ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ታኅሣሥ:- እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው፤ ጥር:- እውቀት፤ የካቲት:- ወደ ይሖዋ ቅረብ፤ መጋቢት:- የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት
◼ ጥር 1, 2007 በሚጀምር ሳምንት በጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት ላይ የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ—2 የተባለውን መጽሐፍ እንከልሳለን።
◼ ለ2007 የመታሰቢያ በዓል የሚያገለግል የመጋበዣ ወረቀት ጉባኤው በሚመራበት ቋንቋ በቅርቡ ለጉባኤዎች ይላካል።
◼ በ2007 የመታሰቢያው በዓል የሚከበርበት ዕለት ሰኞ፣ ሚያዝያ 2 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ይሆናል። በ2008 ደግሞ የመታሰቢያው በዓል የሚከበርበት ዕለት የሚውለው ቅዳሜ፣ መጋቢት 22 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ነው። በዓሉ ትልቅ ግምት የሚሰጠው ከመሆኑ አኳያ የሽማግሌዎች አካል የመታሰቢያውን ንግግር የሚያቀርበውን ወንድም ሲመድብ ብቃት ያለውን ሽማግሌ ይመርጣል እንጂ በተራ እንዲዳረስ ወይም በየዓመቱ አንድ ሽማግሌ ብቻ እንዲያቀርብ ማድረግ የለበትም። ንግግሩን በሚገባ ማቅረብ የሚችል ቅቡዕ ሽማግሌ ካለ እርሱ ሊመደብ ይገባል።
◼ የ2007ን የዓመት ጥቅስ የሚያብራራው የታኅሣሥ 15, 2006 መጠበቂያ ግንብ የሚጠናው ጥር 15 ከሚጀምረው ሳምንት አንስቶ መሆኑን እንገልጽላችኋለን።
◼ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ጽሑፎች አሁንም ስላሉን ማዘዝ ትችላላችሁ:- እንግሊዝኛ:- የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ፣ ወጣቶች—በሕይወታችሁ ምን ለማድረግ አስባችኋል? (ትራክት)፣ የ2006 የይሖዋ ምሥክሮች የዓመት መጽሐፍ፣ ወደ ይሖዋ ቅረብ (በካሴት)፤ ፈረንሳይኛ:- ወጣቶች—በሕይወታችሁ ምን ለማድረግ አስባችኋል? (ትራክት)፤ ሶማልኛ:- በደስታ ኑር! ትግርኛ:- የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ፤ እንግሊዝኛ ብሬይል:- ትራክት ቁ. 13 (መጽሐፍ ቅዱስን ማመን የሚችሉት ለምንድን ነው?)።
◼ አዲስ ይደርሱናል ብለን የምንጠብቃቸው ጽሑፎች፦ አማርኛ:- ቅዱሳን መጻሕፍትን በየዕለቱ መመርመር—2007፣ ትራክት ቁ. 17 (ሰላም የሰፈነበት አዲስ ዓለም ይመጣ ይሆን? ለአይሁዳውያን)፣ ትራክት ቁ. 18 (የይሖዋ ምሥክሮች ምን ብለው ያምናሉ? ለአይሁዳውያን)፤ ቻይንኛ (በቀላል ቋንቋ የተዘጋጀ):- እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው፣ ትራክት ቁ. 26 (ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ማወቅ ይፈልጋሉ?)፤ እንግሊዝኛ:- ቅዱሳን መጻሕፍትን በየዕለቱ መመርመር—2007፣ የ2007 የቀን መቁጠሪያ፣ አዲስ ዓለም ትርጉም (bi12)፣ የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት በዲቪዲ (dvcbi7)፤ ፈረንሳይኛ:- ቅዱሳን መጻሕፍትን በየዕለቱ መመርመር—2007፤ ኦሮምኛ:- ሂዱና ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው (የጥምቀት ጥያቄዎችን የያዘ ቡክሌት)፤ ትግርኛ:- ቅዱሳን መጻሕፍትን በየዕለቱ መመርመር—2007፤ ወላይትኛ:- አምላክ ከእኛ የሚፈልገው፣ የሙታን መናፍስት።
◼ በድጋሚ የደረሱን ጽሑፎች፦ አማርኛ:- የወጣቶች ጥያቄ፣ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው፣ ደም ሕይወትህን ሊያድን የሚችለው እንዴት ነው?፣ ትራክት ቁ. 16 (እናፈቅራቸው የነበሩ ሙታን ምን ተስፋ አላቸው?)፣ ቁ. 20 (ለተጨነቁ ሰዎች የሚሆን መጽናኛ)፣ ቁ. 22 (ዓለምን የሚገዛው ማን ነው?)፤ ፈረንሳይኛ:- ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው?፣ ትራክት ቁ. 21 (በቤተሰብ ኑሮ ተደሰት)፤ ትግርኛ:- የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፣ እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው።