ያገኟቸውን ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ጋብዝ።

15 ደቂቃ:- ቀንደኛውን ከሃዲ ተቃወሙት። በጥር 15, 2006 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 23-24 አን.12-16 ላይ ተመሥርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።

20 ደቂቃ:- ቃሉን መስበክ እረፍት ያስገኛል። በጥር 15, 2002 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 8-9 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። አድማጮች አገልግሎት እረፍት ያስገኘላቸው እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ ጋብዝ። ምናልባትም ሐሳብ የሚሰጡ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎችን አስቀድመህ ማዘጋጀት ትችላለህ።

መዝሙር 4 (8) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ