ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ሚያዝያና ግንቦት:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ተመላልሶ መጠየቅ በምታደርጉበት ወቅት ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ አበርክቱ። ሰኔ:- ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? ሐምሌ:- ብሮሹሮች።
◼ በዚህ ዓመት ለሚደረገው የአውራጃ ስብሰባ የሚሆኑ ደረት ላይ የሚለጠፉ ባጅ ካርዶች ከጽሑፎች ጋር ስለሚላኩላችሁ ማዘዝ አያስፈልጋችሁም። ይሁን እንጂ ጉባኤው ተጨማሪ ካርድ ካስፈለገው በጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S-14) ማዘዝ ይኖርበታል። በጉባኤያችሁ ውስጥ የባጅ መያዣ ፕላስቲክ የሚፈልጉ ካሉ ማዘዝ ይኖርባችኋል።
◼ የጉባኤ ጸሐፊዎች የዘወትር አቅኚነት አገልግሎት ማመልከቻ ቅጽ (S-205) እና የረዳት አቅኚነት አገልግሎት ማመልከቻ ቅጽ (S-205b) በበቂ መጠን ሊኖራቸው ይገባል። እነዚህ ቅጾች እንዲላኩላችሁ በጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S-14) መጠየቅ ይቻላል። ቢያንስ ለአንድ ዓመት የሚበቁ ቅጾች ይኑሯችሁ። የዘወትር አቅኚነት ማመልከቻ ቅጾችን ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው ከመላካችሁ በፊት በደንብ መሞላታቸውን ማረጋገጥ አለባችሁ።
◼ ቅርንጫፍ ቢሮው የሁሉንም ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቾችና ጸሐፊዎች ወቅታዊ አድራሻና ስልክ ቁጥር ማግኘት ይፈልጋል። የአድራሻ ለውጥ በሚኖርበት ጊዜ የጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ የሰብሳቢ የበላይ ተመልካች/የጸሐፊ የአድራሻ ለውጥ ማሳወቂያ ቅጽ (S-29) ሞልቶና ፈርሞ በፍጥነት ለቅርንጫፍ ቢሮው መላክ አለበት። የስልክ ቁጥር ለውጥ ሲኖርም እንደዚህ መደረግ ይኖርበታል።
◼ በማንኛውም ጊዜ ወደ ሌላ አገር ለመጓዝ ስታስቡ እዚያ በሚደረጉ የጉባኤ፣ የልዩና የወረዳ ወይም የአውራጃ ስብሰባዎች ላይ የመገኘት እቅድ ካላችሁ ስብሰባዎቹ የሚደረጉበትን ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ ለማወቅ ጥያቄያችሁን የምትልኩት የዚያን አገር ሥራ በበላይነት ለሚከታተለው ቅርንጫፍ ቢሮ መሆን ይኖርበታል። የቅርንጫፍ ቢሮዎችን አድራሻ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ከተባለው መጽሐፍ መጨረሻ ገጽ ላይ ማግኘት ይቻላል።