የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ታኅሣሥ 11 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 77 (174)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የኅዳር 1 መጠበቂያ ግንብ እና የኅዳር 2006 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ ውይይቱን ለማስቆም “ፍላጎት የለኝም” ለሚል ሰው ምን መልስ መስጠት እንደሚቻል የሚያሳይ ይሁን።—ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 16ን ተመልከት።
15 ደቂቃ:- የ2007 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በንግግርና በቃለ ምልልስ ያቀርበዋል። ከጥቅምት 2006 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይ ለጉባኤያችሁ አስፈላጊ የሆኑ ነጥቦችን አቅርብ። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ተማሪው በዕለቱ በየትኛው የንግግር ባሕርይ ላይ እንደሚሠራ አስቀድሞ መናገር እንደሌለበት ተናገር። በ2007 ከኢሳይያስ ምዕራፍ 24 እስከ ሚልክያስ ያሉትን የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት አንብበን እንጨርሳለን፤ በዚህ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጎላ ያሉ ነጥቦችን እንዲያቀርቡ የሚመደቡትም ሆኑ ምርምር አድርገው ሐሳብ የሚሰጡት ወንድሞች እነዚህ የትንቢት መጻሕፍት የተብራሩባቸውን ጽሑፎች ለመጠቀም አመቺ ሁኔታ ይፈጥርላቸዋል። ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት መካከል ሁለት ወይም ሦስት አስፋፊዎችን መርጠህ ቃለ ምልልስ አድርግላቸው:- በትምህርት ቤቱ ለተመዘገበ አዲስ ተማሪ፣ ጥሩ እድገት እያደረገ ላለ ወጣት እንዲሁም ተሞክሮ ላካበተ ተማሪ። ትምህርት ቤቱ በአገልግሎታቸውም ሆነ በመንፈሳዊነታቸው ላይ ያሳደረውን በጎ ተጽዕኖ እንዲናገሩ ጋብዝ። ሁሉም የሚሰጣቸውን ክፍል በትጋት እንዲዘጋጁ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጎላ ያሉ ነጥቦች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ እንዲሁም በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም ከተባለው መጽሐፍ ላይ በየሳምንቱ የሚቀርበውን ትምህርት ተግባራዊ እንዲያደርጉ አበረታታ።
20 ደቂቃ:- “የቀድሞው ፍቅራችሁ እንዳይጠፋ ተጠንቀቁ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አድማጮች ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ በተጠቀሱ ጥቅሶች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።
መዝሙር 86 (193) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 18 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 74 (168)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። የጥያቄ ሣጥን (1) የሚለውን አቅርብ። በበዓል ቀናት በመስክ አገልግሎት ለመካፈል ስለተደረገ ልዩ ዝግጅት ተናገር።
15 ደቂቃ:- “መጠነኛ ፍላጎት ላሳዩ ሰዎች በሙሉ ተመላልሶ መጠየቅ አድርጉላቸው።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አድማጮች መደበኛ ባልሆነ መንገድ ወይም በመንገድ ላይ ምሥክርነት ሲሰጡ ካጋጠሟቸው ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች፣ አድራሻ እንዴት መቀበል እንደቻሉ ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ። ለእነዚህ ሰዎች ተመላልሶ መጠየቅ ሲያደርጉ ያገኙት ተሞክሮ ካለ እንዲናገሩ ጋብዝ። ሐሳብ የሚሰጡ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎችን አስቀድመህ ልታዘጋጅ ትችላለህ።
20 ደቂቃ:- “የፈቃደኝነት መንፈስ ማሳየት በረከት ያስገኛል።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በፈቃደኝነት ራስን የማቅረብ መንፈስ በማሳየት ለሚታወቅ(ቁ) አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች ቃለ ምልልስ አድርግ። በፈቃደኝነት ራሳቸውን ያቀረቡት እንዴት ነው? ምን ማስተካከያ ማድረግ አስፈልጓቸዋል? እንዴትስ ማስተካከያ ማድረግ ቻሉ? እንዲህ ማድረጋቸው ምን በረከቶችን አስገኝቶላቸዋል?
መዝሙር 80 (180) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 25 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 14 (34)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። በገጽ 8 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የኅዳር 15 መጠበቂያ ግንብ እና የታኅሣሥ 2006 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። እያንዳንዱን ሠርቶ ማሳያ በቀጣዩ ቀጠሮ ወቅት የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ ተጠቅመው መልስ የሚሰጡበትን አእምሮን የሚያመራምር ጥያቄ በማቅረብ ይደመድማሉ።
15 ደቂቃ:- በአገልግሎት የሚታየውን እድገት ሪፖርት ማድረግ። የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ ከተባለው መጽሐፍ ገጽ 83 ላይ ካለው ንዑስ ርዕስ እስከ ምዕራፉ መጨረሻ ድረስ ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ።
20 ደቂቃ:- “የግል የአገልግሎት ክልል አለህ?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ስለ ጉባኤው የአገልግሎት ክልል ስፋት፣ የአገልግሎት ክልሉ ስንት ጊዜ እንደተሸፈነ እንዲሁም ምን ያህል የግል የአገልግሎት ክልል እንዳለ የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ አጭር ሐሳብ እንዲሰጥ አድርግ።
መዝሙር 24 (50) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥር 1 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 51 (127)
5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የታኅሣሥ ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው።
10 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት፤ ወይም የጥያቄ ሣጥን (2) የሚለውን ማቅረብ ትችላላችሁ።
30 ደቂቃ:- “ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች የሰውን ፍርሃት እንዲያሸንፉ እርዱ።” በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ። አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን በአንቀጽ 2, 5, 6 እና 8 ላይ ያሉትን ጥቅሶች አንብብ። በአንቀጽ 2 እና 5 ውስጥ ባለው ሐሳብ ላይ የተመሠረቱ ሁለት አጫጭር ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
መዝሙር 88 (200) እና የመደምደሚያ ጸሎት።