ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት
ክለሳ ታኅሣሥ 25, 2006 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከኅዳር 6 እስከ ታኅሣሥ 25, 2006 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል። [ማሳሰቢያ፦ ከጥያቄው ቀጥሎ መልሱ የሚገኝበት ጽሑፍ ካልተጠቀሰ መልሱን ለማግኘት በግልህ ምርምር ማድረግ ይኖርብሃል።—የአገልግሎት ትምህርት ቤት ገጽ 36-37ን ተመልከት።]
የንግግር ባሕርይ
1. አንድን ጥቅስ ለማስተዋወቅ ተስማሚ የሆነ ሐሳብ በምንመርጥበት ጊዜ ውሳኔያችን ምንን መሠረት ያደረገ መሆን አለበት? [be ገጽ 148 አን. 4 እስከ ገጽ 149 አን. 1]
2. ተፈላጊዎቹን ቃላት ወይም አባባሎች ለማጉላት የሚረዱን አንዳንድ ዘዴዎች ምንድን ናቸው? [be ገጽ 151 አን. 4 እስከ ገጽ 152 አን. 3]
3. የአምላክን ቃል ለሌሎች ማስተማር ከባድ ኃላፊነት በመሆኑ ‘የእውነትን ቃል በትክክል ለማስረዳት’ ምን ይፈለግብናል? (2 ጢሞ. 2:15) [be ገጽ 153 አን. 1-4፣ ሣጥኑ፤ ገጽ 154 አን. 1]
4. ጥቅሶችን ስናነብ ጥቅሱ ከነጥቡ ጋር ያለውን ዝምድና ግልጽ ማድረግ የምንችለው በየትኞቹ መንገዶች ነው? [be ገጽ 154 አን. 3 እስከ ገጽ 155 አን. 3]
5. የትምህርቱን ጥቅም ግልጽ ማድረግ በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ይህን ማድረግ የሚቻልባቸው አንዳንድ መንገዶችስ ምንድን ናቸው? [be ገጽ 157 አን. 1-4፣ ሣጥኑ፤ ገጽ 158 አን. 1]
ክፍል ቁጥር 1
6. ሰሎሞን ሰባኪ የነበረው በምን መንገድ ነው? [bsi ገጽ 25 አን. 1-3]
7. የመክብብ መጽሐፍ ከኢየሱስ ትምህርቶች ጋር የሚስማማው እንዴት ነው? [bsi ገጽ 26 አን. 16]
8. ማሕልየ መሓልይ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ለመሆኑ ምን ማስረጃ አለ? [bsi ገጽ 28 አን. 3-4]
9. በሙት ባሕር አካባቢ የተገኘው የኢሳይያስ ጥቅልል በእጃችን ያለው መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ አነሳሽነት ከተጻፈው ከመጀመሪያው ቅጂ ጋር ተመሳሳይ ለመሆኑ አሳማኝ ማስረጃ የሚሆነው እንዴት ነው? [bsi ገጽ 30 አን. 6]
10. አንድ ተናጋሪ ብዙ ማስታወሻ እንዳይዝ ምን ማድረግ ይችላል? [be ገጽ 42 አን. 1]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. ‘እግዚአብሔርን የሚሹ ሁሉን የሚያስተውሉት’ እንዴት ነው? (ምሳሌ 28:5 የ1954 ትርጉም)
12. ‘የሞኝ ሥራ ራሱን የሚያደክመው’ እንዴት ነው? (መክ. 10:15)
13. ሱላማጢሷ ልጃገረድ ‘እንደ ታጠረ የአትክልት ቦታ’ የሆነችው እንዴት ነው? ላላገቡ ክርስቲያን ሴቶችስ ግሩም ምሳሌ የምትሆነው በምን መልኩ ነው? (ማሕ. 4:12)
14. ይሖዋ እስራኤላውያንን “ኑና እንዋቀስ” ማለቱ ከሕዝቦቹ ጋር ለመደራደር ፈቃደኛ መሆኑን የሚያሳይ ነው? (ኢሳ. 1:18ሀ)
15. ኢሳይያስ 11:6-9 በጥንት ጊዜ ፍጻሜውን ያገኘው እንዴት ነበር? የትንቢቱ የላቀ ፍጻሜስ ምንድን ነው?