የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ኅዳር 13 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 65 (152)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የጥቅምት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የጥቅምት 2006 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ ውይይቱን ለማስቆም “የእናንተን ሃይማኖት በሚገባ አውቀዋለሁ” ለሚል ሰው ምን መልስ መስጠት እንደሚቻል የሚያሳይ ይሁን።—ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 20ን ተመልከት።
20 ደቂቃ:- የምሥራቹ አገልጋዮች። የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ ከተባለው መጽሐፍ ገጽ 77 እስከ ገጽ 83 ንዑስ ርዕሱ ድረስ ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ።
15 ደቂቃ:- “ደፋር ግን ሰላማውያን።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ከአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ከገጽ 252-253 ላይ “ምክንያታዊ መሆን የሚያስፈልግበት ጊዜ” ከሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።
መዝሙር 1 (3) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ኅዳር 20 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 54 (132)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
20 ደቂቃ:- በታኅሣሥ ወር እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው የተባለውን መጽሐፍ አበርክቱ። ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። አድማጮች ታላቅ ሰው የተባለውን መጽሐፍ እንዲያደንቁት ያደረጋቸውን ምክንያት እንዲሁም ከዚህ ቀደም መጽሐፉን ሲያበረክቱ ያገኟቸውን አስደሳች ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ጋብዝ። በጥር 2005 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይ የሚገኙትን የናሙና አቀራረቦች ከልስ። ከናሙና አቀራረቦች አንዱን ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆነ ሌላ አቀራረብ በመጠቀም መጽሐፉን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 80 (180) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ኅዳር 27 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 85 (191)
5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ።
10 ደቂቃ:- በስብሰባዎች ላይ በጣም ጥሩ የሆነ ሐሳብ መስጠት የምንችለው እንዴት ነው? አንድ ሽማግሌ በሰኔ 1995 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የሚገኘውን የጥያቄ ሣጥን ይከልሳል። ረጅምና ዙሪያ ጥምጥም ሐሳብ ከመስጠት መቆጠብ እንዳለብን ጎላ አድርገህ ተናገር። በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም የተባለውን መጽሐፍ ገጽ 70 እና 141ን እንዲሁም የመስከረም 1, 2003 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 21 አንቀጽ 6ን ተመልከት።
15 ደቂቃ:- “መጽሔቶችን ለማበርከት የሚያስችሉ መግቢያዎችን መዘጋጀት የሚቻለው እንዴት ነው?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ሁለት አስፋፊዎች (ባልና ሚስት ሊሆኑ ይችላሉ) የሦስት ደቂቃ ሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርቡ አድርግ። በመጀመሪያ ከገጽ 8 ላይ የጥቅምት 15, መጠበቂያ ግንብ እና የኅዳር 2006 ንቁ! መጽሔቶችን ለማበርከት ከተዘጋጁት መግቢያዎች መካከል አንዱን ከመረጡ በኋላ በራሳቸው አባባል እንዴት አድርገው እንደሚጠቀሙበት ተነጋግረው ይወስናሉ። ከዚያም እየቀረበ ባለው ክፍል ውስጥ የተሰጠውን ሐሳብ ተጠቅመው ለአገልግሎት ክልላቸው የሚሠራ ሌላ ወቅታዊ ርዕስ እንዴት ማስተዋወቅ እንደሚችሉ ይዘጋጁና በሠርቶ ማሳያ ያቀርባሉ።
15 ደቂቃ:- “የደም ክፍልፋዮችንና የራሴን ደም በመጠቀም የሚሰጡ ሕክምናዎችን በተመለከተ ምን ውሳኔ ማድረግ ይኖርብኛል?” በጥያቄና መልስ እንዲሁም በሠርቶ ማሳያ የሚቀርብ። ይህን ክፍል የሚያቀርበው ሽማግሌ ከቅርንጫፍ ቢሮው የተላከውን አስተዋጽኦ በጥብቅ መከተል ይኖርበታል።
መዝሙር 43 (98) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 4 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 66 (155)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የኅዳር ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው።
15 ደቂቃ:- “ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ወንድሞችና እህቶች የመጽሐፉን አንዳንድ ገጽታዎች ማለትም እንደ ሣጥን እና ሥዕሎች የመሳሰሉትን በደንብ እንዲጠቀሙባቸው አበረታታ። ከእያንዳንዱ ጥናት በኋላ ትምህርቱን መጽሐፍ ቅዱስን በመጠቀም ከልሱ።
20 ደቂቃ:- መልስ ስትመልሱ መጽሐፍ ቅዱስን ተጠቀሙ። በነሐሴ 15, 2002 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 17-18 ላይ በሚገኘው “ለምናስተምረው እውነት ፍቅር ማሳደር” በሚለው ንዑስ ርዕስ ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ለእያንዳንዱ ጥያቄ መልስ እንዲሰጡ አድማጮችን ጋብዝ። አንድ አስፋፊ “ገናን የማታከብረው ለምንድን ነው?” ብሎ ለጠየቀው የሥራ ባልደረባው ማመራመር በተባለው መጽሐፍ ተጠቅሞ ቅዱስ ጽሑፋዊ መልስ ሲሰጠው የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርብ አድርግ።
መዝሙር 74 (168) እና የመደምደሚያ ጸሎት።