የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
የካቲት 12 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 47 (112)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የጥር 1 መጠበቂያ ግንብ እና የጥር 2007 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ ውይይቱን ለማስቆም “ለሃይማኖት ግድ የለኝም” ለሚል ሰው እንዴት መልስ መስጠት እንደሚቻል የሚያሳይ ይሁን።—ማመራመር ገጽ 17ን ተመልከት።
35 ደቂቃ:-“የይሖዋን ግርማ በሰፊው አውጁ።” በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ። አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በውይይቱ ወቅት ተስማሚ የሆነ ነጥብ ላይ ስትደርስ የመታሰቢያው በዓል የሚከበርበትን ሰዓትና ቦታ እንዲሁም ተጨማሪ የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎች ለማድረግ የተደረገውን ዝግጅት ተናገር። በተጨማሪም በሚያዝያ ወር ረዳት አቅኚ ሆነው ለሚያገለግሉት ጉባኤው ያደረገውን ዝግጅት ተናገር።
መዝሙር 20 (45) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 19 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 7 (19)
5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
20 ደቂቃ:- “የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ ስትጠቀሙ ታላቁን አስተማሪ ምሰሉ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንቀጽ 6ን ስትወያዩ አንድ አስፋፊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 6 መጨረሻ ላይ የሚገኘውን ሣጥን ተጠቅሞ መጽሐፍ ቅዱስ ለሚያስጠናው ሰው ክለሳ ሲያደርግ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
20 ደቂቃ:- በመጋቢት ወር ጥናት ለማስጀመር ግብ ልታወጡ ትችላላችሁ? ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት። በመጋቢት ወር የመጀመሪያ አጋማሽ ላይ ጥናት የማስጀመር ግብ ይዘን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ እናበረክታለን። በጥር 2006 የመንግሥት አገልግሎታችን ከገጽ 3-6 ባለው አባሪ ላይ የሚገኙትን የመግቢያ ሐሳቦች ከልስ። ገጽ 6 ላይ ከቀረቡት የመግቢያ ሐሳቦች መካከል አንዱን ወይም ለአገልግሎት ክልሉ ተስማሚ የሆነ ሌላ መግቢያ በመጠቀም ሰዎችን በምናነጋግርበት በመጀመሪያው ቀን እንዴት ጥናት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ይህን መጽሐፍ ሲያበረክቱ በተለይ ጥናት ያስጀመሩ ካሉ ያገኙትን አበረታች ተሞክሮ እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።
መዝሙር 98 (220) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 26 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 11 (29)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። በገጽ 8 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የጥር 15 መጠበቂያ ግንብ እና የየካቲት 2007 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ አስፋፊው በንግድ አካባቢ ሲያገለግል የሚያሳይ ይሁን።
15 ደቂቃ:- “የቀዘቀዙትን አትርሷቸው።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ከግንቦት 1, 2004 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 21-22 አንቀጽ 13-16 ላይ ተጨማሪ ሐሳብ አቅርብ።
20 ደቂቃ:- “በአገልግሎታችሁ ክርስቶስን ምሰሉ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አድማጮች ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ የተጠቀሱ ጥቅሶችን አንብበው ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።
መዝሙር 66 (155) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መጋቢት 5 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 12 (32)
15 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። የመታሰቢያው በዓል ልዩ የመጋበዣ ወረቀት ለሁሉም አድማጮች እንዲታደል አድርግ። ከዚያም የመጋበዣ ወረቀቱን በአገልግሎት ክልሉ ውስጥ ለማሰራጨት ምን ዝግጅት እንደተደረገ ተናገር። ሁሉም ሙሉ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አበረታታ። የመጋበዣ ወረቀቱን እንዴት መስጠት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
15 ደቂቃ:- ምሥራቹን በተደራጀ መንገድ መስበክ። የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ ከተባለው መጽሐፍ ከገጽ 102 ንዑስ ርዕስ ጀምሮ እስከ ምዕራፉ መጨረሻ ድረስ ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ።
15 ደቂቃ:-“በአደራ የተሰጠን ውድ ሀብት።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አድማጮች ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ በተጠቀሱ ጥቅሶች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።
መዝሙር 57 (136) እና የመደምደሚያ ጸሎት።