ከታላቁ አስተማሪ ተማር የተባለውን መጽሐፍ ለማጥናት የሚረዱ ጥያቄዎች
አስተማሪ የተባለውን መጽሐፍ ለማጥናት የሚያገለግሉ መመሪያዎች
ይህን መጽሐፍ በደንብ ለማጥናት መግቢያውን ጨምሮ በእያንዳንዱ ምዕራፍ ውስጥ ላሉት አንቀጾች ቁጥር ስጧቸው። አንድ ላይ የተደረጉት አንቀጾች በሙሉ አንድ ላይ መነበብ አለባቸው። ጥናቱ በሚከናወንበት ወቅት በምዕራፉ መጨረሻ ላይ ያሉት ጥቅሶች እንደ አስፈላጊነቱ ውይይት ሊደረግባቸው ይችላል።
ይህ መጽሐፍ በጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በሚጠናበት ጊዜ በእያንዳንዱ ሳምንት አንድ ምዕራፍ ይጠናል፤ መግቢያው እንደ መጀመሪያ ምዕራፍ ተደርጎ ይወሰዳል። መጽሐፉ በ49 የጥናት ሳምንታት ውስጥ ያልቃል።
መግቢያ አንቀጽ 1-5
1. ልጅ መውለድ ተአምር ነው የሚባለው ለምንድን ነው?
2. ወላጆች ለልጆቻቸው ሊያደርጓቸው የሚገቡ አንዳንድ ነገሮች ምንድን ናቸው?
3. ክርስቲያን ወላጆች ለልጆቻቸው የሚሰጧቸው መመሪያዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንጂ በሰው ፍልስፍና ወይም በባሕል ላይ የተመሠረቱ መሆን የሌለባቸው ለምንድን ነው? (ምሳሌ 3:5, 6፤ 14:12፤ ኢሳይያስ 30:21)
አንቀጽ 6-10
4. በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉት ጥያቄዎች ወላጆች ልጆቻቸውን ማስተማር እንዲችሉ በሚረዳ መንገድ የተዘጋጁት እንዴት ነው? አንድ ወላጅ ልጆቹ እንዲህ ላለው ጥያቄ የሚሰጡት መልስ ምን እንዲያውቅ ይረዳዋል?
5. ሥዕሎቹ ጥሩ የማስተማሪያ ዘዴ ሆነው እንዲያገለግሉ ተደርገው የተዘጋጁት እንዴት ነው?
6. የዚህ መጽሐፍ አዘጋጆች ምን ነገር ተስፋ ያደርጋሉ?
ምዕራፍ 1 አንቀጽ 1-6
1. ኢየሱስ አስተማሪ ሆኖ ምን ነገር ማከናወን ችሏል?
2. ኢየሱስ ጥሩ ልጅና ታላቅ አስተማሪ የሆነው እንዴት ነው?
3. ኢየሱስ ከሌሎች ሰዎች ሁሉ የተለየ የሆነው በምን መንገድ ነው?
አንቀጽ 7-11
4. ልጆች ኢየሱስ እንደሚወዳቸው ሊያውቁ የቻሉት እንዴት ነው?
5. ኢየሱስ ልጆችን ያስተማረው ለምንድን ነው? ከእሱ ምሳሌስ ምን ልንማር እንችላለን?
6. ኢየሱስ ትልልቅ ሰዎች እንደ ሕፃን መሆን አለባቸው ሲል ምን ማለቱ ነበር?
አንቀጽ 12-16
7. ኢየሱስ ስለ ወፎችና ስለ አበቦች ሲናገር ምን ማስተማር ፈልጎ ነበር?
8. ኢየሱስ ያስተማረው ነገር አንድ ሰው ከቤተሰቡ ተለይቶ እንዲሄድ የሚያደርግ ሥራን በተመለከተ ጥሩ ውሳኔ እንዲያደርግ ሊረዳው የሚችለው እንዴት ነው?
9. ኢየሱስ በተራራው ስብከት ላይ በሕይወታችን ውስጥ ለአምላክ አንደኛ ቦታ የመስጠትን አስፈላጊነት የሚያሳይ ምን ነገር ተናግሯል?
አንቀጽ 17-21
10. ኢየሱስን ማዳመጥ የምንችለው እንዴት ነው? እንዲህ ማድረጋችንስ ምን ውጤት አለው?
11. አምላክ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ኢየሱስን እንዲሰሙት የነገራቸው መቼ ነው? እውነተኛ ደስታ ማግኘት የምንችለውስ እንዴት ነው?
ምዕራፍ 2 አንቀጽ 1-7
1. መጽሐፍ ቅዱስ ከሌሎች መጻሕፍት ሁሉ ይበልጥ ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?
2. አምላክ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲጻፍ ያደረገው እንዴት ነው? አምላክ ከሰማይ ሆኖ መልእክቶቹን መላክ ይችላል ብሎ ማመን ምክንያታዊ የሆነውስ ለምንድን ነው?
አንቀጽ 8-12
3. የመጀመሪያው የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ እስኪያልቅስ ምን ያህል ጊዜ ፈጅቷል?
4. ከመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች መካከል አንዳንዶቹን ጥቀስ፤ እንዲሁም በሥዕሉ ላይ የሚታዩትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች ለይተህ ተናገር።
5. የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች አንዳንድ ነገሮችን ገና ሳይፈጸሙ ማወቅ የቻሉት እንዴት ነው?
አንቀጽ 13-18
6. ሁሉም ሰው አምላክ ለሰው ልጆች ባስጻፈው ደብዳቤ ላይ የሰፈረውን ነገር መማር የሚችለው ለምንድን ነው?
7. መጽሐፍ ቅዱስ ከሚነግረን ጠቃሚ ነገሮች መካከል አንዳንዶቹ ምንድን ናቸው?
8. ጥበበኞች እንደሆንንና የአምላክን ቃል እንደምናደንቅ ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
ምዕራፍ 3 አንቀጽ 1-10
1. አፈጣጠራችንን በተመለከተ አንተን ይበልጥ የሚያስደንቅህ ምንድን ነው?
2. አምላክ መጀመሪያ የፈጠረው ማንን ነው? ይህንንስ የምናውቀው እንዴት ነው?
3. አምላክ ሕያዋን ነገሮችን የፈጠረው ለምንድን ነው?
4. አምላክ ለእኛ ያለውን ፍቅር ያሳየው እንዴት ነው?
አንቀጽ 11-21
5. አምላክ በእርግጥ እንዳለ ለማስረዳት ምን ምሳሌዎች መጠቀም ትችላለህ?
6. የአምላክን ምስል ለመሥራት መሞከር የሌለብን ለምንድን ነው?
7. አምላክ ላደረገልን ነገር አመስጋኝ መሆናችንን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
ምዕራፍ 4 አንቀጽ 1-6
1. ስም በጣም አስፈላጊ ነገር እንደሆነ የሚያሳየው ምንድን ነው?
2. የአምላክ ስም ማነው? በስሙ መጠቀምስ ያለብን ለምንድን ነው?
3. ኢየሱስ በአምላክ ስም ይጠቀም የነበረው እንዴት ነው? ሌሎችስ ይህን እንዲያደርጉ ያስተማረው እንዴት ነው?
አንቀጽ 7-14
4. አምላክ ስሙን በተመለከተ ለሙሴ ምን ገልጾለታል?
5. ይሖዋ ስሙን በተመለከተ ፈርዖንን ምን ብሎታል?
6. ይሖዋ ስሙ እንዲታወቅ ያደረገው እንዴት ነው? በዛሬው ጊዜስ ይህን የሚያደርገው እንዴት ነው?
አንቀጽ 15-19
7. በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የአምላክን ስም የት ቦታ ላይ ማሳየት ትችላለህ?
8. ይሖዋን እንደምትወደው ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?
ምዕራፍ 5 አንቀጽ 1-8
1. የአምላክ ልጅ ምድር ላይ የተወለደው ለምንድን ነው? (ሉቃስ 1:26-38)
2. ኢየሱስም ሆነ ማርያም ምን ጥሩ ምሳሌ ትተውልናል? እነሱንስ መኮረጅ የምንችለው እንዴት ነው?
3. የኢየሱስ አወላለድ ከሌሎች ሕፃናት አወላለድ የተለየ የሆነው እንዴት ነው?
አንቀጽ 9-17
4. ኢየሱስ በተወለደበት ሌሊት ምን ነገሮች ተፈጽመዋል?
5. ኢየሱስ ያደገው የት ነው? በኋላስ አምላክ በእሱ የተደሰተው ምን እርምጃ በመውሰዱ ነው? (መዝሙር 40:6-8)
6. ኢየሱስ ከተወው ምሳሌ ልንማራቸው የምንችላቸው ሌሎች ነገሮች ምንድን ናቸው?
ምዕራፍ 6 አንቀጽ 1-4
1. አብዛኞቹ ሰዎች ሁልጊዜ ምን ይፈልጋሉ? የኢየሱስ ደቀ መዛሙርትም አንዳንድ ጊዜ እንዲህ ይሰማቸው እንደነበር ያሳዩት እንዴት ነው?
2. ደቀ መዛሙርቱ ቀደም ሲል ኢየሱስ ያስተማራቸውን የትኛውን ትምህርት ሳይማሩ ቀርተዋል?
አንቀጽ 5-11
3. ኢየሱስ ከመሞቱ በፊት በነበረው ምሽት ምን አደረገ? ይህስ ምን ትምህርት ይሰጣል?
4. የኢየሱስን ምሳሌ የምንከተል ከሆነ ምን መልካም ውጤት እናገኛለን?
አንቀጽ 12-17
5. የቤተሰብህን አባላት ማገልገል የምትችለው እንዴት ነው?
6. በትምህርት ቤትም ሆነ በሌሎች ቦታዎች ሰዎችን ማገልገል የምትችለው እንዴት ነው?
7. ሰዎች ለተደረገላቸው ነገር ላያመሰግኑ ቢችሉም እንኳ እነሱን ማገልገል ያለብን ለምንድን ነው?
ምዕራፍ 7 አንቀጽ 1-9
1. ትልልቅ ሰዎችን መስማት ጥበብ የሆነው ለምንድን ነው?
2. በሉቃስ 22:42 ላይ ከሚገኘው የኢየሱስ ጸሎት ምን ልንማር እንችላለን?
3. አምላክን ስንታዘዝ ምን እያሳየን ነው?
አንቀጽ 10-15
4. ልጆች ኤፌሶን 6:1-3 ላይ ያለውን ምክር ተግባራዊ ሊያደርጉ የሚችሉት እንዴት ነው? ይህንንስ ማድረግ ያለባቸው ለምንድን ነው?
5. በጥንት ጊዜ ሰዎች ታዛዥ መሆናቸው ከጥፋት እንዲተርፉ የረዳቸው እንዴት ነው?
አንቀጽ 16-19
6. በዛሬው ጊዜ ልጆች ታዛዦች መሆናቸው ሕይወታቸውን ሊያተርፍላቸው የሚችለው እንዴት ነው?
7. ሁሉም ሰው አምላክን ቢታዘዝ የሚጠቀመው እንዴት ነው?
ምዕራፍ 8 አንቀጽ 1-5
1. በሥልጣንም ይሁን በኃይል ከሰዎች በላይ የሆኑት እነማን ናቸው?
2. ኢየሱስ በምድር ላይ ሕፃን ሆኖ እንዲወለድ አምላክ ምን ተአምር ፈጽሟል?
3. ኢየሱስ ሰው ሆኖ ወደ ምድር ከመምጣቱ በፊትም በሕይወት ይኖር እንደነበር የገለጸው እንዴት ነው?
አንቀጽ 6-11
4. አዳምና ሔዋን አምላክን ቢታዘዙ ኖሮ ምን ዓይነት ሕይወት ይጠብቃቸው ነበር?
5. ዘፍጥረት 2:17 ላይ ከሚገኘው ሐሳብ ምን ጠቃሚ ትምህርት መማር እንችላለን?
አንቀጽ 12-19
6. አምላክ የፈጠረው አንድ መልአክ ሔዋንን ያታለላት እንዴት ነው?
7. አዳምና ሔዋን አምላክን አለመታዘዛቸው ምን ውጤት አስከተለ?
8. ጥሩ የነበረው መልአክ ክፉ የሆነው ለምንድን ነው?
9. የኢየሱስን ምሳሌ በመኮረጅ ዲያብሎስ ውሸታም መሆኑን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
ምዕራፍ 9 አንቀጽ 1-4
1. ስህተት የሆነ ነገር እንድንሠራ በምንፈተንበት ጊዜ በፈተናው ተሸንፈን ስህተት የሆነ ነገር መሥራት የሌለብን ለምንድን ነው?
2. መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ በተጠመቀበት ጊዜ “ሰማያት ተከፈቱ” ሲል ምን ማለቱ ሊሆን ይችላል?
አንቀጽ 5-13
3. ሰይጣን በመጀመሪያ ኢየሱስን የፈተነው እንዴት ነው? ኢየሱስ ይህን ፈተና የተቋቋመው እንዴት ነው?
4. ሰይጣን ያቀረበው ሁለተኛ ፈተና ምን ነበር? ኢየሱስ ምላሽ የሰጠውስ እንዴት ነው?
5. ኢየሱስ ካጋጠመው ሦስተኛ ፈተና ምን መማር እንችላለን?
አንቀጽ 14-20
6. እኛስ አካላዊ ፍላጎታችንን እንድናሟላ ወይም የሞኝነት ድርጊት እንድንፈጽም ልንፈተን የምንችለው እንዴት ነው?
7. ትክክል የሆነውን ነገር ማድረግ ይበልጥ ከባድ የሚሆነው መቼ ነው? ሆኖም ሁልጊዜ ትክክል የሆነውን ነገር እንድናደርግ ምን ሊረዳን ይችላል?
ምዕራፍ 10 አንቀጽ 1-6
1. ከመላእክት አንዱ የአምላክ ተቃዋሚ የሆነው ለምንድን ነው?
2. አንዳንድ መላእክት ምን አደረጉ? ይህስ መጥፎ የነበረው ለምንድን ነው?
3. የመላእክቱ ልጆች ምን ዓይነት ነበሩ? አምላክ በምድር ላይ ያለውን ክፋት ለማጥፋት ምን አደረገ?
አንቀጽ 7-11
4. በአሁኑ ጊዜ ሰይጣንና አጋንንቱ ምን እያደረጉ ነው? በእኛ ላይ ተጽዕኖ ማሳደር የሚችሉትስ እንዴት ነው?
5. ክፉ የሆኑት መላእክት፣ ልጆች ምን መጥፎ ነገር እንዲሠሩ ለማድረግ ይሞክራሉ?
አንቀጽ 12-17
6. ክፉ የሆኑት መላእክት ምን መጥፎ ነገሮችን ይወዳሉ? ሰዎችስ ብዙውን ጊዜ ስለ እነዚህ ነገሮች የሚማሩት ከየት ነው?
7. አጋንንት በጣም ኃይለኞች ቢሆኑም እንኳ እነሱን መፍራት የሌለብን ለምንድን ነው?
ምዕራፍ 11 አንቀጽ 1-11
1. ማየት በማንችላቸው ነገሮች ማመን የምንችለው ለምንድን ነው?
2. ስለ ጥሩዎቹም ሆነ ስለ ክፉዎቹ መላእክት ምን ተምረናል?
3. መላእክት ስለ ምን ነገር ያወራሉ? መላእክት ስለ እኛ ያስባሉ ብለህ እንድታምን የሚያደርግህ ምንድን ነው?
4. በጥንት ዘመን መላእክት አምላክን የሚወዱ ሰዎችን የረዱት እንዴት ነው?
አንቀጽ 12-17
5. የአምላክ መላእክት በምድር ላይ ያሉትን የእሱን አገልጋዮች ለመርዳት ምን ልዩ ሥራ ያከናውናሉ?
6. የአምላክ መላእክት ጳውሎስን ምን ሥራ እንዲያከናውን ረድተውታል?
7. በቅርቡ መላእክት አምላክ በሚያከናውነው በየትኛው ታላቅ ሥራ ይሳተፋሉ?
ምዕራፍ 12 አንቀጽ 1-7
1. ጸሎት ምንድን ነው? በግላችንም ሆነ ከሰዎች ጋር ሆነን መጸለያችን ተገቢ እንደሆነ እንዴት እናውቃለን?
2. በጸሎት መጨረሻ ላይ “አሜን” ማለታችን ተገቢ የሆነው ለምንድን ነው? ይህስ ምን ማለት ነው?
3. በስብሰባዎች ላይ ጸሎት በሚቀርብበት ጊዜ ወሬ ከማየት ወይም ከመረበሽ ይልቅ በአክብሮት ማዳመጣችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
4. ከነህምያ ጸሎት ምን እንማራለን?
አንቀጽ 8-10
5. ጸሎትን በተመለከተ ልናስታውሰው የሚገባ አስፈላጊ ነገር ምንድን ነው?
6. ስለ ምን ነገሮች ወደ አምላክ መጸለይ እንችላለን?
አንቀጽ 11-17
7. ኢየሱስ ተከታዮቹን ይበልጥ አስፈላጊ ስለሆኑት ስለ የትኞቹ ሦስት ነገሮች እንዲጸልዩ አስተምሯቸዋል?
8. ኢየሱስ ስለ የትኞቹም ነገሮች እንድንጸልይ አስተምሯል?
ምዕራፍ 13 አንቀጽ 1-7
1. የኢየሱስ ደቀ መዝሙር መሆን ሲባል ምን ማለት ነው?
2. የኢየሱስ የመጀመሪያዎቹ ስድስት ደቀ መዛሙርት እነማን ነበሩ? ስለ እያንዳንዳቸውስ ምን ታውቃለህ?
3. ዓሣ ወደ ማጥመድ ሥራቸው የተመለሱት አራት ደቀ መዛሙርት እነማን ናቸው? ይሁን እንጂ ከጊዜ በኋላ ኢየሱስ እንዲከተሉት ላቀረበላቸው ግብዣ ምን ምላሽ ሰጡ?
አንቀጽ 8-12
4. እንዲህ ያሉ ሰዎች የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ከሆኑ በኋላ ምን ለማድረግ ፈቃደኞች መሆን አለባቸው?
5. የኢየሱስን ግብዣ ሳይቀበል የቀረው ሰው ማነው? ለምንስ?
6. ኢየሱስ የመረጣቸው 12 ሐዋርያት እነማን ናቸው?
7. ከ12ቱ ሐዋርያት መካከል ታማኝ ሳይሆን የቀረው ማነው? በእሱስ ምትክ የተመረጠው ማነው?
8. ከ12ቱ ሐዋርያት በተጨማሪ ሐዋርያት የሆኑት ሌሎች ሰዎች እነማን ናቸው?
አንቀጽ 13-16
9. ሴቶች የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ሊሆኑ እንደሚችሉ እንዴት እናውቃለን?
10. እውነተኛ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የሆነ ሰው ምን ማድረግ ይጠበቅበታል? ይህንንስ ሊያሳይ የሚገባው የት ነው?
ምዕራፍ 14 አንቀጽ 1-5
1. መጥፎ ድርጊት የሚያደርጉብንን ሰዎች እንዴት ልንይዛቸው ይገባል?
2. ኢየሱስ ‘ሰባ ሰባት ጊዜ ይቅር ማለት እንዳለብህ’ ሲናገር ምን ማለቱ ነው?
3. ኢየሱስ የጴጥሮስን ጥያቄ ከመለሰ በኋላ ምን አደረገ?
አንቀጽ 6-13
4. ንጉሡ ብዙ ገንዘብ ለተበደረው ባሪያ ምን አደረገለት?
5. ይህ ባሪያ ከእሱ ትንሽ ገንዘብ የተበደረውን ባሪያ ምን አደረገው?
6. ንጉሡ፣ ይቅር ያላለው ባሪያ ስላደረገው ነገር ሲሰማ ምን አደረገ?
አንቀጽ 14-18
7. ኢየሱስ በተናገረው ታሪክ ላይ እንደተጠቀሰው ንጉሥ የሆነው ማነው?
8. ኢየሱስ የተናገረው ታሪክ ምን ትምህርት ይዟል?
9. አንድ ሰው ብዙ ጊዜ ይቅር ያልከው ቢሆንም እንኳ እንደገና በድሎህ ይቅርታ ቢጠይቅህ ምን ታደርጋለህ?
ምዕራፍ 15 አንቀጽ 1-7
1. ጭፍን ጥላቻ ሲባል ምን ማለት ነው? ጭፍን ጥላቻ ተገቢ አይደለም ብለህ የምታምነው ለምንድን ነው?
2. ጭፍን ጥላቻ ያለው አንድ ሰው ኢየሱስን የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ምን ማድረግ እንዳለበት ሲጠይቀው ኢየሱስ በመጀመሪያ ምን አለው?
3. ሰውየው ለነበረበት ጭፍን ጥላቻ ሰበብ ለማቅረብ የሞከረው እንዴት ነው?
አንቀጽ 8-15
4. ኢየሱስ ይህን ሰው ለመርዳት ምን ታሪክ ነገረው?
5. ኢየሱስ ታሪኩን ተናግሮ ሲጨርስ ለሰውየው ምን ጥያቄ አቀረበለት? ሰውየውስ ምን መልስ ሰጠ?
አንቀጽ 16-19
6. ኢየሱስ የተናገረው ታሪክ ባልንጀራችን ማን እንደሆነ የሚያሳየው እንዴት ነው?
7. ይሖዋ ጭፍን ጥላቻ እንደሌለው እንዴት እናውቃለን?
8. ጥሩ ባልንጀራ መሆን የምንችለው እንዴት ነው?