ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት
ክለሳ ሚያዝያ 30, 2007 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከመጋቢት 5 እስከ ሚያዝያ 30, 2007 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል። [ማሳሰቢያ፦ ከጥያቄው ቀጥሎ መልሱ የሚገኝበት ጽሑፍ ካልተጠቀሰ መልሱን ለማግኘት በግልህ ምርምር ማድረግ ይኖርብሃል።—የአገልግሎት ትምህርት ቤት ገጽ 36-37ን ተመልከት።]
የንግግር ባሕርይ
1. አስተዋጽኦው ቅልብጭ ያለ እንዲሆን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? [be ገጽ 168 አን. 4]
2. ትምህርቱን መልክ ባለው መንገድ ለማቅረብ የሚረዱንን አራት መንገዶች ዘርዝር። [be ገጽ 170 አን. 3 እስከ ገጽ 172 አን. 4]
3. በአንድ ንግግር ላይ የምናካትታቸውን ነጥቦች ስንመርጥ ምን ነገሮችን ማስታወስ ይኖርብናል? [be ገጽ 173 አን. 1-2]
4. በራስ አባባል መናገር የሚያስገኛቸው አንዳንድ ጥቅሞች ምንድን ናቸው? [be ገጽ 175 አን. 2-4]
5. በጭውውት መልክ መናገር አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ይህን ችሎታ ማዳበር የምንችለውስ እንዴት ነው? [be ገጽ 179 አን. 4፣ ሣጥኑ፤ ገጽ 180፣ ሣጥኑ]
ክፍል ቁጥር 1
6. አንድ ወንድም የሳምንቱን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ጎላ ያሉ ነጥቦች እንዲያቀርብ ክፍል ሲሰጠው መዘጋጀት የሚኖርበት እንዴት ነው? [be ገጽ 47 አን. 3-4]
7. የክርስቶስ ቤዛ ለእኛ ከሚያስገኘው ጥቅም በላይ በዋነኝነት ያስፈለገበት ምክንያት ምንድን ነው? [w05 11/1 ገጽ 14 አን. 1]
8. አንድ ተናጋሪ ለሕዝብ በሚቀርብ ንግግር አስተዋጽኦ ላይ ያሉትን ተጨማሪ ጥቅሶች እንዴት ሊጠቀምባቸው ይገባል? [be ገጽ 53 አን. 1-2]
9. ኢየሱስ ያስተማረበት ዓላማ ምን ነበር? እርሱን መኮረጅ የምንችለውስ እንዴት ነው? [be ገጽ 57 አን. 1]
10. በምናስተምርበት ጊዜ ነገሮችን እያነጻጸሩ ማቅረብ ውጤታማ የሆነው ለምንድን ነው? [be ገጽ 57 አን. 3-4]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. በኤርምያስ 6:16 ላይ ‘በመልካሟና በጥንቷ መንገድ’ መጓዝ እንዳለብን የሚናገረውን ምክር ተግባራዊ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?
12. ይሖዋ ታማኝ ያልነበሩትን እስራኤላውያን ለማስተማር ሽመላን እንደ ምሳሌ አድርጎ የተጠቀመው ለምን ነበር? እኛስ ከዚህ ምን እንማራለን? (ኤር. 8:7)
13. በዛሬ ጊዜ ስላለው መዝናኛ ባለን አመለካከት ረገድ በኤርምያስ 15:17 ላይ የሚገኘውን ትምህርት ተግባራዊ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?
14. የሰው ልጆች በታላቁ ሸክላ ሠሪ በይሖዋ እጅ ውስጥ እንዳለ ጭቃ የሆኑት እንዴት ነው? (ኤር. 18:5-11)
15. በኤርምያስ 25:17-26 ላይ ብሔራት የተጠቀሱበት ቅደም ተከተል ለዘመናችን ምን ትርጉም አለው?