የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
መጋቢት 12 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 24 (50)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የየካቲት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የየካቲት 2007 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
15 ደቂቃ:- የምትወዱት ሰው ይሖዋን ማምለኩን ሲያቆም። በመስከረም 1, 2006 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 17-21 ላይ ተመሥርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።
20 ደቂቃ:- “ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት።”* አንቀጽ 3ን ስትወያዩ ለምንጋብዛቸው ሰዎች ስለ መታሰቢያው በዓል ለማስረዳት የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ እንዴት መጠቀም እንደምንችል ከመጋቢት 2006 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 1 አንቀጽ 3 ላይ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።
መዝሙር 74 (168) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መጋቢት 19 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 20 (45)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 2 ላይ ከሚገኘው “የመታሰቢያውን በዓል የሚመለከቱ ማሳሰቢያዎች” ከሚለው ሣጥን ውስጥ ዋና ዋና ነጥቦችን አቅርብ።
20 ደቂቃ:- አገልግሎትህን ማስፋት የምትችልባቸው መንገዶች። የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 10 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ።
15 ደቂቃ:- “መልስህ ምንድን ነው?”* በንቁ! መጽሔት ላይ የሚወጣውን ይህን ርዕስ በቤተሰብ ጥናታችን ላይ እንዴት ማካተት እንደሚቻል የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 51 (127) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መጋቢት 26 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 88 (200)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የመጋቢት ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የየካቲት 15 መጠበቂያ ግንብ እና የመጋቢት 2007 ንቁ! መጽሔቶች ከመታሰቢያው በዓል ልዩ የመጋበዣ ወረቀት ጋር ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
20 ደቂቃ:- ሕይወቴን እንዴት ብጠቀምበት ይሻላል? በሐምሌ 2006 ንቁ! መጽሔት ከገጽ 23-25 ላይ ተመሥርቶ በንግግር የሚቀርብ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ለጀመሩ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች ቃለ ምልልስ አድርግላቸው። የሙሉ ጊዜ አገልግሎትን ለምን መረጡ? ምን በረከቶችንስ አግኝተዋል?
መዝሙር 63 (148) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሚያዝያ 2 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 79 (177)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች ሚያዝያ 15, 2007 ለሚቀርበው ልዩ የሕዝብ ንግግር እንዲጋብዙ አበረታታ።
20 ደቂቃ:- በመታሰቢያው በዓል ላይ የተገኙትን ሰዎች መርዳታችሁን ቀጥሉ። በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። በመታሰቢያው በዓል ዕለት በጉባኤያችሁ የተገኙትን ተሰብሳቢዎች ቁጥር ተናገር፤ እንዲሁም ከተሰብሳቢዎቹ ውስጥ በግምት ምን ያህሎቹ አዲሶች እንደሆኑ ጥቀስ። ልዩ የመጋበዣ ወረቀት በተሰራጨበት ወቅት የተገኙ ግሩም ተሞክሮዎች ካሉ ተናገር፤ ወይም ስብሰባው እንዳለቀ ወደ አስተናጋጆች ቀርበው መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት እንደሚፈልጉ ያሳወቁ ተጋባዦች ካሉ ተሞክሯቸውን ጥቀስ። በበዓሉ ላይ ለተገኙት ሰዎች ተጨማሪ መንፈሳዊ እርዳታ መስጠት የምንችልባቸውን አንዳንድ መንገዶች ጥቀስ። (የመጋቢት 2006 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 1 አንቀጽ 5ን፤ የየካቲት 2005 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 4 አንቀጽ 9ን በተጨማሪም የየካቲት 2004 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 5 አንቀጽ 16ን ተመልከት።) አስፋፊዎች ዛሬ ነገ ሳይሉ ተከታትለው እንዲረዷቸው አበረታታ።
15 ደቂቃ:- የ2007ን የዓመት መጽሐፍ በጥሩ ሁኔታ ተጠቀሙበት። በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 3 ላይ የሚገኘውን “ከበላይ አካል የተላከ ደብዳቤ” ዋና ዋና ነጥቦች ከልስ። በየካቲት 1, 2007 መጠበቂያ ግንብ ላይ ከወጣው “ዓለም አቀፍ ሪፖርት” ላይ ጎላ ያሉ አኃዛዊ መረጃዎችን ጥቀስ። እንግሊዝኛ የሚችሉ ቤተሰቦች ሙሉውን መጽሐፍ በዓመት ውስጥ አንብበው እንዲጨርሱ አበረታታ። ይህን መጽሐፍ በመጠቀም አዲሶች ስለ ይሖዋ ድርጅት እንዲያውቁ መርዳትና በስብሰባዎች ላይ እንዲገኙ ማበረታታት የምንችልባቸውን አንዳንድ መንገዶች ግለጽ።
መዝሙር 4 (8) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
[የግርጌ ማስታወሻዎች ]
አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።